የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ፖለቲካ እና ደህንነት

በሲዳማ ክልል የዘንድሮው የበጋ መስኖ ልማት የሥራ ዕድል ፈጠራን እና ገበያን ለማረጋጋት ባለመ መልኩ ይከናወናል

Oct 13, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ሀዋሳ፣ ጥቅምት 2/2019 (ኢዜአ)፡- በሲዳማ ክልል የዘንድሮው የበጋ መስኖ ልማት የሥራ ዕድል ፈጠራን እና ገበያን ለማረጋጋት ባለመ መልኩ እንደሚከናወን የክልሉ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ መምሩ ሞኬ ገለፁ።

የሲዳማ ክልል እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ የ2019 የበጋ መስኖ ልማት ንቅናቄ መድረክ በሐዋሳ ከተማ አካሂዷል።


በተያዘው የበጋ መስኖ ሥራ 106 ሺህ ሄክታር መሬት በመስኖ የማልማት ሥራ መጀመሩን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ገልጸዋል።

በሥነ ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የሲዳማ ክልል የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ መምሩ ሞኬ እንዳሉት፤ በክልሉ የዘንድሮው የበጋ መስኖ ልማት ሥራ የዕድል ፈጠራን እና ገበያን ለማረጋጋት ባለመ መልኩ ይከናወናል።

በዚህም ክልሉ የተለያዩ የውኃ አማራጮችን በመጠቀም በወልና በመንግሥት ይዞታ ሥር በሚገኙ ማሳዎች ላይ ከ4 ሺህ የሚበልጡ ሥራ አጦችን በማደራጀት በበጋ መስኖ ልማት እንዲሰማሩ የማድረግ ሥራ ልዩ ትኩረት እንደተሰጠው ተናግረዋል።

በያዝነው የበጋ ወቅት አንድም መሬት ከልማት ውጭ እንዳይሆን ለማድረግ በየደረጃው ያሉ አመራሮች በትኩረት መሥራት እንዳለባቸው የክልሉ የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ መምሩ አሳስበዋል።

አርሶ አደሩ ግብዓትን በአግባቡ ተጠቅሞ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ እንዲችል የግብርና ባለሙያዎችና አመራሩ ክትትልና ድጋፋቸውን ማጠናከር እንዳለባቸውም ገልጸዋል።


የሲዳማ ክልል እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ አስፋው ጎኔሶ በበኩላቸው፤ በተያዘው የበጋ መስኖ ሥራ 106 ሺህ ሄክታር መሬት በጓሮ አትክልት፣ በአዝርዕትና በፍራፍሬ እንደሚለማ ተናግረዋል።

ለመስኖ ሥራ ምቹ በሆኑ የክልሉ ሁሉም አካባቢዎች በገበያ ተፈላጊ የሆኑ ምርቶች እንደ ቲማቲም፣ ጥቅል ጎመን፣ ሽንኩርት፣ ካሮትና ሌሎች የጓሮ አትክልቶች እንዲሁም ቦሎቄና ፍራፍሬ ለማልማት ታስቦ ሥራ መጀመሩን ገልጸዋል።

በዚህም በልማቱ ከ200 ሺህ በላይ አርሶ አደሮች እንዲሳተፉ በማድረግ ከ24 ሚሊዮን ኩንታል የሚበልጥ ምርት ለመሰብሰብ መታቀዱን ጠቁመዋል።


የሰሜናዊ ሲዳማ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የገጠር ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ዱሬሳ ሌዳሞ እንዳሉት፤ በዞኑ ስድስት ወረዳዎች 42 ሺህ ሄክታር መሬት በማልማት 11 ነጥብ 2 ሚሊዮን ኩንታል ለማምረት ታቅዶ ሥራ ተጀምሯል።

በዞኑ አምና 32 ሺህ ሄክታር መሬት በማልማት ከ8 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት እንደተገኘ አስታውሰው፣ በዘንድሮው የበጋ መስኖ አምና በበልግ ዝናብ እጥረት ምክንያት ያጋጠመውን የምርት መቀነስ ለማካካስ እንደሚሠራ ገልጸዋል።


የደቡባዊ ሲዳማ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የግብርናና ገጠር ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ደበበ ሻሌ በበኩላቸው፤ በዞኑ 22 ሺህ 360 ሄክታር መሬት በበጋ መስኖ በማልማት 4 ነጥብ 5 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ መታቀዱን ተናግረዋል።

በንቅናቄ መድረኩ ላይ የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት፣ የዞንና የወረዳ አመራሮች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

ኢትዮጵያ በሰጥቶ መቀበል መርህ የባህር በር ባለቤት ለመሆን የምታደርገው ጥረት ለቀጣናው ሰላም ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው

ዲላ፤ መስከረም 29/2019 (ኢዜአ) ፦ኢትዮጵያ በሰጥቶ መቀበል መርህ የባህር በር ባለቤት ለመሆን እያደረገች ያለው ጥረት ለቀጠናው ሰላምና መረጋጋት ያላትን ቁ...

Oct 10, 2026

በገጠር ዘመናዊ ህይወት መኖር ጀምረናል፤ የዚህ እድል ተጠቃሚ በመሆናችንም ተደስተናል- አርሶ አደሮች

ሚዛን አማን፣ መስከረም 13/2019 (ኢዜአ)፡-በገጠር ዘመናዊ ህይወት መኖር ጀምረናል፤ የዚህ እድል ተጠቃሚ በመሆናችንም ተደስተና ሲሉ በካፋ ዞን የሺሾ እንዴ ...

Sep 24, 2026

በክልሉ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የተጀመሩ ስራዎችን ማጠናከር ይጠበቅባቸዋል- ርእሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)

ሆሳዕና ፤ ነሐሴ 21/2018 (ኢዜአ) ፦ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ...

Aug 28, 2026

በኢሉባቦር ዞን በኩታ ገጠም ከለማው የበቆሎ ሰብል የተሻለ ምርት ለማገኘት የእንክብካቤ ስራ ተጠናክሯል

መቱ፤ ነሐሴ 11/2018 (ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል በኢሉባቦር ዞን በክረምት እርሻ እየለማ ከሚገኘው የበቆሎ ሰብል የላቀ ምርት ለማገኘት የሰብል እንክብካቤና ጥ...

Aug 18, 2026