🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ጥቅምት 2/2019(ኢዜአ)፦የዲጂታል ምኅዳራችንን ከሳይበር ሥጋቶች መጠበቅ የሀገራችንን የዲጂታል ሉዓላዊነት፣ የዜጎችን ደኅንነትና የልማት ጉዟችንን የማስጠበቅ ጉዳይ ነው።
የሳይበር ደኅንነት የሀገር ደኅንነት ነው።
ዛሬ የ7ኛውን ሀገር አቀፍ የሳይበር ደኅንነት ወር “ንቁ ዜጋ፤ ደኅንነቱ ለተጠበቀ ሀገር!” በሚል መሪ ሐሳብ በይፋ አስጀምረናል።

በዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ያሳካናቸው የኢንተርኔት ተጠቃሚነት መስፋፋት፣ የቴሌኮም ዘርፉ ለውድድር መከፈት፣ የዲጂታል ክፍያ ሥርዓቶች መስፋፋትና የመንግሥት አገልግሎቶችን በዲጂታል መንገድ የማቅረብ ርምጃዎች ለዲጂታል ሽግግር መሠረት ጥለዋል።
ይህንን ወደ ቀጣይ ምዕራፍ በማሸጋገር፣ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ራዕያችንን እውን ለማድረግና የቴክኖሎጂ ዕድገት የሀገራዊ ብልጽግናችን ወሳኝ ዐቅም እንዲሆን በሁሉም መስክ እየተሠራ ነው።
የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር የሀገራችንን የሳይበር ምኅዳር ሙሉ በሙሉ አስተማማኝ በማድረግ፣ ለሀገራዊ ልማት፣ ለዲጂታል 2030 ስትራቴጂ ስኬት እና ለላቀ ሀገራዊ ብልጽግና የሚያደርገውን የ24/7 ጥረት ዕውቅና መስጠት ያስፈልጋል።

የዲጂታል ምኅዳራችንን ከሳይበር ሥጋቶች መጠበቅ የሀገራችንን የዲጂታል ሉዓላዊነት፣ የዜጎችን ደኅንነትና የልማት ጉዟችንን የማስጠበቅ ጉዳይ ነው።
የዲጂታል ምኅዳራችንን የሚጠብቅ፣ የሀገራችንን ደኅንነት የሚያጠናክርና የዲጂታል ወደፊት ጉዟችንን የሚያረጋግጥ ንቁና ኃላፊነት የሚሰማው ዜጋ መገንባት ከሁላችንም ይጠበቃል።
ዲላ፤ መስከረም 29/2019 (ኢዜአ) ፦ኢትዮጵያ በሰጥቶ መቀበል መርህ የባህር በር ባለቤት ለመሆን እያደረገች ያለው ጥረት ለቀጠናው ሰላምና መረጋጋት ያላትን ቁ...
Oct 10, 2026
ሚዛን አማን፣ መስከረም 13/2019 (ኢዜአ)፡-በገጠር ዘመናዊ ህይወት መኖር ጀምረናል፤ የዚህ እድል ተጠቃሚ በመሆናችንም ተደስተና ሲሉ በካፋ ዞን የሺሾ እንዴ ...
Sep 24, 2026
ሆሳዕና ፤ ነሐሴ 21/2018 (ኢዜአ) ፦ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ...
Aug 28, 2026
መቱ፤ ነሐሴ 11/2018 (ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል በኢሉባቦር ዞን በክረምት እርሻ እየለማ ከሚገኘው የበቆሎ ሰብል የላቀ ምርት ለማገኘት የሰብል እንክብካቤና ጥ...
Aug 18, 2026