
አዲስ አበባ፤ የካቲት 10/2017(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን መቋቋም የሚያስችሉ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን ተግባራዊ በማድረግ ውጤታማ ስራዎች እያከናወነች መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ገለጹ።
ስምንተኛው የአፍሪካ ቢዝነስ ፎረም “ከእመርታ ወደ ብልጽግና፤ የአፍሪካን ቀጣናዊ የእሴት ሰንሰለቶች አቅም ማጠናከር” በሚል መሪ ሀሳብ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።
የቢዝነስ ፎረሙ በአፍሪካ የቁም እንስሳት፣ ግብርና እና ፋርማሲዩቲካል ዘርፎች ቀጣናዊ የእሴት ሰንሰለት እና ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ልማት ላይ ያተኮረ ነው፡፡
ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በዚሁ ወቅት እንዳሉት በምርቶች ላይ እሴት መጨመር የአፍሪካን ዓለም አቀፋዊ ተወዳዳሪነት ያሳድጋል።
ለኢኮኖሚያዊ ዕድገትና ስራ ዕድል ፈጠራ ያለውን ፋይዳም ጠቅሰዋል።

ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን የመቋቋም አቅምን ከማሳደግ ረገድ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን ተግባራዊ እያደረገች መሆኑን ገልጸዋል።
በዚህም ተጨባጭ ውጤቶችን ማስመዘግቧን ጠቅሰው፤ በአጭር ጊዜ ምርታማነትን በመጨመር በስንዴ ምርት ራሷን መቻሏን ጠቁመዋል።
በአፍሪካ የማምረት አቅምን ለማሳደግ ለውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታ መፍጠር እንደሚገባም ገልጸዋል።
በዚህ ረገድ ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት በርካታ የኢንዱስትሪ ፓርኮችን በመገንባት ለኢንቨስትመነት ፍሰት ምቹ ሁኔታ መፍጠሯን አንስተዋል።
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡት ግቦች መሳካት ጉል...
Sep 4, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 10/2018 (ኢዜአ)፡- ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን መቻሉን የአዲስ አበባና የድሬዳዋ አስተዳደር ሥነ...
Aug 17, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 4/2018 (ኢዜአ)፡-በአዳማ ከተማ ከልማት ሥራዎች ጎን ለጎን ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር መሸፈኑን የከተማዋ ግብርና ጽሕ...
Aug 11, 2026
አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 30/2018 (ኢዜአ) ፦በባሕር ዳር ከተማ የተከናወኑ አበረታች የልማት እንቅስቃሴዎች የብልፅግና አቅጣጫዎችን በግልጽ ያመላከቱ መሆናቸውን ...
Aug 7, 2026