🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ህዳር 14/2018(ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከቡድን 20 ጉባኤ ጎን በተካሄደው Compact with Africa (CwA) መርሃ ግብር ላይ ተካፍለዋል።
መርሃ ግብሩ ሥራው የደረሰበትን ደረጃ በመገምገም የወደፊት ትልሙን መመልከት ላይ ያተኮረ እንደነበር የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር በንግግራቸው የማክሮ ኢኮኖሚ መረጋጋት ሥራዎችን፣ እንደ ገበያን ክፍት የማድረግ ተግባራት፣ የቁጥጥር ማህቀፎች የማጠናከር ሥራዎች፣ የካፒታል ገበያዎችን የማበርታት እንቅስቃሴዎች ያሉ የኢትዮጵያን ወሳኝ የኢኮኖሚ ሪፎርም ሥራዎችን አንስተው የረጅም ጊዜ የግል ኢንቨስትመንትን በመሳብ የኢትዮጵያን ተወዳዳሪነት ከፍ ለማድረግ እንዳስቻሉ ማውሳታቸውንም ገልጿል።

መርሃግብሩ Compact with Africa 2.0 የአፍሪካን ብሎም የሰፊውን አለም የጋራ ብልጽግና በማሳደግ ረገድ ከፍ ያለ ርዕይ ሊይዝ እንደሚገባ ጥሪ በማስተላለፍ ተጠናቅቋል ነው ያለው።
አዲስ አበባ፤ መስከረም 1/2019 (ኢዜአ)፦የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ከኃይል ማመንጫነት በላይ ትርጉም ያለው፣ የአፍሪካን የውስጥ...
Sep 14, 2026
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡት ግቦች መሳካት ጉል...
Sep 4, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 10/2018 (ኢዜአ)፡- ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን መቻሉን የአዲስ አበባና የድሬዳዋ አስተዳደር ሥነ...
Aug 17, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 4/2018 (ኢዜአ)፡-በአዳማ ከተማ ከልማት ሥራዎች ጎን ለጎን ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር መሸፈኑን የከተማዋ ግብርና ጽሕ...
Aug 11, 2026