የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ፖለቲካ እና ደህንነት

የክልሉ ዲያስፖራ በልማትና ኢንቨስትመንት እያደረገ ያለውን የነቃ ተሳትፎ አጠናክሮ ይቀጥላል

Sep 30, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዳማ ፤ መስከረም 19/2019(ኢዜአ) ፦የኦሮሚያ ክልል ዲያስፖራ በልማትና በኢንቨስትመንት እያደረገ ያለውን የነቃ ተሳትፎ አጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ከተሞች ልማት ክላስተር ጽሕፈት ቤት ገለጸ።

የኦሮሚያ ዲያስፖራ የኢንቨስትመንት ፎረም በአዳማ ተካሄዷል።

የኦሮሚያ ከተሞች ልማት ክላስተር ጽሕፈት ቤት ሃላፊ አቶ ሙሉጌታ ገብረህይወት በወቅቱ፤ የክልሉ መንግሥት የተሳለጠ የኢንቨስትመንት ፍሰት ለማረጋገጥ አዳዲስ አሰራሮችና አደረጃጀቶችን እየዘረጋ ይገኛል ብለዋል።

በተለይም ለኢንቨስተሮች አመች ሁኔታዎችን ለመፍጠር አገልግሎትን ከማዘመንና ዲጂታል ከማድረግ ጀምሮ ዘርፈ ብዙ ተግባራት እያከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።

በከተሞች የኮሪደር ልማትን ጨምሮ ዘርፈ ብዙ የመሰረተ ልማት ዝርጋታዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ ያሉት አቶ ሙሉጌታ፤ ይህም ለውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትና በዘርፉ ለሚሰማሩ የዲያስፖራ አባላት ምቹ ሁኔታዎችን እንደሚፈጥር ጨምረው ገልጸዋል።


የክልሉ ዲያስፖራ በልማትና ኢንቨስትመንት እያደረገ ያለውን የነቃ ተሳትፎ ያደነቁት ሃላፊው፤ ይኸም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

የኦሮሚያ ዲያስፖራ ዳይሬክተር አቶ አሚን ጁንዲ በበኩላቸው ሀገሪቷ ከለውጡ ወዲህ እያስመዘገበች ያለው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማትና ዕድገት የሚደነቅ ነው ብለዋል።


እየተመዘገበ ያለው ሁለንተናዊ ልማትና ዕድገት አኩሪ የአፈፃፀም ተግባር የታየበት በመሆኑ ዲያስፖራው ይሄንን ተገንዝቦ ሀገሩን ለመለወጥ መዘጋጀቱን ገልጸዋል።

ባለፉት አምስት ዓመታት በክልሉ ከ90 ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ 2ሺህ 542 የዲያስፖራ አባላት መሬት ወስደው በኢንቨስትመንት መሰማራታቸውን ያስታወሱት ዳይሬክተሩ፤ በዚህም ከ185ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ ዕድል መፍጠራቸውን ተናግረዋል።

የአዳማ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽሕፈት ቤት ሃላፊ አቶ በሪሶ ዶሪ እንደገለፁት አዳማ በፈጣን ልማትና ዕድገት ላይ ትገኛለች።

በተለይም ከተማዋ በቀጣይ 15 ዓመታት የምትመራበት ዘመናዊ የልማት ፕላን ተዘጋጅቶ ወደ ተግባር መግባቱን ገልጸው፤ በዚህም ከ10ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ለማኑፋክቸሪንግ፣ ለቱሪዝምና ቴክኖሎጂ ኢንቨስትመንት በማዘጋጀት ባለሃብቶችን ለመቀበል በዝግጅት ላይ መሆኗን ተናግረዋል።

ዲያስፖራውም አስተዳደሩ የፈጠረውን ምቹ አጋጣሚ በመጠቀም ወደ ኢንቨስትመንት በመግባት የእድሉ ተጠቃሚ መሆን እንደሚገባው አመላክተዋል ።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በገጠር ዘመናዊ ህይወት መኖር ጀምረናል፤ የዚህ እድል ተጠቃሚ በመሆናችንም ተደስተናል- አርሶ አደሮች

ሚዛን አማን፣ መስከረም 13/2019 (ኢዜአ)፡-በገጠር ዘመናዊ ህይወት መኖር ጀምረናል፤ የዚህ እድል ተጠቃሚ በመሆናችንም ተደስተና ሲሉ በካፋ ዞን የሺሾ እንዴ ...

Sep 24, 2026

በክልሉ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የተጀመሩ ስራዎችን ማጠናከር ይጠበቅባቸዋል- ርእሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)

ሆሳዕና ፤ ነሐሴ 21/2018 (ኢዜአ) ፦ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ...

Aug 28, 2026

በኢሉባቦር ዞን በኩታ ገጠም ከለማው የበቆሎ ሰብል የተሻለ ምርት ለማገኘት የእንክብካቤ ስራ ተጠናክሯል

መቱ፤ ነሐሴ 11/2018 (ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል በኢሉባቦር ዞን በክረምት እርሻ እየለማ ከሚገኘው የበቆሎ ሰብል የላቀ ምርት ለማገኘት የሰብል እንክብካቤና ጥ...

Aug 18, 2026

በሲዳማ ክልል የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማትን በማሻሻል ለሕዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ ናቸው

ሀዋሳ፤ ነሐሴ 2/2018 (ኢዜአ)፦ በሲዳማ ክልል የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማትን በማሻሻል ለሕዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ መሆና...

Aug 10, 2026