የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ፖለቲካ እና ደህንነት

የኢትዮጵያ የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር የዓሳ ሃብት እምቅ አቅምን ወደ ተጨባጭ ውጤት ቀይሯል

Oct 23, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ ፤ ጥቅምት 12/2019 (ኢዜአ) ፦የኢትዮጵያ የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር የዓሳ ሃብት እምቅ አቅምን ወደ ተጨባጭ ውጤት መቀየሩን በግብርና ሚኒስቴር የዓሳ ሀብት ልማት ዴስክ ኃላፊ ዶክተር ፋሲል ዳዊት ገለጹ።

ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብና ታላቅ ርዕይ

በአፍሪካ ኅብረት የግብርና፣ ገጠር ልማት፣ ብሉ ኢኮኖሚና ዘላቂ ከባቢ አየር ኮሚሽን ሥር የሚገኘው የአፍሪካ ኅብረት የእንስሳት ሀብት ጉዳዮች ቢሮ የዓሣ ሀብት አስተዳደር ፕሮጀክት ሁለተኛ ምዕራፍ (FishGov2) የማጠቃለያ ስብሰባ ተካሂዷል።


በመድረኩ የተገኙት በግብርና ሚኒስቴር የዓሣ ሀብት ልማት ዴስክ ኃላፊ ዶክተር ፋሲል ዳዊት፤ በኢትዮጵያ ለዓሣ ሀብትና የውኃ አካላት ልማት የተሰጠው ትኩረት ምርታማነትን እያሳደገ ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ የዓሣ ሀብት በዘልማድ ሲመራ እንደነበር በማስታወስ፤ አሁን ላይ ግን የዘርፉን የምርታማነት አቅም ማሻሻል የሚያስችል አሠራርና ፕሮጀክት ተቀርጾ መተግበሩን ገልጸዋል።

ለአብነትም የ10 ዓመት ፍኖተ ካርታ በማዘጋጀት ለዓሣ ሀብትና የውኃ አካላት ደኅንነት በማስተር ፕላን የሚመራበትን ዕድል መፍጠር እንደተቻለ ተናግረዋል።

የ10 ዓመቱ የዓሣ ሀብት ልማት ማስተር ፕላንም በዓመት ከ500 ሺህ ቶን በላይ ማምረት የሚያስችል እምቅ ሀብት መኖሩን እንደተረጋገጠ አንስተዋል።

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጭነት ተግባራዊ የተደረገው የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር የዓሣ ሀብት ምርታማነትን በሦስት እጥፍ ማሻሻል እንደተቻለ አስረድተዋል።

በዚህም በዓመት 70 እና 80 ሺህ ቶን የሚጠጋ የነበረውን የዓሣ ምርታማነት አሁን ላይ ወደ 300 ሺህ ቶን በማሳደግ ማምረት እየተቻለ መሆኑን አብራርተዋል።

የአፍሪካ ኅብረት የግብርና፣ ገጠር ልማት፣ ብሉ ኢኮኖሚ እና ዘላቂ ከባቢ አየር ኮሚሽነር ሞሰስ ቪላካቲ በበኩላቸው፤ ፕሮጀክቱ የአፍሪካን የዓሣ ሀብት ምርታማነት ለማሳደግ ጉልህ ጠቀሜታ አለው ብለዋል።

የአህጉሪቷን የዓሣ ሀብት ምርታማነት በማሻሻል የምግብ ሥርዓትን ለማሻሻል ከአባል ሀገራት ጋር በትብብር እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል።

የአህጉሪቷን የዓሣ ሀብት ልማት ዘላቂነት፣ የአስተዳደርና አጠቃቀም ሥርዓት ለማሻሻል አባል ሀገራት ቁርጠኛ የፖሊሲና የአሠራር ሥርዓት እርምጃ መውሰድ እንደሚኖርባቸው አስገንዝበዋል።

በፕሮጀክቱ አማካይነት ዘላቂ የውኃ ሥነ-ምህዳሮችንና ሁሉን አሳታፊ የዓሣ ሀብት እሴት ሰንሰለቶችን መደገፍ መቻሉን የገለጹት ደግሞ የአፍሪካ ኅብረት የእንስሳት ሀብት ጉዳዮች ቢሮ ዳይሬክተር ሁያም ሳሊህ ናቸው።


በውኃ ውስጥ የሚገኘው የዓሣ ሀብት በዘላቂነት እንዲጠበቅና የዓሣ አጥማጅ ማኅበረሰቦች የሚያገኙት ጥቅም እንዲጨምር ማድረግ መቻሉን ገልጸዋል።

ውጤታማና ለችግሮች ምላሽ የሚሰጥ የአስተዳደር ሥርዓትና የፖሊሲ ትግበራ ከሌለ፣ የግሉ ዘርፍ በዘላቂነት እንዲያድግ ምቹ ሁኔታ መፍጠር እንደማይቻል ገልጸዋል።

የፕሮጀክቱ የመጨረሻ ግብ ዘላቂ፣ ችግሮችን መቋቋም የሚችሉና ሁሉን አሳታፊ የውኃ ምግብ ሥርዓቶችን በመገንባት በአፍሪካ የምግብና የአመጋገብ ዋስትናን ማሻሻል መሆኑን ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

ሀብትን አውቆና አበልጽጎ ለትውልድ የሚተርፍ ወረት መፍጠር የመደመር መንግሥት ዋነኛ ዓላማ ነው - አቶ ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 5/2019 (ኢዜአ)፦የመደመር መንግሥት ዋና ዓላማ ያሉትን ሀብቶች አውቆና አበልጽጎ ለተከታዩ ትውልድ የሚተርፍ ወረት መፍጠር መሆኑን የኢፌ...

Oct 16, 2026

ኢትዮጵያ በሰጥቶ መቀበል መርህ የባህር በር ባለቤት ለመሆን የምታደርገው ጥረት ለቀጣናው ሰላም ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው

ዲላ፤ መስከረም 29/2019 (ኢዜአ) ፦ኢትዮጵያ በሰጥቶ መቀበል መርህ የባህር በር ባለቤት ለመሆን እያደረገች ያለው ጥረት ለቀጠናው ሰላምና መረጋጋት ያላትን ቁ...

Oct 10, 2026

በገጠር ዘመናዊ ህይወት መኖር ጀምረናል፤ የዚህ እድል ተጠቃሚ በመሆናችንም ተደስተናል- አርሶ አደሮች

ሚዛን አማን፣ መስከረም 13/2019 (ኢዜአ)፡-በገጠር ዘመናዊ ህይወት መኖር ጀምረናል፤ የዚህ እድል ተጠቃሚ በመሆናችንም ተደስተና ሲሉ በካፋ ዞን የሺሾ እንዴ ...

Sep 24, 2026

በክልሉ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የተጀመሩ ስራዎችን ማጠናከር ይጠበቅባቸዋል- ርእሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)

ሆሳዕና ፤ ነሐሴ 21/2018 (ኢዜአ) ፦ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ...

Aug 28, 2026