🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3 /2019 (ኢዜአ)፦ በ2019 ዓ.ም በጀት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የከተማዋን ነዋሪዎች ተጠቃሚ ያደረጉና ለቀጣይ ሥራዎች መሠረት የጣሉ ውጤታማ ተግባራት መከናወናቸውን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።
ከንቲባዋ በመልዕክታቸው፣ በሩብ ዓመቱ በትራንስፖርትና መሠረተ ልማት ዘርፍ አራት ትላልቅ የመኪና ማቆሚያና ተርሚናል ማዕከላት ተገንብተው አገልግሎት መስጠት የጀመሩ ሲሆን፣ አዳዲስ የመኪና መንገዶች፣ የእግረኛና የብስክሌት መንገዶችም መገንባታቸውን አመልክተዋል።

ከዚህ በተጨማሪም የውሃ ማስወገጃና የፍሳሽ መስመሮች ግንባታ የተካሄደ ሲሆን፣ የጎርፍ አደጋ መከላከያ ሥራዎች መከናወናቸውን ተናግረዋል።
በከተማዋ የሥራ ዕድል ፈጠራንና የዜጎችን የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል በተከናወኑ ተግባራት ለ68 ሺህ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር መቻሉን ጠቁመዋል።
የኑሮ ውድነት ጫናን ለመቀነስ ደግሞ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ነዋሪዎች ያማከለ የማዕድ ማጋራት ሥራዎች የተከናወኑ ሲሆን፣ በሰባት የገበያ ማዕከላት በኩል ሰፊ የምርት አቅርቦት ወደ ከተማዋ እንዲገባ መደረጉን ነው የገለጹት።
በተመሳሳይ መልኩ የቅዳሜና እሁድ ገበያዎችን ደረጃ የማሳደግ ሥራ መከናወኑንም ከንቲባዋ አመልክተዋል።

በቤት ልማት ዘርፍ የቤቶች ግንባታ ሥራዎች የተከናወኑ ሲሆን፣ የቤት ችግር ያለባቸው ነዋሪዎችና የልማት ተነሺዎች ንጹህ እንዲሁም የዜጎችን ክብር የሚጠብቁ ቤቶች እንዲያገኙ ተደርጓል።
የማህበራዊ ዘርፍ ልማትን በተመለከተም 38 የትምህርት ፕሮጀክቶች ተገንብተው ወደ ሥራ የገቡ ሲሆን፣ በጤናው ዘርፍም ዘመናዊ አገልግሎት መስጠት መቻሉን ከንቲባዋ ጠቁመዋል።
የአገልግሎት አሰጣጥን ለማዘመንና ከተማዋን ለነዋሪዎች ምቹ ለማድረግ በተከናወኑ ተግባራት 23 አገልግሎቶች ወደ መሶብ የአንድ ማዕከል ዲጂታል መንግሥት አገልግሎት እንዲገቡ መደረጉን አመልክተዋል።
ከተማዋን ለህፃናት ምቹ ለማድረግ በተከናወነው ሥራ ደግሞ የመጫወቻዎችን ቁጥር ከ6,070 በላይ፣ የህፃናት ማቆያዎችን ደግሞ 1,200 ማድረስ መቻሉንም ነው ያመለከቱት።
የአረንጓዴ ዐሻራ ሥራዎችም በስፋት መከናወናቸውን አንስተዋል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በሩብ ዓመቱ በቱሪዝም፣ በሰላምና ፀጥታ፣ በመብራት መሠረተ ልማት እንዲሁም በጽዳት ዘርፎች ከፍተኛ ውጤት መመዝገቡን በመልዕክታቸው ላይ አስፍረዋል።
ዲላ፤ መስከረም 29/2019 (ኢዜአ) ፦ኢትዮጵያ በሰጥቶ መቀበል መርህ የባህር በር ባለቤት ለመሆን እያደረገች ያለው ጥረት ለቀጠናው ሰላምና መረጋጋት ያላትን ቁ...
Oct 10, 2026
ሚዛን አማን፣ መስከረም 13/2019 (ኢዜአ)፡-በገጠር ዘመናዊ ህይወት መኖር ጀምረናል፤ የዚህ እድል ተጠቃሚ በመሆናችንም ተደስተና ሲሉ በካፋ ዞን የሺሾ እንዴ ...
Sep 24, 2026
ሆሳዕና ፤ ነሐሴ 21/2018 (ኢዜአ) ፦ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ...
Aug 28, 2026
መቱ፤ ነሐሴ 11/2018 (ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል በኢሉባቦር ዞን በክረምት እርሻ እየለማ ከሚገኘው የበቆሎ ሰብል የላቀ ምርት ለማገኘት የሰብል እንክብካቤና ጥ...
Aug 18, 2026