የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ፖለቲካ እና ደህንነት

በሲዳማ ክልል አርሶ አደሩን ከእንስሳት ልማቱ ተጠቃሚ ለማድረግ የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ ሆነዋል

Aug 10, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ይርጋለም፤ ነሀሴ 1/2018 (ኢዜአ)፡-አርሶ አደሩን ከእንስሳት ልማቱ ተጠቃሚ ለማድረግ በመኖ አቅርቦትና ጤና አጠባበቅ ላይ የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ መሆናቸውን የሲዳማ ክልል የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አብርሀም ማርሻሎ ተናገሩ።

የሲዳማ ክልል እንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ የ2019 በጀት ዓመት የእንስሳት መኖ ልማትና የበሽታ መከላከያ ክትባት ሥራዎች ይፋዊ ማስጀመሪያ መርሀግብር በይርጋዓለም ከተማ ተካሂዷል።


‎በመርሀግብሩ ላይ የሲዳማ ክልል የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አብርሀም ማርሻሎ በክልሉ የአርሶ አደሩን ከእንስሳት ልማቱ ተጠቃሚ ለማድረግ የተከናወኑ የመኖ አቅርቦትና ጤና አጠባበቅ ተግባራት ውጤታማ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ዘመናዊ የእንስሳት እርባታ ዘዴው ‎ለእንስሳት ዝርያ ማሻሻል፣ ለመኖ አቅርቦትና ለጤና አጠባበቅ ሥራ ከፍተኛ እገዛ ማድረጉንም ገልጸዋል።

‎አርሶ አደሩ የመኖ አቅርቦቱን ከሌማት ቱሩፋት ሥራ ጋር በማቀናጀትና የተሻሻሉ የእንስሳት ዝርያዎችን በመጠቀም ምርታማነቱን ማሳደጉን ጠቁመዋል።

የክልሉ መንግስት የአርሶ አደሩን ከእንስሳት ልማቱ ተጠቃሚ ለማድረግ ከሚያደርገው ሞያዊ እገዛ በተጨማሪ የተሻሻሉ የእንስሳት ዝርያዎችን ማቅረቡን አንስተዋል።


የክልሉ እንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ አሰፋ ፎና በክልሉ የሌማት ትሩፋት መርሀግብር ከመጀመሩ በፊት 170 ሺህ የነበረው የተሻሻሉ የዳልጋ ከብቶች ቁጥር በአሁኑ ወቅት ወደ 600 ሺህ ለማሳደግ መቻሉን አብራርተዋል።

ይህም የክልሉን የእንስሳትና እንስሳት ተዋጽኦ ከማሳደግ ባለፈ የአርሶ አደሩን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት መሳደጉን አንስተዋል።

ከዚህ በተጓዳኝም የእንስሳት መኖ አቅርቦትን ለማስፋት በተደረገ ጥረት በበጀት ዓመቱ ከ32 ሺህ ሄክታር በሚበልጥ መሬት ላይ ልማቱ መካሄዱን ጠቁመዋል።

በክልሉ የእንስሳት ጤናን ለመጠበቅም የበሽታ መከላከልና ክትባት ሽፋኑንለማሳደግ በቅንጅት መሰራቱን አስረድተዋል።

ይህም የሌማት ትሩፋት መርሀ ግብር ለማሳካትና የአርሶ አደሩ ተጠቃሚነት ከማሳድግ ባለፈ ለኢንዱስትሪዎች ግብአት ለማቅረብ አስችሏል ብለዋል።


በይርጋዓለም ከተማ ጋኔ ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር ደረጀ ሙጤ የተሻሻሉ ዝርያ ያላቸው የወተት ላሞች በማርባት ወተትና የወተት ተዋጾን ለገበያ በማቅረብ ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ለእንስሳቱም በግማሽ ሄክታር መሬታቸው ላይ የመኖ ሣር በማልማት ውጤታማነታቸውን ለማጉላት እየሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል።

‎የእንስሳቱን ምርታማነት ለማሳደግ የምጥን መኖ አቅርቦትና ጤናቸውን መከታተል ላይ የባለሞያ ድጋፍ ማግኘታቸውንም ጠቁመዋል።


በማስጀመሪያ መርሀ ግብሩ ላይ የሲዳማ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ፋንታዬ ከበደን ጨምሮ የክልል፣ የዞን፣ የወረዳና የከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች የተገኙ ሲሆን በይርጋለም ከተማም የተለያዩ የሌማት ትሩፋት ስራዎች ተጎብኝተዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በክልሉ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የተጀመሩ ስራዎችን ማጠናከር ይጠበቅባቸዋል- ርእሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)

ሆሳዕና ፤ ነሐሴ 21/2018 (ኢዜአ) ፦ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ...

Aug 28, 2026

በኢሉባቦር ዞን በኩታ ገጠም ከለማው የበቆሎ ሰብል የተሻለ ምርት ለማገኘት የእንክብካቤ ስራ ተጠናክሯል

መቱ፤ ነሐሴ 11/2018 (ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል በኢሉባቦር ዞን በክረምት እርሻ እየለማ ከሚገኘው የበቆሎ ሰብል የላቀ ምርት ለማገኘት የሰብል እንክብካቤና ጥ...

Aug 18, 2026

በሲዳማ ክልል የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማትን በማሻሻል ለሕዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ ናቸው

ሀዋሳ፤ ነሐሴ 2/2018 (ኢዜአ)፦ በሲዳማ ክልል የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማትን በማሻሻል ለሕዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ መሆና...

Aug 10, 2026

በክልሉ በበጀት ዓመቱ ውጤታማ የልማት ሥራዎች ተከናውነዋል 

አዳማ፤ ሐምሌ 12/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል በበጀት ዓመቱ ሰላምና መልካም አስተዳደርን ከማረጋገጥ ጎን ለጎን ውጤታማ የልማት ሥራዎች መከናወናቸውን የክል...

Jul 20, 2026