🔇Unmute
ሞስኮ፣ጥቅምት 17/ 2019 (ኢዜአ)፦አፍሪካ የምግብ ሉዓላዊነቷን ለማረጋገጥ ለምታደርገው ጥረት ራሽያ በግብናው ዘርፍ ያላትን የዳበረ ልምድ ለማካፈል ዝግጁ ናት ሲሉ የራሽያ የፕሬዚዳንት አስተዳደር ምክትል ኃላፊ ማክሲም ኦሬሽኪን ገለጹ።
የራሽያ-አፍሪካ ሚድያ ጉባዔ"የእያንዳንዱን የአፍሪካ ሀገር አቅም በጋራ ማሳደግ"በሚል ሐሳብ ተካሂዷል።

በሚዲያ ጉባኤው ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የራሽያ የፕሬዚዳንት አስተዳደር ምክትል ኃላፊ ማክሲም ኦሬሽኪን የሁለቱ አካላት ትብብር ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱን ገልጸዋል።
አፍሪካ ከጥገኝነት በመውጣት ሁሉ አቀፍ ሉዓላዊነቷን ማረጋገጥ ይገባታል ያሉት ምክትል ኃላፊው በተለይም በምግብ ራስን አለመቻል የአህጉሪቱ ተግዳሮት ሆኖ ሊቀጥል እንደማይገባ ጠቁመዋል።
ለዚህም ራሽያ ባላት ከፍተኛ የእርሻ ምርት አቅምና የቴክኖሎጂ ልምድ ከአፍሪካ አገራት ጋር በመተባበር ምርታማነትን ለማሳደግና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እንደምትሰራ ጠቁመዋል።
ራሽያ ከዓለም ቀዳሚ የስንዴ ላኪ አገራት አንዷ መሆኗን ገልፀው ፣እያደገ የመጣው ትብብርም የአፍሪካን የእርሻ ቴክኖሎጂ ሽግግር ለማፋጠን የሚያግዝ ነው ያሉት።
የሉዓላዊ ዓለም ሥርዓት ኢኮኖሚን ለመገንባት አፍሪካዊያን በራሳቸው አቅም ምግብ ማምረት፣ማቀነባበርና ራሳቸውን መመገብ እንዲችሉ ራሽያ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ ትቀጥላለች ብለዋል።
ይህ ጉባኤም ራሽያ ከአፍሪካ ጋር ያላትን ትብብር ሁሉን አቀፍ ለማድረግ የምታደርገውን ጥረት የሚያንፀባርቅ ነው ሲሉ ተናግረዋል።
የራሽያ እና አፍሪካ ሚድያ ተቋማትም የትብብር ግቦች እንዲሳኩ የመረጃ ልውውጥን በማጠናከር እና አዎንታዊ ምስል በመፍጠር ወሳኝ ሚና ይኖራቸዋል ብለዋል።
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 5/2019 (ኢዜአ)፦የመደመር መንግሥት ዋና ዓላማ ያሉትን ሀብቶች አውቆና አበልጽጎ ለተከታዩ ትውልድ የሚተርፍ ወረት መፍጠር መሆኑን የኢፌ...
Oct 16, 2026
ዲላ፤ መስከረም 29/2019 (ኢዜአ) ፦ኢትዮጵያ በሰጥቶ መቀበል መርህ የባህር በር ባለቤት ለመሆን እያደረገች ያለው ጥረት ለቀጠናው ሰላምና መረጋጋት ያላትን ቁ...
Oct 10, 2026
ሚዛን አማን፣ መስከረም 13/2019 (ኢዜአ)፡-በገጠር ዘመናዊ ህይወት መኖር ጀምረናል፤ የዚህ እድል ተጠቃሚ በመሆናችንም ተደስተና ሲሉ በካፋ ዞን የሺሾ እንዴ ...
Sep 24, 2026
ሆሳዕና ፤ ነሐሴ 21/2018 (ኢዜአ) ፦ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ...
Aug 28, 2026