የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የባቡር ሐዲድ

በአማራ ክልል የቅርስ ጥገና፣ እንክብካቤና የሙዝየም ግንባታ እየተከናወነ ነው

Nov 26, 2025

IDOPRESS

🔇Unmute

ባህር ዳር፤ ሕዳር 16/2018(ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል ለቱሪዝም ዘርፍ በተሰጠው ትኩረት የቅርስ ጥገና፣ እንክብካቤና የሙዝየም ግንባታ እየተከናወነ መሆኑን የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ።

የቢሮው ሃላፊ መልካሙ ፀጋየ ለኢዜአ እንዳሉት፤ በክልሉ ከለውጡ ወዲህ የቱሪዝም ዘርፉን በማልማትና በማስተዋወቅ የዘርፉን ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ለማሳደግ ትኩረት ተሰጥቷል።

በተለይም ለቱሪዝም ዘርፍ በተሰጠው ትኩረት የመስህብ ሃብቶች ልማት፣ ቅርስ ጥበቃና እንክብካቤ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን አንስተዋል።

በክልሉ 437 ሚሊዮን ብር ተመድቦ የሙዚየሞች ግንባታና የቅርሶች ጥገና እየተካሄደ መሆኑን ለአብነት ጠቅሰዋል።

በግንባታ ላይ ካሉ ሙዝየሞች መካከል በባህርዳር የክልሉ ህዝብ ሙዝየም፣ በዋግ ህምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ሰቆጣ ከተማ የጀነራል ሀይሉ ከበደ መታሰቢያ ሙዝየም፣ በደቡብ ወሎ ዞን አምባሰል ወረዳ የይስማህ ንጉስ ሙዝየም እንደሚገኙበት ለአብነት ጠቅሰዋል።

በዚህ አመትም የ27 ቅርሶች ጥገና ስራ እንደሚጠናቀቅ ጠቁመው በማእከላዊ ጎንደር ዞን ጎንደር ዙሪያ ወረዳ የሚገኙ ባህሪ ግንብና ድብሳን ግንብ እንደሚገኙበት አመልክተዋል።

የክልሉን የቱሪስት መስህቦች የማልማትና ቅርሶችን የመጠበቅ ተግባራትም የሀገር ውስጥና የውጪ ሀገር ቱሪስቶችን ፍሰት ከማሳደጉ ባሻገር ቆይታቸውን ለማራዘም የሚያግዝ መሆኑን አስገንዝበዋል።

የቅርስ ጥበቃና እንክብካቤ ስራው የቱሪዝም ዘርፉን ከማሳደግ በለፈ ትውልዱ ታሪክን በመረዳት ለልማትና ለሰላም ይበልጥ እንዲተጋ የራሱ ድርሻ እንዳለውም ገልፀዋል።

በክልሉ የቅርስ ጥበቃ ስራው በመንግስትና በህብረተሰቡ ተሳትፎ የሚከናወን መሆኑን ጠቁመው ወደፊትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የአፍሪካ የልማትና ትብብር ዓርማ - ታላቁ የሕዳሴ ግድብ በታዋቂው ታይም መጽሔት ገጽ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 1/2019 (ኢዜአ)፦የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ከኃይል ማመንጫነት በላይ ትርጉም ያለው፣ የአፍሪካን የውስጥ...

Sep 14, 2026

በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡ ግቦች መሳካት ጉልህ አስተዋጽኦ አለው-ዋምኬሌ ሜኔ

አዲስ አበባ፤ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡት ግቦች መሳካት ጉል...

Sep 4, 2026

ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን ተችሏል

አዳማ፤ ነሐሴ 10/2018 (ኢዜአ)፡- ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን መቻሉን የአዲስ አበባና የድሬዳዋ አስተዳደር ሥነ...

Aug 17, 2026

በአዳማ ከተማ ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር ተሸፍኗል

አዳማ፤ ነሐሴ 4/2018 (ኢዜአ)፡-በአዳማ ከተማ ከልማት ሥራዎች ጎን ለጎን ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር መሸፈኑን የከተማዋ ግብርና ጽሕ...

Aug 11, 2026