🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ሕዳር 22/2018 (ኢዜአ)፡- ሕዝብን በማስተባበር እየተከናወኑ የሚገኙ ሥራዎች ሐረር ቀደምት ስልጣኔዋን በሚመጥን ደረጃ ላይ እንድትገኝ እያስቻሉ መሆኑን የሐረሪ ክልል የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ገለጸ።
ሐረር ከተማ የዘመናዊ ከተሜነትን እሳቤ ቀድሞ በመተግበር ከሚጠቀሱት ግንባር ቀደሞች መካከል መሆኗን የሐረሪ ክልል የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሔኖክ ሙሉነህ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ አውስተዋል።
ይሁን እንጅ በተለይም ከለውጡ መንግሥት በፊት ለውጥን እንደናፈቀች የሕዝቦቿም የመልማት ፍላጎት ከምኞት መሻገር ሳይችል መቆየቱን በቁጭት አንስተዋል።

ከለውጡ መንግሥት ወዲህ ግን የአመራሩ ቁርጠኝነት እና ሕዝቡ በልማቱ የመሳተፍ ዐቅም በይበልጥ በማደጉ ከተማዋን የማዘመን ተግባራት አርአያ በሚሆን መልኩ እየተሠሩ መሆኑን ጠቅሰዋል።
ለአብነትም፤ ከኮሪደር ልማቱ ጅማሮ ማግስት የክልሉ መንግሥት የአካባቢያዊ ፀጋዎችንና ዐቅሞችን መነሻ ያደረጉ ውጤታማ ሥራዎችን በተቀናጀና በተናበበ መልኩ እያከናወነ እንደሚገኝም ጠቁመዋል።
ይህን ተከትሎም በአነስተኛ ወጪ፣በላቀ የአመራር ጥበብና ቁርጠኝነት ሕዝብን በማስተባበር እየተከናወኑ የሚገኙ ሥራዎች የከተማዋን ታሪክና ቀደምት ሥልጣኔ በሚመጥን ደረጃ እንድትገኝ የሚያስችሉ ናቸው።
ሐረር ዛሬ በይበልጥ መነቃቃቷን የገለጹት ኃላፊው፤ ወደ ኋላ የቀረችባቸው ዓመታትን ለመካስ በሚያስችል ደረጃ ቀንና ሌሊት እየተሠራ ነው ብለዋል።
አመራሩም ለሥራዎቹ ጥራትና ፍጥነት በላቀ ኃላፊነት ክትትል እያደረገ እንደሚገኝም አክለዋል።
የተሽከርካሪና የብስክሌት እንዲሁም የእግረኛ መንገድን ጨምሮ አረንጓዴ ስፍራንና ዘመናዊ የመንገድ ዳር መብራቶችን ባካተተ መልኩ እየተሠራ የሚገኘው የኮሪደር ልማት ከተማዋን ለነዋሪዎች ምቹ፣ ውብና ማራኪ እንድትሆን አስችሏል ብለዋል።
የክልሉ ሕዝብና መንግሥት እጅ ለእጅ በመያያዝ እያኖሩት የሚገኘው አዲስ የስኬት ታሪክም የከተማውን ውበት የገለጠ ብቻ ሳይሆን፤ በክልሉ ያለውን እምቅ የቱሪዝም ዐቅም ለመጠቀም ያገዘ ነው ብለዋል።
በከተማው በየአካባቢው እውን የተደረጉና እየተደረጉ የሚገኙ የኮሪደር ልማት ሥራዎችም ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል ተጠቃሚ ማድረጉንም ጠቅሰዋል።
በተጨማሪም ከፅዳት መጓደል ጋር በተያያዘ ሲስተዋሉ የቆዩ ችግሮችን በመቅረፍ ረገድም ተጨባጭ ውጤት ማስገኘቱን አረጋግጠዋል።
የሐረርን ከፍታ ሲመኙ የነበሩ የከተማው ነዋሪዎችም እያደረች እየፈካች በምትገኘ ከተማቸው ልማት ላይ ሁሉን አቀፍ ድጋፍ እያደረጉ መሆናቸውን አመላክተዋል።
ከሰሃራ በታች ካሉ የአፍሪካ ከተሞች ብቸኛዋ የዓለም ቅርስ ከተሞች ድርጅት አባል በሆነችው ሐረር ከተማ ቀን ከሌሊት በመሥራት በአጭር ጊዜ የተገኘው ውጤትና የተመዘገበው ስኬትም የሥራ ባህልን የቀየረና የይቻላል መንፈስን ያሰረፀ ሆኗል ነው ያሉት።
የሕዝቡን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን በሚያሳድግ መልኩ እየተሠሩ የሚገኙ ሥራዎችና የታዩ ውጤቶችም የሐረርን ገናናነት ዳግም እውን ማድረግ እንደሚቻል አመላካች መሆኑን በአጽንኦት አንስተዋል ኃላፊው።
አዲስ አበባ፤ መስከረም 1/2019 (ኢዜአ)፦የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ከኃይል ማመንጫነት በላይ ትርጉም ያለው፣ የአፍሪካን የውስጥ...
Sep 14, 2026
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡት ግቦች መሳካት ጉል...
Sep 4, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 10/2018 (ኢዜአ)፡- ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን መቻሉን የአዲስ አበባና የድሬዳዋ አስተዳደር ሥነ...
Aug 17, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 4/2018 (ኢዜአ)፡-በአዳማ ከተማ ከልማት ሥራዎች ጎን ለጎን ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር መሸፈኑን የከተማዋ ግብርና ጽሕ...
Aug 11, 2026