የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የባቡር ሐዲድ

የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የአርሶአደሮችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት አሳድጓል

Nov 28, 2025

IDOPRESS

🔇Unmute

አምቦ ፤ ሕዳር 18/2018(ኢዜአ)፦ የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የምግብ ዋስትናቸውን ከማረጋገጥ አልፎ አኮኖሚያዊ አቅማቸውን ለማሳደግ እንዳገዛቸው የአምቦ ከተማ ዙሪያ አርሶ አደሮች ተናገሩ ።

የአምቦ ከተማ ዙሪያ የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት በዘር የመሸፈን የማስጀመሪያ መርሃ ግብር ዛሬ ተካሂዷል።


በመርሃ ግብሩ የተሳተፉ የአምቦ ከተማ ዙሪያ አርሶአደሮች ለኢዜአ እንደተናገሩት፤ የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የዝናብ ወቅትን ጠብቀው በአመት አንድ ጊዜ የሚያለሙትን ስርአት በመቀየር ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን ማሳደጋቸውን ተናግረዋል።

አርሶአደር አቶ ተሾመ ለገሠ እንዳሉት፤ ከዚህ በፊት የመኽር ሰብላቸውን ከሰበሰቡ በኃላ በበጋው ወቅት መሬታቸው ከልማት ውጭ እንደሚሆን አስታውሰዋል።


ባለፉት አመታት ግን በበጋው ወቅት ከልማት ውጪ የሆነውን መሬታቸውን በበጋ ስንዴ መስኖ ማልማት የሚችሉበትን ግንዛቤ ከግብርና ባለሙያዎች በማግኘታቸው ወደ ተግባር እንደገቡ ገልጸዋል፡፡

ለዘንድሮው የበጋ ስንዴ መስኖ ልማት መሬታቸውን ደጋግመው ማረሳቸውንና ምርጥ ዘርና ማዳበርያ በወቅቱ ማግኘታቸውን ተናግረዋል፡፡

ሌላው አርሶ አደር መለሰ ታምሩ በበኩላቸው፤ በመኽር ወቅት ያለሙትን የበቆሎ ሰብል በማንሳት በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት መሳተፋቸውን ጠቁመዋል።


በዚህም የበጋ መስኖ ስንዴ ልማቱ ገቢያቸውን ማሳደጉንና የምግብ ዋስትናቸውን ማረጋገጥ መቻሉን አስረድተዋል።

ከበጋ መስኖ ስንዴ ልማቱ ያገኙትን ጥቅም ለሌሎች አርሶ አደሮች እያካፈሉ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡

በከተማው የበጋ መስኖ ስንዴ እና አትክልትና ፍራፍሬን በ120 ሄክታር መሬት ለማልማት ታቅዶ ወደ ስራ መገባቱን የተናገሩት ደግሞ የአምቦ ከተማ ግብርና ጽህፈት ቤት ሀላፊ ተወካይ አቶ ታከለ ኩምሳ ናቸው፡፡


የከተማዋን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ በመኽር ወቅት ብቻ መስራቱ በቂ ባለመሆኑ የበጋ መስኖ ስንዴ፣ አትክልትና ፍራፍሬዎችን የማልማቱ ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉንና የበጋ መስኖ የስንዴ ልማቱ በዘር የመሸፈን መርሃ ግብሩ ዛሬ በይፋ መጀመሩን ተናግረዋል ፡፡

የአምቦ ከተማ ከንቲባ አቶ ሃጫሉ ገመቹ፤ በበጋ መስኖ ስንዴ ዘርን ባስጀመሩበት ወቅት እንዳሉት የአምቦ ከተማ ግብርና የማህበረሰቡን የምግብ ዋስትና ከማረጋገጥ አልፎ ለከተማዋ እድገት አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው።


አርሶ አደሩ ዝናብን ጠብቆ በዓመት አንድ ጊዜ ብቻ ሰብል የሚያመርትበትን የስራ ባህል ጭምር መቀየሩን አክለዋል።

በከተማዋ እየተለመደ የመጣው የበጋ መስኖ የስንዴ፣ አትክልትና ፍራፍሬዎች ልማት የነዋሪውን የተመጣጠነ ምግብ እቅርቦት ማሳደጉን ገልጸዋል።

የበጋ መስኖ ልማቱን ውጤታማ ለማድረግም የግብአትና የባለሙያ ድጋፍና ክትትል መጠናከሩን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የቡና ጥራትና ምርታማነትን ለማሻሻል የተጀመሩ ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ

እምድብር፤ ሐምሌ 18/2018(ኢዜአ):- የቡና ጥራትና ምርታማነትን ለማሳደግ የተጀመሩ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን አስታ...

Jul 27, 2026

በጌዴኦ ዞን ከ44 ሺህ 700 ሄክታር በላይ መሬት ለማልማት ወደ ተግባር ተገብቷል

ዲላ፤ ሐምሌ 13/2018 (ኢዜአ)፦ በጌዴኦ ዞን በ2018/19 የመኸር አዝመራ ወቅት ከ44 ሺህ 700 ሄክታር በላይ መሬት ለማልማት ታቅዶ ወደ ትግበራ መገባቱን...

Jul 21, 2026

ከአፍሪካ ትልሞች ጋር የተሳሰረው የኢትዮጵያ ሜጋ ፕሮጀክቶች ስኬት

ኢትዮጵያ በታሪክ አጋጣሚዎች በአፍሪካ የነጻነት ትግል ግንባር ቀደም በመሆን፣ የቅኝ ግዛት ቀንበርን በመስበር ለቀሪው አህጉር የተስፋ ብርሃን የፈነጠቀች ሀገር ና...

Jun 27, 2026

በኦሮሚያ ክልል የተከናወኑ የመስኖ ልማት ሥራዎች ዜጎችን ከተረጂነት አውጥተዋል

ሮቤ፣ሰኔ 18/2018(ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል የአርሶና አርብቶ አደሩን የድርቅ ተጋላጭነት ለመቀነስ የተከናወኑ የመስኖ ልማት ሥራዎች ዜጎችን ከተረጂነት በማውጣ...

Jun 26, 2026