🔇Unmute
ጥቅምት 5/2019 (ኢዜአ)፦የዓለም የድህነት ቅነሳ እድሎችና ፈተናዎች
የድህነት መገለጫ የገንዘብ እጥረት ብቻ ሳይሆን የምግብ፣ የመጠለያ፣ የጤና፣ የትምህርት፣ የንጹሕ ውሃና የሥራ ዕድል እጥረትን የሚያካትት የሰው ልጆች ልማት እንቅፋት ነው። ድህነት የሰዎችን የኑሮ ደረጃ ከማውረድ ባለፈ፣ በማኅበራዊ ፍትሕ፣ በእኩል ዕድል፣ በሰላምና በዘላቂ ልማት ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ያሳድራል።
በየዓመቱ በአውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ጥቅምት 17 የሚከበረው ዓለም አቀፍ የድህነት ቅነሳ ቀን፣ ድህነትን ለመዋጋት የተጠናከረ የጋራ ጥረት እንዲደረግ፣ የድህነት ተጎጂዎች ድምፅ እንዲሰማና የሰው ልጆች ሁሉ በክብር የሚኖርበት ዓለም እንዲገነባ በማሰብ ነው።
የድህነት ቅነሳም ከሰው ልጆች መብት፣ ክብርና ከሰላም ጋር በቀጥታ የሚያያዝ መሆኑን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በግልጽ ያስቀመጠ በመሆኑ እ.ኤ.አ ከ2026 እስከ 2028 “ደህንነቱ የተጠበቀ መኖሪያ ቤት ለሁሉም” በሚል መርህ ለሰብአዊነትና ለሰላም በጋራ እንቁም በማለት እየተሰራ ይገኛል።
እለቱን ከመኖሪያ ቤት ጋር በማገናኘት ለማክበር የተፈለገውም አሁን በዓለም ላይ ከ2 ነጥብ 8 ቢሊዮን በላይ ሰዎች የተሟላ የመኖሪያ ቤት የሌላቸውና በድህነት ውስጥ የሚኖሩ በመሆኑ በተለይም ለጤና፣ ለትምህርት፣ ለስራ እና ለማህበራዊ ተሳትፎ እንከን የዳረጋቸው መሆኑ በመረጋገጡ ነው።
በዓለም ላይ ድህነትን ለመቀነስ የተደረጉ ጥረቶች ውጤት ያስገኙ ቢሆንም፣ አሁንም በርካቶች መሠረታዊ ፍላጎቶቻቸውን ለማሟላት ተቸግረው በድህነት ውስጥ መሆናቸው ተጨማሪ ተግባራትን ማከናወን እንደሚገባ ይታመናል።
በተለያዩ አገራት የጦርነትና ግጭት መስፋፋት፣ የኑሮ ውድነት፣ የሥራ አጥነት፣ የአየር ንብረት ለውጥ፣ የተፈጥሮ አደጋዎችና የሀብት ክፍፍል ኢ-ፍትሐዊነት ድህነትን ለመቀነስ የሚደረገውን ጥረት እየፈተኑት ይገኛሉ። በመሆኑም የድህነት ቅነሳ የአንድ መንግሥት ወይም የአንድ ሀገር ብቻ ኃላፊነት ሳይሆን የዓለም አቀፍ ትብብር፣ የፍትሐዊ የሀብት አጠቃቀምና የጋራ ቁርጠኝነት መሆን ይኖርበታል።
በአፍሪካ ድህነትን ለመቀነስ የሚያስችሉ ሰፊ እድሎች ቢኖሩም በተለያዩ ፈተናዎች እስካሁንም የሚፈለገውን ማሳካት አልተቻለም። አፍሪካ ሰፊ መሬት፣ እምቅ የተፈጥሮ ሀብት፣ በርካታ የወጣት ሃይል ያላት ብትሆንም ከችግርና ድህነት መላቀቅ አቅቷታል። በተለይም ከሰሃራ በታች ባሉት የአፍሪካ አገራት ከፍተኛ ድህነት መኖሩን መረጃዎች ይጠቁማሉ። የግጭትና የፖለቲካ አለመረጋጋት፣ የግብርና ምርታማነት መቀነስ፣ የዘመናዊ ቴክኖሎጂና የፋይናንስ አገልግሎት እጥረት፣ የመሠረተ ልማት ውስንነት፣ የአየር ንብረት ለውጥና የውጭ ዕዳ ጫና ለችግሩ መባባስ አስተዋጽኦ እያደረጉ ይገኛሉ።
በመሆኑም በአፍሪካ ያለውን እምቅ የተፈጥሮ ሀብት በአግባቡ በማልማትና ጥቅም ላይ በማዋል ምርታማነትን በማሳደግ ለልማት በመንቀሳቀስ ድህነትን መቀነስ ይገባል። የአህጉራዊ ንግድን ማስፋፋት፣ ኢንቨስትመንትን ማጠናከር፣ ለወጣቶች የስራ እድልን ማመቻቸት ብሎም አሀጉራዊ ሰላምና መረጋጋትን በማፅናት ከድህነት መውጣት እንደሚገባ ይመከራል።
በዚህ ረገድ በኢትዮጵያ እየተከናወኑ የሚገኙ የድህነት ቅነሳ መርሃ ግብሮች የላቀ ስኬት እየተመዘገበባቸው መሆኑን መመልከት ይቻላል። የቡና ልማት፣ የአረንጓዴ አሻራ፣ የሌማት ትሩፋት፣ የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት፣ የአትክልትና ፍራፍሬ ልማት እንዲሁም ሌሎች የግብርና ልማት ስራዎች እመርታዊ ውጤት አምጥተዋል። ከግብርና ልማት ባሻገርም በኢንዱስትሪ፣ በአገልግሎት ዘርፍና በመሠረተ ልማትና ኢንቨስትመንት ተመሳሳይ ውጤት የመጣባቸው ናቸው። በተለይም የመስኖ ልማት በዝናብ ላይ ያለውን ጥገኝነት በመቀነስ፣ በዓመት ከአንድ ጊዜ በላይ ምርት ለማምረትና የአርሶ አደሮችን የገቢ ምንጭ ለማሳደግ አስችሏል።
የዘንድሮው ዓለም አቀፍ የድህነት ቅነሳ ቀን የፊታችን ቅዳሜ ጥቅምት 7 ቀን 2019 ዓ.ም በተለያዩ ዝግጅቶች በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚከበር መሆኑ ታውቋል።
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 5/2019 (ኢዜአ)፦የመደመር መንግሥት ዋና ዓላማ ያሉትን ሀብቶች አውቆና አበልጽጎ ለተከታዩ ትውልድ የሚተርፍ ወረት መፍጠር መሆኑን የኢፌ...
Oct 16, 2026
ዲላ፤ መስከረም 29/2019 (ኢዜአ) ፦ኢትዮጵያ በሰጥቶ መቀበል መርህ የባህር በር ባለቤት ለመሆን እያደረገች ያለው ጥረት ለቀጠናው ሰላምና መረጋጋት ያላትን ቁ...
Oct 10, 2026
ሚዛን አማን፣ መስከረም 13/2019 (ኢዜአ)፡-በገጠር ዘመናዊ ህይወት መኖር ጀምረናል፤ የዚህ እድል ተጠቃሚ በመሆናችንም ተደስተና ሲሉ በካፋ ዞን የሺሾ እንዴ ...
Sep 24, 2026
ሆሳዕና ፤ ነሐሴ 21/2018 (ኢዜአ) ፦ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ...
Aug 28, 2026