🔇Unmute
ነሐሴ 27/ 2018 (ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የአምራች ኢንዱስትሪዎችን ምርታማነት በማሳደግ እና አዳዲስ ባለሀብቶችን በመሳብ የላቀ ውጤት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ገለፀ።
የቢሮው የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ትውውቅ መድረክ በባህር ዳር ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

የቢሮው ኃላፊ አቶ እንድሪስ አብዱ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፤ የክልሉን የመልማት አቅም መሠረት በማድረግ የኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ዘርፍን ለማሳደግ ወደ ስራ ተገብቷል።
በዚሁ መሠረት 174 አዳዲስ መካከለኛና ከፍተኛ ኢንዱስትሪዎች አስፈላጊው ድጋፍና እገዛ ተደርጎላቸው ወደ ማምረት እንዲገቡ መደረጉን ተናግረዋል።
የኢንዱስትሪዎችን የማምረት አቅም ለማሳደግ በተደረገው ጥረትም የምርታማነት አቅማቸውን ከ59 በመቶ ወደ 65 በመቶ ማሳደግ እንደተቻለ ነው የጠቆሙት።
በ"ኢትዮጵያ ታምርት" ንቅናቄም 77 ኢንዱስትሪዎች ወደ ማምረት እንዲገቡ መደረጉን ገልጸዋል።
በበጀት ዓመቱ በ583 ኢንዱስትሪዎች የተመረተ ከ789 ሺህ ቶን በላይ የተለያዩ ምርቶችን ለአገር ውስጥ ገበያ በማቅረብ ከ1 ቢሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ ማዳን ተችሏል ነው ያሉት።
በተጨማሪም በ45 ኢንዱስትሪዎች የተመረተ ከ154 ሺህ ቶን በላይ ምርት ለውጭ ሀገራት ገበያ በማቅረብ ከ206 ሚሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ ገቢ መገኘቱን አብራርተዋል።
በዘርፉ ከ100 ሺህ ለሚበልጡ ዜጎች የሥራ ዕድል በመፍጠር የኢኮኖሚ ተጠቃሚ ማድረግ እንደተቻለም አክለው ገልጸዋል።

አዳዲስ ባለሀብቶችን ወደ ክልሉ ለመሳብ በተደረገው እንቅስቃሴም ከ553 ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል ላስመዘገቡ 3 ሺህ 961 ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ ተሰጥቷል።
ባለሀብቶቹ በግብርና፣ ኢንዱስትሪ፣ ሆርቲካልቸር እና አገልግሎት ዘርፎች የሚሰማሩ ሲሆን፣ ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ እንዲገቡ የቦታ አቅርቦትና ሌሎች አስፈላጊ ድጋፎች እየተደረጉላቸው ይገኛል።
በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የአምራች ኢንዱስትሪዎችን ምርታማነት በማሳደግ፣ አዳዲስ ባለሀብቶችን በማሳተፍ፣ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በመተካትና ለውጭ ገበያ የሚቀርቡ ምርቶችን በማምረት በኩል አበረታች ውጤት ተመዝግቧል ብለዋል።
የተገኘውን ውጤት እንደ መነሻ በመውሰድ በ2019 በጀት ዓመት ቅንጅታዊ አሠራርን በማጠናከር የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ ርብርብ ይደረጋል ብለዋል።
በመድረኩ በየደረጃው የሚገኙ የዘርፉ አመራሮችና ባለሙያዎች በመሳተፍ ላይ ናቸው።
ሆሳዕና ፤ ነሐሴ 21/2018 (ኢዜአ) ፦ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ...
Aug 28, 2026
መቱ፤ ነሐሴ 11/2018 (ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል በኢሉባቦር ዞን በክረምት እርሻ እየለማ ከሚገኘው የበቆሎ ሰብል የላቀ ምርት ለማገኘት የሰብል እንክብካቤና ጥ...
Aug 18, 2026
ሀዋሳ፤ ነሐሴ 2/2018 (ኢዜአ)፦ በሲዳማ ክልል የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማትን በማሻሻል ለሕዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ መሆና...
Aug 10, 2026
አዳማ፤ ሐምሌ 12/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል በበጀት ዓመቱ ሰላምና መልካም አስተዳደርን ከማረጋገጥ ጎን ለጎን ውጤታማ የልማት ሥራዎች መከናወናቸውን የክል...
Jul 20, 2026