
መቱ፤ ሐምሌ 3/2017(ኢዜአ)፦ ግብርን በወቅቱ በመክፈል በከተማዋ የተጀመሩ የልማት ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ የበኩላችንን እንወጣለን ሲሉ ለኢዜአ አስተያየታቸውን የሰጡ የመቱ ከተማ ግብር ከፋዮች ተናገሩ።
በከተማው በ2018 በጀት ዓመት በአጠቃላይ ከ1 ቢሊዮን 100 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰብ ማቀዱን የመቱ ከተማ ገቢዎች ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።
አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ የከተማዋ ግብር ከፋዮች እንደገለፁት፤ በከተማዋ የተጀመሩ የኮሪደርም ሆነ ሌሎች የልማት ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ግብርን በወቅቱ በመክፈል የድርሻችንን እንወጣለን።

ከአስተያየት ሰጪዎቹ መካከል ስመኢሉ አበበ በከተማው የደረጃ 'ሐ' ግብር ከፋይ ሲሆኑ ግብርን መክፈል የሀገር ልማትን በማረጋገጥ የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማሳደግ ወሳኝ ነው።
ለዚህም ግብርን በወቅቱ በመክፈል ለማህበረሰቡ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት መረጋገጥ የድርሻቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል።

አቶ ሺፋ ቀኖ የተባሉ ግብር ከፋይ በበኩላቸው ግብርን በታማኝነትና በወቅቱ በመክፈል ልማትን መጠየቅ ተገቢ ነው ብለዋል።
ግብርን በታማኝነትና በወቅቱ በመክፈል ኃላፊነታቸውን እየተወጡ መሆኑን የገለፁት ወይዘሮ ካሰች ገዛኸኝ በከተማዋ እየተከናወነ ባለው የልማት ስራ ከተማዋ እየተለወች መሆኑን ተናግረዋል።
ለዚህም ግብርን በወቅቱ ከመክፈል በተጨማሪ ለከተማዋ ልማት መፋጠን የበኩላቸውን እንደሚወጡ አመልክተዋል።

በከተማው ኢኮኖሚው የሚያመነጨውን ገቢ በአግባቡ በመሰብሰብ ለታቀደለት ዓላማ ለማዋል በትኩረት ተግተን እየሰራን ነው ያሉት ደግሞ የመቱ ከተማ ገቢዎች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ዳንኤል ደበበ ናቸው።
በዚህም ባለፈው በጀት ዓመት 700 ሚሊዮን ብር መሰብሰቡን ተናግረው በ2018 በጀት ዓመት በአጠቃላይ ከ1 ቢሊዮን 100 ሚሊዮን በላይ ገቢ ለመሰብሰብ መታቀዱን አመልክተዋል።
በከተማው በተያዘው የበጀት ዓመት የገቢ ግብር አሰባሰቡን ስኬታማ ለማድረግ ግብር ከፋዮች ያለምንም እንግልትና የጊዜ ብክነት ግብር መክፈል የሚችሉበት የዘመነ የግብር አከፋፈል ስርዓት መዘርጋቱን ገልጸዋል።

የመቱ ከተማ ምክትል ከንቲባ ጆን ተስፋዬ በበኩላቸው በከተማው የሚታቀዱ የልማት ስራዎችን ከግብ ለማድረስ ከሁሉም የገቢ ምንጮች ለመሰብሰብ የታቀደውን ለማሳካት እንደሚሰራ ገልጸዋል።
አዲስ አበባ፤ መስከረም 1/2019 (ኢዜአ)፦የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ከኃይል ማመንጫነት በላይ ትርጉም ያለው፣ የአፍሪካን የውስጥ...
Sep 14, 2026
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡት ግቦች መሳካት ጉል...
Sep 4, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 10/2018 (ኢዜአ)፡- ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን መቻሉን የአዲስ አበባና የድሬዳዋ አስተዳደር ሥነ...
Aug 17, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 4/2018 (ኢዜአ)፡-በአዳማ ከተማ ከልማት ሥራዎች ጎን ለጎን ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር መሸፈኑን የከተማዋ ግብርና ጽሕ...
Aug 11, 2026