የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ፖለቲካ እና ደህንነት

በክልሉ ከተሞችን ለነዋሪዎች ምቹ ለማድረግ የተከናወኑ ተግባራት ተጨባጭ ውጤት አምጥተዋል

Aug 5, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ቡታጅራ ፤ ሐምሌ 28/2018 (ኢዜአ) ፦በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከተሞችን ለነዋሪዎች ምቹ ለማድረግ የተከናወኑ ተግባራት ተጨባጭ ውጤት ማምጣታቸውን የክልሉ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ገለፀ።

ቢሮው አንድነት ለፅዳት፣ ትጋት ለአገልግሎት፣ ውሳኔ ለልማት በሚል መሪ ሀሳብ ያዘጋጀው የምክክር ጉባኤ በቡታጅራ ከተማ እየተካሄደ ነው።


በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የኢንዱስትሪ ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ሀላፊ አቶ ስንታየሁ ወልደሚካኤል በወቅቱ እንዳሉት፤ በ2018 በጀት ዓመት በክልሉ ከተሞችን በማህበረሰብ ተሳትፎ በማልማት ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ማሳደግ ተችሏል።

በክልሉ መንግስት ለከተሞች ልማት ከመደበው በጀት ባለፈ ህብረተሰቡ ከ2 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ ማዋጣቱን ተናግረዋል።

በዚህም የውስጥ ለውስጥ አስፓልትን ጨምሮ የመንገድ፣ የውሃና ሌሎች መሰረተ ልማት ስራዎች ተደራሽነትን በማስፋት የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ተችሏል ብለዋል።

ከተሞችን ውብና ለነዋሪዎች ምቹ ለማድረግ በክልሉ ሰባት ከተሞች በሁለት ምዕራፍ 165 ኪሎ ሜትር የኮሪደር ልማት ስራ እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የክልሉን ከተሞች የብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ የተጀመሩ ስራዎችን ለማጠናከርና የተስተዋሉ ጉድለቶችን ለማረም የምክክር መድረኩ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት አመልክተዋል።

የምስራቅ ጉራጌ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ደሱ አበጋዝ በበኩላቸው፤ በዞኑ በበጀት ዓመቱ የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ በርካታ የልማት ስራዎች ተጠናቀው ለአገልግሎት ክፍት ስለመደረጋቸው ተናግረዋል።


ከተሞችን ውብና ፅዱ ለነዋሪዎች ምቹ ለማድረግ በተጀመሩ ስራዎች በቡታጅራ ከተማ በመጀመሪያ ምዕራፍ እየተተገበረ ከሚገኘው 21 ኪሎ ሜትር የኮሪደር ልማት ስራ ውስጥ 11 ነጥብ 26 ኪሎ ሜትር የሚሆነው ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት ስለመደረጉም ጠቅሰዋል።

የከተማዋን የአገልግሎት አሰጣጥ በማዘመን የማህበረሰቡን እርካታ ለማረጋገጥ እየተሰራ መሆኑንም ገልጸዋል።

በምክከር መድረኩ የክልል፣ የዞን፣ የልዩ ወረዳ፣ የወረዳና የከተማ አስተዳደር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና የዘርፉ ባለሙያዎች እየተሳተፉ ነው።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

ሀብትን አውቆና አበልጽጎ ለትውልድ የሚተርፍ ወረት መፍጠር የመደመር መንግሥት ዋነኛ ዓላማ ነው - አቶ ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 5/2019 (ኢዜአ)፦የመደመር መንግሥት ዋና ዓላማ ያሉትን ሀብቶች አውቆና አበልጽጎ ለተከታዩ ትውልድ የሚተርፍ ወረት መፍጠር መሆኑን የኢፌ...

Oct 16, 2026

ኢትዮጵያ በሰጥቶ መቀበል መርህ የባህር በር ባለቤት ለመሆን የምታደርገው ጥረት ለቀጣናው ሰላም ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው

ዲላ፤ መስከረም 29/2019 (ኢዜአ) ፦ኢትዮጵያ በሰጥቶ መቀበል መርህ የባህር በር ባለቤት ለመሆን እያደረገች ያለው ጥረት ለቀጠናው ሰላምና መረጋጋት ያላትን ቁ...

Oct 10, 2026

በገጠር ዘመናዊ ህይወት መኖር ጀምረናል፤ የዚህ እድል ተጠቃሚ በመሆናችንም ተደስተናል- አርሶ አደሮች

ሚዛን አማን፣ መስከረም 13/2019 (ኢዜአ)፡-በገጠር ዘመናዊ ህይወት መኖር ጀምረናል፤ የዚህ እድል ተጠቃሚ በመሆናችንም ተደስተና ሲሉ በካፋ ዞን የሺሾ እንዴ ...

Sep 24, 2026

በክልሉ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የተጀመሩ ስራዎችን ማጠናከር ይጠበቅባቸዋል- ርእሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)

ሆሳዕና ፤ ነሐሴ 21/2018 (ኢዜአ) ፦ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ...

Aug 28, 2026