የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የባቡር ሐዲድ

ግድቡ አፍሪካውያን ለጋራ ራዕይ ከቆሙ ህልማቸውን ማሳካት እንደሚችሉ ያሳየ ነው - የኢጋድ የሚዲያ ሽልማት አሸናፊዎች እና ተሳታፊ ጋዜጠኞች

Dec 2, 2025

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ ህዳር 22/2018(ኢዜአ)፦ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አፍሪካውያን ለጋራ ራዕይ ከቆሙ ህልማቸውን ማሳካት እንደሚችሉ ያሳየ ነው ሲሉየምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) የሚዲያ ሽልማት አሸናፊዎች እና ተሳታፊ ጋዜጠኞች ገለጹ።

የታላቁ ሕዳሴ ግድብ የአፍሪካን ትርክት በመቀየር ትልቅ ሚና የሚወጣ ግዙፍ ፕሮጀክት መሆኑንም ተናግረዋል።

ሶስተኛው የኢጋድ የሚዲያ ሽልማት ለሁለት ቀናት በአዲስ አበባ ኢትዮጵያ መካሄዱ ይታወቃል።

የሶስተኛው የኢጋድ የሚዲያ ሽልማት አሸናፊዎች እና ተሳታፊ ጋዜጠኞች ዛሬ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን ጎብኝተዋል።

በሴት ጋዜጠኞች ዘርፍ አሸናፊ ከሆኑት መካከል ዩጋንዳዊቷ ጋዜጠኛ አይባሬ ሲንደሬላ ኢትዮጵያ በዜጎቿ አስተዋጽኦ ህዳሴ ግድብን ለመገንባት ያሳየችውን ቁርጠኝነት አድንቃለች።

በበርካታ ሀገራት ዜጎች ከሚከፍሉት ታክስ ተጨባጭ ውጤቶችን እምብዛም ሲያዩ አይስተዋልም ያለችው ጋዜጠኛዋ ኢትዮጵያ በግልጽነትና በጠንካራ ራዕይ የህዝብን ሀብቶች አሻጋሪ ብሄራዊ ፕሮጀክት መቀየሯን ተናግራለች።

የአፍሪካ መሪዎች ከሕዳሴ ግድብ ጠቃሚ ተሞክሮዎችን ሊወስዱ ይገባል ብላለች።

የኬንያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ከፍተኛ አዘጋጅ አሻ ሃሚሲ አፍሪካውያን የራሳቸውን ችግሮች ያለ ምንም ጣልቃ ገብነት መፍታት እንዳለባቸው ገልጻለች።

ሕዳሴ ግድብ ዜጎች ለሀገራቸው መስዋዕትነት እንደሚከፍሉ የሚያሳይ ፕሮጀክት ነው ያለችው አሻ ይህም በህዝብ እና በመንግስት መካከል ያለ መተማመንና ነገን የተሻለ ለማድረግ ዛሬ ላይ መስራት ያለውን ቁርጠኝነት የሚያመላከት ነው ብላለች።

ግድቡ አፍሪካውያን ለጋራ ራዕይ ከቆሙ ህልማቸውን ማሳካት እንደሚችሉ ያሳየ እንደሆነም ተናግራለች።

በኢጋድ ሚዲያ ሽልማት በዲጂታል ሚዲያ ዘርፍ ካሸነፉት ጋዜጠኞች መካከል አንዱ የሆነው ደቡብ ሱዳናዊው የፊልም ባለሙያ እና ተራኪ ጋብርኤል ጋትሉዋክ ዋል ኬት በበኩሉ ህዳሴ ግድብ አፍሪካ ያላትን አቅም በተግባር ያሳየ ነው ሲል ተናግሯል።

ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን የመሰለ ግዙፍ ፕሮጀክት ካሳካች ሌሎች ሀገራትም ይህን ፈለግ ተከትለው ትላልቅ ፕሮጀክቶችን እውን ማድረግ ይችላሉ ብሏል።

አፍሪካውያን ሀገራቸውን በራሳቸው መገንባት እንደሚችሉ ማመን አለባቸው ያለው ኬት የራሳቸውን ዕጣ ፈንታ ሌሎች እንዲወስኑላቸው መፍቀድ የለባቸውም ሲልም ገልጿል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው ለሕዳሴ ግድብ ኢትዮጵያን እና በውጭ የሚኖሩ ዳያስፖራዎች የከፈሉትን መስዋዕትነት አንስተዋል።

ሕዳሴ ግድ የአፍሪካ የስኬት ተምሳሌት ፕሮጀክት እንደሆነ ገልጸው ከግድቡ የሚገኘው የኤሌክትሪክ ኃይል ጎረቤት ሀገራትን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ አመልክተዋል።

ይህም ቀጣናዊ ትስስርን የሚያጠናክርና የአፍሪካ ህብረት አጀንዳ 2063 ራዕይ የሆነውን የበለጸገች እና የተሳሰረች አፍሪካን የመፍጠር ራዕይን እንደሚደግፍም ተናግረዋል።

ግድቡ የአፍሪካን ትርክት የመቀየር ትልቅ ኃይል ያለው ፕሮጀክት ነው ብለዋል አምባሳደሩ።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የቡና ጥራትና ምርታማነትን ለማሻሻል የተጀመሩ ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ

እምድብር፤ ሐምሌ 18/2018(ኢዜአ):- የቡና ጥራትና ምርታማነትን ለማሳደግ የተጀመሩ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን አስታ...

Jul 27, 2026

በጌዴኦ ዞን ከ44 ሺህ 700 ሄክታር በላይ መሬት ለማልማት ወደ ተግባር ተገብቷል

ዲላ፤ ሐምሌ 13/2018 (ኢዜአ)፦ በጌዴኦ ዞን በ2018/19 የመኸር አዝመራ ወቅት ከ44 ሺህ 700 ሄክታር በላይ መሬት ለማልማት ታቅዶ ወደ ትግበራ መገባቱን...

Jul 21, 2026

ከአፍሪካ ትልሞች ጋር የተሳሰረው የኢትዮጵያ ሜጋ ፕሮጀክቶች ስኬት

ኢትዮጵያ በታሪክ አጋጣሚዎች በአፍሪካ የነጻነት ትግል ግንባር ቀደም በመሆን፣ የቅኝ ግዛት ቀንበርን በመስበር ለቀሪው አህጉር የተስፋ ብርሃን የፈነጠቀች ሀገር ና...

Jun 27, 2026

በኦሮሚያ ክልል የተከናወኑ የመስኖ ልማት ሥራዎች ዜጎችን ከተረጂነት አውጥተዋል

ሮቤ፣ሰኔ 18/2018(ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል የአርሶና አርብቶ አደሩን የድርቅ ተጋላጭነት ለመቀነስ የተከናወኑ የመስኖ ልማት ሥራዎች ዜጎችን ከተረጂነት በማውጣ...

Jun 26, 2026