የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የባቡር ሐዲድ

ማዕከላቱ በመዲናዋ የምርት አቅርቦትና ፍላጎትን በማመጣጠን የተረጋጋ የግብይት ሥርዓት እንዲፈጠር አስችለዋል

Nov 6, 2025

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 26/2018(ኢዜአ)፡-በአዲስ አበባ የተገነቡ የንግድ ማዕከላት የምርት አቅርቦትና ፍላጎቱን በማመጣጠን የተረጋጋ የግብይት ሥርዓት እንዲፈጠር ሚናቸውን እየተወጡ መሆኑን ሸማቾችና ነጋዴዎች ገለጹ።

በአዲስ አበባ ሸማችና ነጋዴውን ማገናኘት የሚያስችሉ ግዙፍ የገበያ ማዕከላት ተገንብተው ወደ ስራ የገቡ ሲሆን ማዕከላቱ መሰረታዊ የፍጆታ ሸቀጦችን ጨምሮ የግብርናና የኢንዱስትሪ ምርቶችን በስፋት እያቀረቡ ይገኛሉ።


የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ጸጋየ ደበሌ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ በአዲስ አበባ ዘመናዊ የግብይት ሥርዓት ለመዘርጋትና የምርት አቅርቦትና ፍላጎትን ለማጣጣም የተለያዩ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን አንስተዋል።

በዚህም በመዲናዋ የተለያዩ ቦታዎች ግዙፍ የገበያ ማዕከላት መገንባታቸውን ጠቅሰው፤ ማዕከላቱ የሰብል፣ የአትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም የኢንዱስትሪ ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ እያቀረቡ እንደሚገኙ አስታውቀዋል።

በገበያ ማዕከላቱ የሚቀርቡ ምርቶች ከ15 እስከ 20 በመቶ የዋጋ ቅናሽ እንዳላቸው አመልክተዋል።

ከገበያ ማዕከላቱ በተጨማሪ የቅዳሜ እና እሁድ ገበያዎች ገበያን በማረጋጋት ረገድ ጉልህ ሚና እየተጫወቱ መሆኑን ጠቅሰዋል።


በገበያ ማዕከላቱ ሲገበያዩ ያገኘናቸው ፍቅሬ ድርሻ የሚፈልጉትን ምርት በተመጣጣኝ ዋጋ መገብየታቸውን ተናግረዋል።

ፈቲያ አሚኑ በበኩሏ በማዕከሉ ለገበያ የቀረቡ ምርቶች ውጭ ከሚሸጡበት ዋጋ ሰፊ ልዩነት እንዳላቸው ገልጻለች።


የአትክልት እና ፍራፍሬ ምርቶቹ ከአምራቾች በቀጥታ ለሸማቾች መቅረባቸው ጥራት ያላቸውን ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያገኙ ዕድል መፍጠሩን የተናገሩት ደግሞ ደረጀ ሀይሉ ናቸው።


በገበያ ማዕከሉ ምርቶቻቸውን ከሚያቀርቡ አምራቾች መካከል ጉርሙ ጨልቀባ የግብይት ሰንሰለቱን በማሳጠር ምርታቸውን በቀጥታ ለሸማቹ እያቀረቡ መሆኑን ገልጸዋል።


በመዲናዋ አራቱም ማዕዘናት በሚገኙ የገበያ ማዕከላት በተመጣጣኝ ዋጋ ጥራት ያለው ምርት እያቀረቡ መሆኑን የገለፁት አቶ ሄኖክ መንግስቱ የተባሉ አምራች ናቸው።


ሌላኛው አምራች አቶ አለማየሁ ራጎ በበኩላቸው መንግስት ለአምራቹ የመስሪያ ቦታ ማመቻቸቱ ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ ለሸማቾች እንዲደርሱ ዕድል መፍጠሩን አስታውቀዋል።


የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የአፍሪካ የልማትና ትብብር ዓርማ - ታላቁ የሕዳሴ ግድብ በታዋቂው ታይም መጽሔት ገጽ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 1/2019 (ኢዜአ)፦የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ከኃይል ማመንጫነት በላይ ትርጉም ያለው፣ የአፍሪካን የውስጥ...

Sep 14, 2026

በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡ ግቦች መሳካት ጉልህ አስተዋጽኦ አለው-ዋምኬሌ ሜኔ

አዲስ አበባ፤ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡት ግቦች መሳካት ጉል...

Sep 4, 2026

ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን ተችሏል

አዳማ፤ ነሐሴ 10/2018 (ኢዜአ)፡- ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን መቻሉን የአዲስ አበባና የድሬዳዋ አስተዳደር ሥነ...

Aug 17, 2026

በአዳማ ከተማ ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር ተሸፍኗል

አዳማ፤ ነሐሴ 4/2018 (ኢዜአ)፡-በአዳማ ከተማ ከልማት ሥራዎች ጎን ለጎን ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር መሸፈኑን የከተማዋ ግብርና ጽሕ...

Aug 11, 2026