የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የባቡር ሐዲድ

አምቦ ዩኒቨርሲቲ የአርሶ አደሩን የግብርና ምርታማነት ይበልጥ ለማሳደግ በምርምር እየደገፈ ነው

Oct 23, 2025

IDOPRESS

🔇Unmute

አምቦ ፤ጥቅምት 11/2018(ኢዜአ)፡- አምቦ ዩኒቨርሲቲ የአርሶ አደሩን የግብርና ምርታማነት ማሳደግ የሚያስችሉ ዝርያዎችን በምርምር በማወጣት እየደገፈ መሆኑን ገለጸ።

በአምቦ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት የተመራ ቡድን በጉደር ማሞ መዘመር ካምፓስ በምርምር የተከናወኑና በመከናወን ላይ ያሉ የግብርና ሥራዎችን በመስክ ተመልክቷል።


በወቅቱ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ባይሳ ለታ(ዶ/ር) እንዳመለከቱት፤ ተቋሙ ከመማር ማስተማር ተግባሩ ጎን ለጎን የአካባቢውን ማህበረሰብ ህይወት ለማሻሻል የሚያስችሉ ምርምሮችን እያካሄደ ነው።

ሌሎች ድርጅቶችን በማሳተፍ ጭምር የአርሶ አደሩን ምርትና ምርታማነት ማሳደግ የሚያስችሉ የሰብል ዝሪያዎችን በምርምር አውጥቶ ለአርሶ አደሮች ማከፋፈሉን አንስተዋል።

የአካባቢው አርሶ አደር የቀረቡለትን የተሻሻሉ የሰብል ዝሪያዎች የተፈጥሮ ማዳበሪያን በመጠቀም ምርታቸውን ማሳደግ እንዲቻል በተከታታይ የባለሙያዎች ድጋፍ ተደርጎለታል ብለዋል።


በዚህም አርሶ አደሩ ውጤታማ መሆኑን ያመለከቱት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት፤ በተጨማሪም የወተት ላሞች እርባታ ፤ የዶሮ እርባታ እና የማር ምርት ከዩኒቨርሲቲው ማሕብረሰብ ባሻገር ለአካባቢው ነዋሪዎች በማቅረብ ተጠቃሚ እያደረገ መሆኑንም አስረድተዋል።

የዛሬው የመስክ ጉብኝት ዓላማም ዩኒቨርሲቲው የምርምርና የማሕበረሰብ አገልግሎቶችን ለባለድርሻ አካላት ማሳወቅ ብሎም ከሌሎች የምርምር ተቋማት ጋር የልምድ ልውውጥ ለማድረግ መሆኑን የገለጹት ደግሞ በዩኒቨርሲቲው የጉደር ማሞ መዘመር ካምፖስ ዳይሬክተር ንጉሴ በቀለ ( ዶ/ር ) ናቸው፡፡


በካምፓሱ የሰብል ምርምር ፤ የወተት ላሞች እና የዶሮ እርባታዎችን አርሶ አደሩና ሌላውም ማህበረሰብ በማሳተፍ ጭምር በመደገፍ ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

ሌላው የመስክ ጉብኝቱ ላይ የተገኙት የግብርና ተማራማሪ ተስፋዬ ሽፈራው(ዶ/ር) እንዳሉት፤ ከአምቦ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመቀናጀት በሚያደርጉት የምርምር ስራ የተሻለ ውጤት እየተገኘ ነው።

በዚህም ለአካባቢው ነዋሪዎችም በምርምር የተገኙ የተለያዩ የሰብል ዝሪያዎችን፣ የተሻሻሉ የወተት ላሞችንና ዶሮዎችን እያቀረብን ነው ብለዋል።


የቶኬ ኩታዬ ወረዳ ነዋሪ ወይዘሮ ሙሉ እመቤት ኢዶሳ በሰጡት አስተያየት፤ በአምቦ ዩኒቨርሲቲ የጉደር ማሞ መዘመር ካምፓስ የተለያየ ድጋፍ እያደረገላቸው መሆኑን ገልጸዋል።

ከካምፓሱ ከሶስት ዓመት በፊት የወተት ላም እንደተሰጣቸው ያስታወሱት ወይዘሮ ሙሉእመቤት ፤ ላሟ ሶስት ጥጃዎች በመውለዷ ተጠቃሚ እየሆንኩ ነው ብለዋል።


በተጨማሪም የተሻሻሉ የሰብል ዝሪያዎችን እንደሰጧቸው ጠቅሰው፤ ተቋሙ ለሌሎች የአካባቢው ነዋሪዎች ተመሳሳይ ድጋፍ ማድረጉን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የአፍሪካ የልማትና ትብብር ዓርማ - ታላቁ የሕዳሴ ግድብ በታዋቂው ታይም መጽሔት ገጽ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 1/2019 (ኢዜአ)፦የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ከኃይል ማመንጫነት በላይ ትርጉም ያለው፣ የአፍሪካን የውስጥ...

Sep 14, 2026

በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡ ግቦች መሳካት ጉልህ አስተዋጽኦ አለው-ዋምኬሌ ሜኔ

አዲስ አበባ፤ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡት ግቦች መሳካት ጉል...

Sep 4, 2026

ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን ተችሏል

አዳማ፤ ነሐሴ 10/2018 (ኢዜአ)፡- ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን መቻሉን የአዲስ አበባና የድሬዳዋ አስተዳደር ሥነ...

Aug 17, 2026

በአዳማ ከተማ ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር ተሸፍኗል

አዳማ፤ ነሐሴ 4/2018 (ኢዜአ)፡-በአዳማ ከተማ ከልማት ሥራዎች ጎን ለጎን ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር መሸፈኑን የከተማዋ ግብርና ጽሕ...

Aug 11, 2026