የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ፖለቲካ እና ደህንነት

ኢትዮጵያ ከአህጉራዊ የልማት ዕቅዶች ጋር የተጣጣመ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የግብርና ምርታማነት አቅም እየገነባች ነው

Aug 19, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 12/2018 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ ከአህጉራዊ የልማት ዕቅዶች ጋር የተጣጣመ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የግብርና ምርታማነት አቅም እየገነባች መሆኗን የግብርና ሚኒስቴር ገለጸ።

የምሥራቅ አፍሪካ ልማት በይነ-መንግሥታት (ኢጋድ) አባል ሀገራት የግብርና ትራንስፎርሜሽን አፈጻጸም ግምገማ እና ከ2026 እስከ 2035 የሚተገበረውን የካምፓላ ድንጋጌ ማዕቀፍ አስመልክቶ በአዲስ አበባ ሲካሄድ የቆየው የሁለት ቀናት መድረክ ተጠናቋል።

የግብርና ሚኒስትር አማካሪ ዜና ሀብተወልድ እንዳሉት፤ በኢትዮጵያ የግብርና ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ የሚያስችሉ ውጤታማ ተግባራት ተከናውነዋል።

ሀገሪቱ የዘርፉን ምርታማነት ለማሳደግ በሌማት ትሩፋት፣ በመስኖ ስንዴ እና በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብሮች ላይ ትኩረት በመስጠት ስኬታማ መሆኗን ጠቁመዋል።

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ደረጃ በአጀንዳ 2063 የተቀመጠውን የበለጸገች አፍሪካን የመፍጠር ርዕይ ለማሳካት የሚያስችሉ ሥራዎችን በቁርጠኝነት እያከናወነች ትገኛለች ብለዋል።

በመሆኑም አህጉራዊ አቅጣጫዎችን ከሀገራዊ እቅዶች ጋር በማጣጣም የግብርናውን ዘርፍ ይበልጥ ለማሳደግ እና የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ በትኩረት እንደሚሠራ ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ የግብርና ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ የሚያስችሉ ውጤታማ ተግባራት ተከናውነዋል።

ኢትዮጵያ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ እና ምርታማነትን ለማሳደግ በሌማት ትሩፋት፣ በበጋ መስኖ ስንዴና በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብሮች ላይ ትኩረት በመስጠት ስኬታማ ተግባራትን ማከናወኗን አስረድተዋል።

በምሥራቅ አፍሪካ ልማት በይነ-መንግሥታት (ኢጋድ) የፖሊሲና የምግብ ዋስትና ኤክስፐርት ሲልቪያ ሄንጋ (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም የሚያስችሉ ቴክኖሎጂዎችን ለአርሶ አደሩ ማዳረስና አቅሙን መገንባት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።

ሀገራዊ እና ቀጣናዊ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እሴት መጨመር፣ በድህረ-ምርት አስተዳደር እንዲሁም አህጉር አቀፍ የንግድ ትስስርን ማጠናከር ላይ ልዩ ትኩረት ሊደረግ እንደሚገባ ገልጸዋል።

በተጨማሪም ሕፃናት እና እናቶች የተመጣጠነ ምግብና አስፈላጊ ንጥረ ነገሮችን እንዲያገኙ መሥራት ወሳኝ መሆኑን አንስተው፣ አባል ሀገራት የግብርና ሥርዓቱን ለማሻሻል በቁርጠኝነት ሊሠሩ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በኢሉባቦር ዞን በኩታ ገጠም ከለማው የበቆሎ ሰብል የተሻለ ምርት ለማገኘት የእንክብካቤ ስራ ተጠናክሯል

መቱ፤ ነሐሴ 11/2018 (ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል በኢሉባቦር ዞን በክረምት እርሻ እየለማ ከሚገኘው የበቆሎ ሰብል የላቀ ምርት ለማገኘት የሰብል እንክብካቤና ጥ...

Aug 18, 2026

በሲዳማ ክልል የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማትን በማሻሻል ለሕዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ ናቸው

ሀዋሳ፤ ነሐሴ 2/2018 (ኢዜአ)፦ በሲዳማ ክልል የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማትን በማሻሻል ለሕዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ መሆና...

Aug 10, 2026

በክልሉ በበጀት ዓመቱ ውጤታማ የልማት ሥራዎች ተከናውነዋል 

አዳማ፤ ሐምሌ 12/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል በበጀት ዓመቱ ሰላምና መልካም አስተዳደርን ከማረጋገጥ ጎን ለጎን ውጤታማ የልማት ሥራዎች መከናወናቸውን የክል...

Jul 20, 2026

የአየር ማረፊያው ለአገልግሎት መብቃት የአካባቢውን የንግድ፣ የኢንቨስትመንትና የቱሪዝም እንቅስቃሴ በከፍተኛ ሁኔታ የሚያነቃቃ ነው-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

አዲስ አበባ ፤ሐምሌ 5 /2018 (ኢዜአ)፦የአየር ማረፊያው ለአገልግሎት መብቃትም የአካባቢውን የንግድ፣የኢንቨስትመንትና የቱሪዝም እንቅስቃሴ በከፍተኛ ሁኔታ በማ...

Jul 13, 2026