የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ፖለቲካ እና ደህንነት

በድሬዳዋ ባለፉት ዓመታት የተመዘገቡ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስኬቶች ተጠናክረው ይቀጥላሉ

Jul 20, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ድሬዳዋ፤ ሐምሌ 12/2018 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ባለፉት አምስት ዓመታት በልማትና በመልካም አስተዳደር የተመዘገቡ ስኬቶች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግስት ዋና ተጠሪ ኢብራሒም ዩሱፍ ገለጹ።

የአስተዳደሩ ምክርቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ኢብራሒም ዩሱፍ ዛሬ በሰጡት መግለጫ እንደገለጹት፤ ባለፉት አምስት ዓመታት ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ያደረጉ የልማት ሥራዎች ተከናውነዋል።

በተለይ የገጠርና የከተማ ነዋሪዎችን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች በተቀናጀ መንገድ ለመፍታት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ መሆናቸውን አንስተዋል።

የድሬዳዋን የንግድ፣ የኢንዱስትሪ እና የአገልግሎት ማዕከልነት በተጨባጭ ያረጋገጡ አዳዲስ አምራች ኢንዱስትሪዎች እንዲሁም ደረጃቸውን የጠበቁ ዘመናዊ ሆቴሎችና የሎጅስቲክ ማሳለጫ ማዕከላት ተገንብተው ለአገልግሎት መብቃታቸውን አስረድተዋል።

በተለይ በመጀመሪያው ምዕራፍ በከተማዋ ዋና ዋና አካባቢዎች ከ16 ኪሎ ሜትር በላይ የተከናወነው የኮሪደር ልማት ድሬዳዋን ጽዱ፣ ውብና ለኑሮ ተመራጭ እያደረጋት መምጣቱን ገልጸዋል።

ታሪካዊ ቅርሶችን በጠበቀና ገጽታዋን በሚገነባ መልኩ የተከናወነው የኮሪደር ልማት በከተማዋ አዳዲስ መሠረተ ልማቶች እንዲስፋፉ ማድረጉንም ጠቁመዋል።

መሰረተ ልማቶቹ ባለሀብቶችን ከመሳብ በተጨማሪ የትራፊክ መጨናነቅን በማስቀረት የተሽከርካሪ አደጋን ለመቀነስ አስችለዋል ብለዋል።

በመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የፌደራልና የአስተዳደሩ ተቋማት ተቀናጅተው ፈጣንና ቀልጣፋ ዲጂታል አገልግሎት በመስጠታቸው የዘመናት የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን እየፈታ መሆኑንም አቶ ኢብራሒም ተናግረዋል።

እንደ እሳቸው ገለጻ በቅዳሜና እሁድ ገበያዎች የኢንዱስትሪና የግብርና ምርቶችን ለሕብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ የኑሮ ውድነትን ማቅለል የሚያስችል ውጤታማ ሥራ ተከናውኗል።

በአስተዳደሩ አገልግሎት መስጠትና ማምረት በጀመሩ ተቋማትና ኢንዱስትሪዎች በብዙ ሺህ ለሚገመቱ ወጣቶች የሥራ ዕድል ለመፍጠር መቻሉንም የመንግስት ዋና ተጠሪው አንስተዋል።

በኢንተርፕራይዝ የተደራጁ ወጣቶችን ውጤታማ ለማድረግ የስልጠና፣ የመስሪያ ቦታ፣ የብድርና የሙያ ድጋፍ መሰጠቱንም አመልክተዋል።

ባለፉት 5 ዓመታት በሁሉም ዘርፍ የተመዘገቡ ውጤቶችን በላቀ ደረጃ ለማሳደግ አስተዳደሩ የተቀናጀ እንቅስቃሴ መጀመሩንም አቶ ኢብራሒም ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በክልሉ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የተጀመሩ ስራዎችን ማጠናከር ይጠበቅባቸዋል- ርእሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)

ሆሳዕና ፤ ነሐሴ 21/2018 (ኢዜአ) ፦ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ...

Aug 28, 2026

በኢሉባቦር ዞን በኩታ ገጠም ከለማው የበቆሎ ሰብል የተሻለ ምርት ለማገኘት የእንክብካቤ ስራ ተጠናክሯል

መቱ፤ ነሐሴ 11/2018 (ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል በኢሉባቦር ዞን በክረምት እርሻ እየለማ ከሚገኘው የበቆሎ ሰብል የላቀ ምርት ለማገኘት የሰብል እንክብካቤና ጥ...

Aug 18, 2026

በሲዳማ ክልል የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማትን በማሻሻል ለሕዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ ናቸው

ሀዋሳ፤ ነሐሴ 2/2018 (ኢዜአ)፦ በሲዳማ ክልል የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማትን በማሻሻል ለሕዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ መሆና...

Aug 10, 2026

በክልሉ በበጀት ዓመቱ ውጤታማ የልማት ሥራዎች ተከናውነዋል 

አዳማ፤ ሐምሌ 12/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል በበጀት ዓመቱ ሰላምና መልካም አስተዳደርን ከማረጋገጥ ጎን ለጎን ውጤታማ የልማት ሥራዎች መከናወናቸውን የክል...

Jul 20, 2026