የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የባቡር ሐዲድ

የኢትዮጵያ የተቀማጭ ገንዘብ መድን ፈንድ ከአባል የፋይናንስ ተቋማት 13 ነጥብ 84 ቢሊየን ብር አረቦን ሰብስቧል

Jul 10, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 3/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የተቀማጭ ገንዘብ መድን ፈንድ ባለፉት ሁለት ዓመታት ከአባል የፋይናንስ ተቋማት 13 ነጥብ 84 ቢሊየን ብር መነሻ እና ዓመታዊ አረቦን መሰብሰቡን አስታውቋል።

የተቀማጭ ገንዘብ መድን ፈንድ ግንዛቤን ለማሳደግ ያለመ ወርክሾፕ እየተካሄደ ነው።

በመድረኩ የብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዥ እና የኢትዮጵያ ተቀማጭ ገንዘብ መድን ፈንድ የቦርድ ሊቀ መንበር ሰለሞን ደስታ፣ የኢትዮጵያ ተቀማጭ ገንዘብ መድን ፈንድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ደሳለኝ አምባው (ዶ/ር) እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

አቶ ሰለሞን ደስታ በዚሁ ጊዜ እንዳሉት የሀገሪቱ የፋይናንስ ስርዓት ጤናማ፣ ለአደጋ ያልተጋለጠና የተረጋጋ እንዲሆን ፈንዱ የበኩሉን ሚና ይጫወታል፡፡

ለገንዘብ አስቀማጮች ተገቢውን ጥበቃ በማድረግ ለፋይናንስ ሥርዓቱ መረጋጋት የላቀ አስተዋጽዖ ከማበርከት ባለፈ የሀገሪቱን የፋይናንስ ዘርፍ ለማረጋጋት ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ገልጸዋል።

ፈንዱ ከተመሠረተበት ጊዜ አንስቶ በርካታ ሥራዎችን በማቀድ የተጣለበትን ኃላፊነት በተሟላ እና በሚፈለገው ደረጃ እየተወጣ ይገኛል ነው ያሉት።

ገንዘብ አስቀማጮች እና ባለድርሻ አካላት ስለፈንዱ በቂ ግንዛቤና ዕውቀት እንዲኖራቸው መሰል መድረኮችን በማጠናከር ግንዘቤን ማስፋት እንደሚገባ ነው ያስታወቁት።

የኢትዮጵያ የተቀማጭ ገንዘብ መድን ፈንድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ደሳለኝ አምባው (ዶ/ር) በበኩላቸው ፈንዱ በአጭር ጊዜ ውስጥ በርካታ ሥራዎችን በማከናወን አመርቂ ውጤቶችን ማስመዝገቡን ተናግረዋል።

ፈንዱን በማደራጀት እና ለሥራ የሚያስፈልጉ የሰው ኃይል እና ሌሎች ግብዓቶችን በማሟላት ረገድ አበረታች ሥራ መስራቱን ጠቅሰዋል።

በዚህም ፈንዱ ባለፉት ሁለት ዓመታት ከአባል የፋይናንስ ተቋማት 13 ነጥብ 84 ቢሊዮን ብር መነሻ እና ዓመታዊ አረቦን መሰብሰቡን ተናግረዋል።

ፈንዱ በንግድ ባንኮችም ሆነ በአነስተኛ ፋይናንስ ተቋማት ገንዘብ ለሚቆጥበው ወይም ለሚያስቀምጠው ማኅብረሰብ ዋስትና የሚሰጥ ሲሆን፣ በባንኮች ላይ ወይም ማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ላይ አደጋ ቢያጋጥም፣ አስቀማጮች ካሳ የሚያገኙበት ስርዓት ነው።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የአፍሪካ የልማትና ትብብር ዓርማ - ታላቁ የሕዳሴ ግድብ በታዋቂው ታይም መጽሔት ገጽ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 1/2019 (ኢዜአ)፦የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ከኃይል ማመንጫነት በላይ ትርጉም ያለው፣ የአፍሪካን የውስጥ...

Sep 14, 2026

በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡ ግቦች መሳካት ጉልህ አስተዋጽኦ አለው-ዋምኬሌ ሜኔ

አዲስ አበባ፤ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡት ግቦች መሳካት ጉል...

Sep 4, 2026

ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን ተችሏል

አዳማ፤ ነሐሴ 10/2018 (ኢዜአ)፡- ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን መቻሉን የአዲስ አበባና የድሬዳዋ አስተዳደር ሥነ...

Aug 17, 2026

በአዳማ ከተማ ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር ተሸፍኗል

አዳማ፤ ነሐሴ 4/2018 (ኢዜአ)፡-በአዳማ ከተማ ከልማት ሥራዎች ጎን ለጎን ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር መሸፈኑን የከተማዋ ግብርና ጽሕ...

Aug 11, 2026