የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የባቡር ሐዲድ

የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ ሀገራዊ ጥቅምን ያስቀደመ የመላው ህዝብ አጀንዳ ነው

Nov 28, 2025

IDOPRESS

🔇Unmute

ጎንደር፤ ህዳር 19/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ ሀገራዊ ጥቅምን ያስቀደመ የመላው ህዝብን የዘመናት ቁጭትን የሚመልስ ወቅታዊ አጀንዳ ነው ሲሉ በጎንደር ከተማ የሚንቀሳቀሱ የተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮች ተናገሩ፡፡

ትውልዱ ኢትዮጵያ የባህር በር ያጣችበት መንገድ ሁሌም ሲቆጭ መቆየቱና የህልውና ጉዳይ በመሆኑ ፈጣን ምላሽ እንዲገኝም መጠየቁ አልቀረም።

በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡት በጎንደር የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ሀገራዊ ጥቅምን ያስቀደመ የመላው ህዝብ አጀንዳ ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ ህዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ የአመራር አባል ካሳ በለጠ፤ኢትዮጵያ የባህር በር እንድታጣ የተደረገበት አካሄድ ሀገሪቱን ለማዳከም የተሸረበ ተግባር ነው ብለዋል።

የባህር በር ጥያቄው የሀገርን ጥቅም ያስቀደመና የህልውና ጉዳይ ነው ሲሉም ተናግረዋል፡፡

የባህር በር ጥያቄ የመላ ኢትዮጵያውያን ጉዳይ መሆኑን የገለፁት ደግሞ የቅማንት ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት ተገኑ ደረጀ ናቸው።

የህብር ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሃላፊ መኮንን ብርሃን የባህር በር ባለቤትነት ጉዳይ ወቅታዊና ህዝባዊ አጀንዳ መሆኑን ጠቁመዋል።

ኢትዮጵያ ከ30 ዓመታት በላይ ከቀይ ባህር ርቃ ቆይታ ዳግም ለመመለስ በምትችልበት አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ላይ ትገኛለች ሲሉም አስረድተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የአፍሪካ የልማትና ትብብር ዓርማ - ታላቁ የሕዳሴ ግድብ በታዋቂው ታይም መጽሔት ገጽ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 1/2019 (ኢዜአ)፦የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ከኃይል ማመንጫነት በላይ ትርጉም ያለው፣ የአፍሪካን የውስጥ...

Sep 14, 2026

በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡ ግቦች መሳካት ጉልህ አስተዋጽኦ አለው-ዋምኬሌ ሜኔ

አዲስ አበባ፤ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡት ግቦች መሳካት ጉል...

Sep 4, 2026

ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን ተችሏል

አዳማ፤ ነሐሴ 10/2018 (ኢዜአ)፡- ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን መቻሉን የአዲስ አበባና የድሬዳዋ አስተዳደር ሥነ...

Aug 17, 2026

በአዳማ ከተማ ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር ተሸፍኗል

አዳማ፤ ነሐሴ 4/2018 (ኢዜአ)፡-በአዳማ ከተማ ከልማት ሥራዎች ጎን ለጎን ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር መሸፈኑን የከተማዋ ግብርና ጽሕ...

Aug 11, 2026