የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ፖለቲካ እና ደህንነት

የወለጋ ዩኒቨርሲቲ ከምርምር ማዕከላት ጋር በመቀናጀት የአርሶ አደሩን ምርታማነት እያሳደገ ነው

Oct 9, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ነቀምቴ፤ መስከረም 28/2019 (ኢዜአ)፡- ወለጋ ዩኒቨርሲቲ ከምርምር ማዕከላት ጋር ተቀናጅቶ በመስራት የአርሶ አደሩን ምርታማነት እያሳደገ መሆኑን አስታወቀ።

የዩኒቨርሲቲው የምርምርና ሥርፀት ኦፊሰር ተመራማሪ ጋዲሳ ተሾመ ከመማር ማስተማር በተጓዳኝ ከባኮ ብሔራዊ የበቆሎ ምርምር ማዕከል ጋር በመተባበር BH-520 የተሰኘ የተሻሻለ የበቆሎ ዝርያን በማባዛት የአርሶ አደሩን ምርታማነት እያሳደገ ነው።

ይህም የአርሶ አደሩን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት ከማገዝ ባለፈ ኢኮኖሚያዊ አቅሙን እያጠናከረ መምጣቱን ተናግረዋል።

ዩኒቨርሲቲው የግብርና ምርታማነትን ለማሳደግ የተሻሻሉ የሰብል ዝርያዎችን በማባዛት ለ300 የአርሶ አደር ማሰራጨቱንም ተመራማሪው ገልጸዋል።

የከተማ ግብርናን ለማስፋፋት የሚያግዙ የአትክልት ዘር ማቅረብና ተጠቃሚዎችም ውጤታማ እንዲሆኑ ሙያዊ ድጋፍ ማድረጉን አንስተዋል።

በቀጣይም የግብርናን ውጤታማነት በማሳደግ አርሶ አደሮችን ይበልጥ ተጠቃሚ ለማድረግ የጀመረውን የሥልጠናና የቴክኖሎጂ ድጋፍ እንደሚያጠናክር ገልፀዋል።

ከወለጋ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመቀናጀት ለአርሶ አደሩ የሚያቀርቡት የግብርና ቴክኖሎጂ የአርሶ አደሮችን ምርታማነትን ማሳደጉን የገለጹት ደግሞ የዋዩ ቱቃ ወረዳ ግብርና ባለሙያ አቶ ሚልኬሳ ነመራ ናቸው።

ይህም የአርሶ አደሩን የተሻሻሉ የሰብል ዝርያዎችንና የግብርና ቴክኖሎጂዎችን የመጠቀም ባህል እያዳበረው መምጣቱን ገልጸዋል።

ዩኒቨርሲቲው የሚያቀርበው የተሻሻሉ የሰብል ዝርያዎች ከአካባቢው የአየርና የአፈር ሁኔታ ጋር የሚስማሙ መሆናቸው ለምርታማነት ማሳደግ ከፍተኛ ድርሻ ማበርከታቸውን አስረድተዋል።

የዋዩ ቱቃ ወረ ባቦ ቀበሌ አርሶ አደር አቶ መልካሙ ሀነቢሳ በበኩላቸው እንደገለጹት፣ ከዩኒቨርሲቲው ያገኙትን የተሻሻለ የበቆሎ ዘር ተጠቅመው ምርታማነታቸውን ማሳደጋቸውን ተናግረዋል።

በዚህም የቤተሰባቸውን የምግብ ፍላጎት ከማሟላት ባለፈ ተጨማሪ ገቢ ለማግኘት እንዳገዛቸው ገልጸዋል።

ዩኒቨርሲቲው ያቀረበላቸው የተሻሻለ የሰብል ዝርያና የግብርና ቴክኖሎጂ ድጋፍ ምርታማነታቸውን ለማሳደግ እንዳገዛቸው የጠቆሙት ደግሞ ሌላው ተጠቃሚ አርሶ አደር ጀቤሳ ቱፍ ናቸው።

ዩኒቨርሲቲው ውጤታማ እንዲሆኑ ያበረከተላቸው አስተዋጽኦ በኑሮዋቸው ላይ ተጨባጭ ለውጥ በማምጣቱ ተሞክሯቸውን ለሌሎች አርሶ አደሮች እያካፈሉ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በገጠር ዘመናዊ ህይወት መኖር ጀምረናል፤ የዚህ እድል ተጠቃሚ በመሆናችንም ተደስተናል- አርሶ አደሮች

ሚዛን አማን፣ መስከረም 13/2019 (ኢዜአ)፡-በገጠር ዘመናዊ ህይወት መኖር ጀምረናል፤ የዚህ እድል ተጠቃሚ በመሆናችንም ተደስተና ሲሉ በካፋ ዞን የሺሾ እንዴ ...

Sep 24, 2026

በክልሉ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የተጀመሩ ስራዎችን ማጠናከር ይጠበቅባቸዋል- ርእሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)

ሆሳዕና ፤ ነሐሴ 21/2018 (ኢዜአ) ፦ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ...

Aug 28, 2026

በኢሉባቦር ዞን በኩታ ገጠም ከለማው የበቆሎ ሰብል የተሻለ ምርት ለማገኘት የእንክብካቤ ስራ ተጠናክሯል

መቱ፤ ነሐሴ 11/2018 (ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል በኢሉባቦር ዞን በክረምት እርሻ እየለማ ከሚገኘው የበቆሎ ሰብል የላቀ ምርት ለማገኘት የሰብል እንክብካቤና ጥ...

Aug 18, 2026

በሲዳማ ክልል የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማትን በማሻሻል ለሕዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ ናቸው

ሀዋሳ፤ ነሐሴ 2/2018 (ኢዜአ)፦ በሲዳማ ክልል የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማትን በማሻሻል ለሕዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ መሆና...

Aug 10, 2026