የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የባቡር ሐዲድ

ሰብል በሚሰበሰብበትና በሚከማችበት ወቅት ብክነት እንዳይኖር ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል

Dec 2, 2025

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ ሕዳር 22/2018 (ኢዜአ)፡- ሰብል በሚሰበሰብበትና ምርት በሚቀመጥበት ወቅት ብክነት እንዳይኖር አርሶ አደሩ ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ግብርና ቢሮ አሳሰበ።

በቢሮው የሰብል ልማትና ጥበቃ ዳይሬክተር ታገል ታምሩ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ በ2017/18 የመኸር ወቅት 371 ሺህ 975 ሔክታር የእርሻ መሬት በዘር መሸፈኑን እና ከ 8 ነጥብ 5 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት እንደሚጠበቅ ገልጸዋል።

በአጠቃላይ በዘር ከተሸፈነው 85 ሺህ 568 ሔክታሩ በ1 ሺህ 723 ክላስተሮች በተደራጁ አርሶ አደሮች መልማቱን አስረድተዋል።

አሁን ላይ በሜካናይዜሽን እና በሰው ኃይል የደረሱ ሰብሎችን የመሰብሰብ ሥራ በትጋት እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።


እስካሁን ባለው ሂደትም ከ133 ሺህ 500 ሔክታር መሬት ላይ ሰብል መሰብሰቡን ገልጸው፤ ከዚህም ከ3 ነጥብ 5 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት መገኘቱን አረጋግጠዋል።

በመኸሩ ወቅት ዋናዋና የምግብ ሰብሎች የሚባሉት ጤፍ፣ ስንዴ፣ ሩዝ፣ ገብስ፣ በቆሎ፣ ባቄላ፣ አተር፣ ማሽላ፣ ቦሎቄ፣ ማሾ እና ሌሎችም በስፋት መልማታቸውን አብራርተዋል።

ድንገት በሚጥል ዝናብ ምክንያት የምርት መበላሸት እንዳይኖር የደረሱ ሰብሎችን ሁሉንም አማራጭ በመጠቀም በፍጥነትና በአግባቡ መሰብሰብ እንደሚገባም አሳስበዋል።


በሌላ በኩል የተሰበሰበ ምርትን በደረቅ ቦታ በማስቀመጥ የምርት ብክነት እንዳይኖር ጥንቃቄ እንዲደረግ መክረዋል።

የግብርና ባለሙያዎችም ለአርሶ አደሩ ሙያዊ ድጋፋቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የአፍሪካ የልማትና ትብብር ዓርማ - ታላቁ የሕዳሴ ግድብ በታዋቂው ታይም መጽሔት ገጽ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 1/2019 (ኢዜአ)፦የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ከኃይል ማመንጫነት በላይ ትርጉም ያለው፣ የአፍሪካን የውስጥ...

Sep 14, 2026

በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡ ግቦች መሳካት ጉልህ አስተዋጽኦ አለው-ዋምኬሌ ሜኔ

አዲስ አበባ፤ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡት ግቦች መሳካት ጉል...

Sep 4, 2026

ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን ተችሏል

አዳማ፤ ነሐሴ 10/2018 (ኢዜአ)፡- ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን መቻሉን የአዲስ አበባና የድሬዳዋ አስተዳደር ሥነ...

Aug 17, 2026

በአዳማ ከተማ ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር ተሸፍኗል

አዳማ፤ ነሐሴ 4/2018 (ኢዜአ)፡-በአዳማ ከተማ ከልማት ሥራዎች ጎን ለጎን ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር መሸፈኑን የከተማዋ ግብርና ጽሕ...

Aug 11, 2026