🔇Unmute
የሌማት ትሩፋት በዋናነት የእንስሳት ተዋጽኦ ምርቶችን ማለትም ወተት፣ ሥጋ፣ እንቁላልና ማርን በስፋት በማምረት የኢትዮጵያን የምግብ ሉዓላዊነትና የሥርዓተ-ምግብ ዋስትና ማረጋገጥን አላማ በማድረግ እየተተገበረ ያለ ሀገራዊ ኢኒሼቲቭ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሌማት ትሩፋትን በጥቅምት ወር 2018 ዓ.ም በአርባምንጭ ከተማ በይፋ አስጀምረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በወቅቱ ባስተላለፉት መልዕክት በምግብ ራስን አለመቻል የሀገርን ክብር እንደሚነካና፣ ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን ካልቻለች ሙሉ ነፃነት ሊኖራት እንደማይችል ገልጸዋል።
በስንዴ ምርት የታየውን ስኬት በሌማት ትሩፋት መደገም እንዳለበትም አሳስበዋል።
ጤናማና አምራች ትውልድ ለመፍጠርም ሀገራዊ ሌማታችንን በተመጣጠነ ምግብ ማሟላት እንደሚገባ አብራርተዋል።
የሌማት ትሩፋት ዋና ግብ በቤተሰብ ደረጃ የተመጣጠነ ምግብን ተደራሽ በማድረግ የህፃናት መቀንጨርን መቀነስ፣ ለወጣቶችና ለሴቶች ሰፊ የሥራ ዕድል መፍጠር፣ እንዲሁም የዜጎችን ኑሮ ማሻሻል መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።
ይህ ሀገራዊ መርሐ ግብር የተለያዩ እና አጋዥ የሆኑ የትኩረት መስኮችን ይዞ መንቀሳቀሱን ቀጥሏል።
የወተት ላሞችን ዝርያ በማሻሻል የወተት ምርትን ማሳደግ፣ የዶሮ ሥጋና እንቁላልን በቤተሰብ ደረጃ ተደራሽ ማድረግ፣ እንዲሁም ዘመናዊ ቀፎዎችን በመጠቀም የማር ጥራትና ምርት መጨመር ቁልፍ ምሰሶዎች ናቸው።
ከዚህ ጎን ለጎንም ግብርናንና የእንስሳት እርባታን የከተማ ግብርና አካል የማድረግ ሰፊ የንቅናቄ እንቅስቃሴ መፈጠሩ ትልቅ መሻሻል ነው።
የዶሮና የእንቁላል ምርት በከፍተኛ ሁኔታ ማደጉ ብቻ ሳይሆን፣ በብዙ ክልሎች የወተት ማቀነባበሪያ ፋብሪካዎችና የመሰብሰቢያ ማዕከላት በስፋት ተስፋፍተዋል።
የሌማት ትሩፋት ለወጣቶችና ለሴቶች ሰፊ የሥራ ዕድል በመፍጠር አስተማማኝ የገቢ ምንጭ ሆኗል።
አርሶ አደሩ ከመደበኛው የሰብል ምርቱ በተጓዳኝ በየዕለቱ ገቢ ማግኘት መቻሉ የኑሮ ደረጃውን በከፍተኛ መጠን እንዲያሻሽል አግዞታል።
በፕሮቲን በበለጸጉ ምግቦችን በተለይም እንቁላልና ወተትን ለህጻናትና ለነፍሰ ጡር እናቶች ተደራሽ በማድረግ ረገድ አበረታች ለውጦች ታይተዋል።
በሀገር አቀፍ ደረጃ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የአንድ ቀን ጫጩቶች፣ ዝርያቸው የተሻሻሉ የወተት ላሞችና ዘመናዊ የንብ ቀፎዎች ለአርሶ አደሩና ለከተማ ነዋሪው ተደራሽ መደረጋቸው ተችሏል።
ይህም ቀደም ሲል በግዢ ብቻ ይሟሉ የነበሩ የምግብ ምርቶች አሁን ላይ በብዙ ቤተሰቦች ጓሮ በራሳቸው እንዲመረቱ አድርጓል።
ይህ ተሞክሮ በቤተሰብ ደረጃ የፕሮቲን አቅርቦትን በማሳደግ በሕፃናት ላይ የሚታየውን የምግብ እጥረትና መቀንጨር ለመቀነስ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል።
በተለይም የከተማ ግብርናን በማስፋት ነዋሪው በውስን ቦታ ምርታማ መሆን እንደሚችል በተግባር የታየበትና በምግብ ራስን የመቻል ጉዞ ተስፋ ሰጪ ውጤቶች ታይተዋል።
በተጨማሪም ጥራት ያለው የማርና የሥጋ ምርት ለውጭ ገበያ ለማቅረብ የተጀመሩ ጥረቶች የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሬ ግኝት ለማሳደግ አዲስ በር ከፍተዋል።
የሌማት ትሩፋት ኢትዮጵያ በምግብ ራስን ለመቻልና የዜጎቿን የአመጋገብ ሥርዓት ለማሻሻል የጀመረችው ስትራቴጂካዊ ጉዞ ዋና አካል ነው።
መርሐ ግብሩ ከመነሻው አንስቶ በምርት ዕድገት፣ በሥራ ዕድል ፈጠራና በሥራ ባህል ለውጥ ረገድ እጅግ ተስፋ ሰጪ ውጤቶችን አሳይቷል።
ይህ ንቅናቄ በተለይ የእንስሳት ተዋጽኦን በየጓሮውና በየቤቱ ተደራሽ በማድረግ በሕፃናት ላይ የሚታየውን የመቀንጨር ችግር ለመቅረፍ አስችሏል።
እንዲሁም አነስተኛ አምራቾችን የዕለት ገቢ ባለቤት በማድረግ የኢኮኖሚ አቅማቸውን እንዲገነቡ አድርጓል።
በአጠቃላይ የሌማት ትሩፋት ኢትዮጵያ በታሪክ አጋጣሚዎችና በተለያዩ ውጫዊና ውስጣዊ ምክንያቶች የሚገጥሟትን የምግብ ዋስትና ተግዳሮቶች በጽናት ለመቀልበስ መንግስት ተግባራዊ ካደረጋቸው ቁልፍ ስራዎች መካከል አንዱ ማሳያ ነው።
መርሐ ግብሩ የሀገሪቱን ነባር ችግሮች ወደ ታላቅ የኢኮኖሚ እድል በመቀየር ረገድ እጅግ የላቀ ድርሻ እያበረከተ የሚገኝ ሲሆን፣ ለዘላቂ ብልጽግና መሠረት የሚጥል ታላቅ ብሔራዊ ስኬትም ነው።
ሚዛን አማን፣ መስከረም 13/2019 (ኢዜአ)፡-በገጠር ዘመናዊ ህይወት መኖር ጀምረናል፤ የዚህ እድል ተጠቃሚ በመሆናችንም ተደስተና ሲሉ በካፋ ዞን የሺሾ እንዴ ...
Sep 24, 2026
ሆሳዕና ፤ ነሐሴ 21/2018 (ኢዜአ) ፦ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ...
Aug 28, 2026
መቱ፤ ነሐሴ 11/2018 (ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል በኢሉባቦር ዞን በክረምት እርሻ እየለማ ከሚገኘው የበቆሎ ሰብል የላቀ ምርት ለማገኘት የሰብል እንክብካቤና ጥ...
Aug 18, 2026
ሀዋሳ፤ ነሐሴ 2/2018 (ኢዜአ)፦ በሲዳማ ክልል የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማትን በማሻሻል ለሕዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ መሆና...
Aug 10, 2026