የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ፖለቲካ እና ደህንነት

በተወሰዱ ተግባራዊ እርምጃዎች የኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅም ከ69 በመቶ በላይ አድጓል

Oct 4, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ ፤መስከረም 23/2019 (ኢዜአ)፦የኢንዱስትሪዎችን የማምረት አቅም ለማሳደግ በተወሰዱ ተግባራዊ እርምጃዎች የማምረት አቅማቸው ከ69 በመቶ በላይ ማደጉን የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ ሀሰን መሐመድ ገለጹ።

ኢትዮጵያን የአፍሪካ የአምራች ኢንዱስትሪ ማዕከል ለማድረግ ዘርፉን በተኪ ምርት፣ በምርታማነት፣ በጥራትና በቴክኖሎጂ ሽግግር ለማጠናከር እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብ፣ ታላቅ ርዕይ በመሰነቅ የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተጋች ትገኛለች።

በዚህም ባለፉት ዓመታት ተግባራዊ በተደረጉ የኢንዱስትሪ ፖሊሲ እና የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያዎች ዘርፉን በማነቃቃት በርካታ ውጤቶች ተገኝተዋል።

የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ ሀሰን መሐመድ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለጹት፤ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄና የብሔራዊ አምራች ካውንስል የኢንዱስትሪዎችን ማነቆዎች በመፍታት የአምራች ዘርፉን ተግባራዊ አቅም እያሳደጉ ይገኛሉ።

በተለይም ከዚህ በፊት ተዘግተው የነበሩ ፋብሪካዎችን ወደ ሥራ ለመመለስ የኤሌክትሪክ፣ የውሃ፣ የካፒታልና የግብዓት እጥረት ጨምሮ የተለያዩ ችግሮች እየተፈቱ መሆኑን አስረድተዋል።

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በክልሎችና በከተማ አስተዳደሮች ካሉ መዋቅሮች ጋር በመቀናጀት እየሰራ መሆኑንም አመልክተዋል።

ባለፈው ዓመት ከውጭ ይገቡ የነበሩ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በመተካት 5 ነጥብ 9 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ የውጭ ምንዛሬ ማዳን መቻሉን ገልጸው፣በጨርቃ ጨርቅና አልባሳት፣ በምግብና መጠጥ፣ በብረታ ብረትና በቆዳ ዘርፎች የተኪ ምርት እየተስፋፋ መምጣቱን ጠቁመዋል።

የተኪ ምርት መስፋፋት የውጭ ምንዛሬ ወጪን ከመቀነስ ባለፈ የንግድ ሚዛንን ለማሻሻል፣ የሥራ ዕድል ለመፍጠርና የአምራች ዘርፉን በኢኮኖሚው ውስጥ ያለውን ድርሻ ለማሳደግ እንደሚያግዝ ገልጸዋል።

በዚህም የኢንዱስትሪዎችን የማምረት አቅም ለማሳደግ በተወሰዱ ተግባራዊ እርምጃዎች የማምረት አቅማቸው ወደ 69 ነጥብ 2 በመቶ ማደጉን ተናግረዋል።

የኢንዱስትሪ ዘርፉ የምርት ጥራትንና ምርታማነትን ማሳደግ፣ የዋጋ ጨማሪን ማስፋፋት፣ ከግብርና ጋር ያለውን የኋልዮሽና የፊት ለፊት ትስስር ማጠናከር እንዲሁም የቴክኖሎጂ ሽግግርን ማፋጠን ላይ በትኩረት እየሰራ መሆኑንም አስረድተዋል።

ኢትዮጵያ የአምራች ማዕከል በመሆን የአፍሪካ ሀገራትን በአምራች ዘርፍ ለማሰልጠንና የካይዘን ፍልስፍናን በአህጉሩ ለማስፋፋት እየሰራች መሆኗንም ገልጸዋል።

የኢንዱስትሪ ዘርፉ የሥራ ዕድል ፈጠራን፣ ኢንቨስትመንትንና የወጪ ንግድን በማሳደግ በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ያለውን ድርሻ እንዲያሳድግ በቀጣይ የተለያዩ ዕቅዶች መያዛቸውን ገልጸዋል።

በዚህ መሠረት በ10 ዓመቱ የመሪ ልማት ዕቅድ የኢንዱስትሪ ዘርፉን የወጪ ንግድ 9 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ፣ የሥራ ዕድል ፈጠራን ወደ 5 ሚሊዮን ለማሳደግና የዘርፉን በኢኮኖሚው ያለውን ድርሻ 17 ነጥብ 2 በመቶ ለማድረስ ዕቅድ መያዙን አስታውቀዋል።

የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሙ ከኢንዱስትሪው በፊት የነበሩ የውጭ ምንዛሬ እጥረትን ጨምሮ ማነቆዎችን ለመፍታት ዕድል መፍጠሩን ገልጸዋል።

በተለይም የመለዋወጫ ዕቃዎችን፣ ማሽኖችንና ቴክኖሎጂዎችን ከውጭ ለማስመጣት የነበሩ የውጭ ምንዛሬ ችግሮች መቀነሳቸውን ጠቅሰው፣ የተሻሻሉ ሕጎች፣ ደንቦችና መመሪያዎችም ለአምራች ዘርፉ ምቹ ሁኔታ እየፈጠሩ መሆኑን አስረድተዋል።

የአምራች ዘርፉ የውጭ ገበያን በመያዝ የውጭ ምንዛሬ ለማስገኘትም አቅሙን እያሳደገ መምጣቱን ጠቅሰዋል።

የኢንዱስትሪ ልማት የአንድ ተቋም ብቻ ሥራ ባለመሆኑ ክልሎች፣ ከተማ አስተዳደሮችና የተለያዩ የፌዴራል ተቋማት በቅንጅት መሥራታቸውን ማጠናከር እንደሚገባም አመልክተዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በገጠር ዘመናዊ ህይወት መኖር ጀምረናል፤ የዚህ እድል ተጠቃሚ በመሆናችንም ተደስተናል- አርሶ አደሮች

ሚዛን አማን፣ መስከረም 13/2019 (ኢዜአ)፡-በገጠር ዘመናዊ ህይወት መኖር ጀምረናል፤ የዚህ እድል ተጠቃሚ በመሆናችንም ተደስተና ሲሉ በካፋ ዞን የሺሾ እንዴ ...

Sep 24, 2026

በክልሉ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የተጀመሩ ስራዎችን ማጠናከር ይጠበቅባቸዋል- ርእሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)

ሆሳዕና ፤ ነሐሴ 21/2018 (ኢዜአ) ፦ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ...

Aug 28, 2026

በኢሉባቦር ዞን በኩታ ገጠም ከለማው የበቆሎ ሰብል የተሻለ ምርት ለማገኘት የእንክብካቤ ስራ ተጠናክሯል

መቱ፤ ነሐሴ 11/2018 (ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል በኢሉባቦር ዞን በክረምት እርሻ እየለማ ከሚገኘው የበቆሎ ሰብል የላቀ ምርት ለማገኘት የሰብል እንክብካቤና ጥ...

Aug 18, 2026

በሲዳማ ክልል የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማትን በማሻሻል ለሕዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ ናቸው

ሀዋሳ፤ ነሐሴ 2/2018 (ኢዜአ)፦ በሲዳማ ክልል የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማትን በማሻሻል ለሕዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ መሆና...

Aug 10, 2026