የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የባቡር ሐዲድ

በምስራቅ ሐረርጌ ዞን በ20 ወረዳዎች ሙዝ በኩታ ገጠም እየለማ ነው

Dec 2, 2025

IDOPRESS

🔇Unmute

ሐረር ፤ ሕዳር 23/2018 (ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሐረርጌ ዞን በ20 ወረዳዎች ሙዝ በኩታ ገጠም እየለማ መሆኑን የዞኑ አስተዳደር ገለጸ።

በኦሮሚያ ክልል ባለው ምቹ ሥነ ምህዳር፣ ተስማሚ የአየር ንብረትና ሰፊ የሚለማ መሬት ልክ አልምቶ የህዝቡን ተጠቃሚነት ለማሳደግ የተለያዩ የግብርና ልማት ኢንሼቲቮች ተቀርጸው ወደ ተግባር ገብተዋል።

ከእነዚህ አዳዲስ ኢንሼቲቮች መካከል የሻይ ቅጠል፣ አቮካዶ፣ ፓፓያ፣ ሩዝ፣ የበጋ መስኖ ስንዴ እና ሙዝ ልማት ተጠቃሾች ናቸው።

ምሥራቅ ሐረርጌ ዞንም የክልሉን የልማት ኢንሼቲቮች ተቀብለው ተግባራዊ ካደረጉ ዞኖች አንዱ ነው።


የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ወይዘሮ ሚስኪ መሐመድ ለኢዜአ እንደተናገሩት፤ እንደ ምስራቅ ሐረርጌ ዞን በኢንሼቲቭ ከሚከናወኑና ትልቅ ለውጥ እያስገኙ ከሚገኙት የልማት መስኮች አንዱ የሙዝ ምርት ነው።

በ2011 ዓ.ም በስድስት ወረዳዎች የተጀመረው የሙዝ ልማት ኢንሼቲቭ በአሁኑ ወቅት በ20 ወረዳዎች ላይ በኩታገጠም እየለማ ይገኛል ብለዋል።


ከዚህ በተጨማሪ በዞኑ አቮካዶ፣ ብርትኳንና የመሳሰሉት ፍራፍሬዎች እየለሙና ሌሎች የሌማት ትሩፋት ተግባራትም እየተከናወኑ መሆኑን ተናግረዋል።

በልማት ስራው እየተሳተፉ የሚገኙ የተደራጁ ወጣቶችና አርሶ አደሮችም ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸው እያደገ መምጣቱን ገልጸዋል።

የሙዝ ምርቱ ከዞኑ ባለፈ ለድሬዳዋ፣ ሐረርና ጅግጅጋ አካባቢዎች እንዲሁም ጅቡቲን ጨምሮ ለጎረቤት አገራት ገበያ እየቀረበ መሆኑን ጠቅሰው የሙዝ ልማቱን የማስፋት ስራ በተጠናከረ መልኩ ይቀጥላል ብለዋል።


በዞኑ ሙዝ አብቃይ ከሆኑ ወረዳዎች መካከል የጉርሱም ወረዳ አንዱ ሲሆን በወረዳው የሃሮ ባቴ ቀበሌ ሊቀመንበር አቶ ንዋይ ታዬ ፤ በቀበሌው በ6 ነጥብ 5 ሄክታር መሬት ላይ የተጀመረው የሙዝ ልማት በአሁኑ ወቅት ወደ 26 ነጥብ 5 ሄክታር መሬት ከፍ ብሎ በኩታ ገጠም እየለማ መሆኑን ገልጸዋል።


በቀበሌው በኩታ ገጠም እየለማ የሚገኘውና አርሶ አደሩን ተጠቃሚ ያደረገው የሙዝ ዝርያ የተሻለ ምርት የሚሰጥ መሆኑን በመረዳት የማስፋት ስራ እየተከናወነ ይገኛል ብለዋል።

በወረዳው የሙዝና አቮካዶ ልማት ኢንሼቲቭ በስፋት እየተከናወነ ይገኛል ያሉት ደግሞ በጉርሱም ወረዳ የቡናና ፍራፍሬ ልማት ቡድን መሪ አቶ ሶሬሳ ንጉሳ ናቸው።


በተለይ በወረዳው 1 ሺህ 472 አርሶ አደሮች ሙዝን በኩታገጠም እያለሙና ተጠቃሚነታቸውንም እያረጋገጡ እንደሚገኙ ጠቁመው የሙዝ ልማትን የማጎልበት ስራው እየተከናወነ መሆኑንም ተናግረዋል።

በጉርሱም ወረዳ የሃሮ ባቴ ቀበሌ ነዋሪው አርሶ አደር ከድር አብዱላሂ፣ በኩታገጠም ሙዝ እያመረቱበት የሚገኘው መሬት ቀደም ሲል ምንም ጥቅም ሳይሰጥ የቆየ መሆኑን አንስተዋል።


ባለፈው ዓመት ባከናወኑት ስራ 2 ሚሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘታቸውን እና ዘንድሮ ከአምናው ሶስት እጥፍ ገቢ የሚያስገኝ የሙዝ ልማት ማከናወናቸውን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የአፍሪካ የልማትና ትብብር ዓርማ - ታላቁ የሕዳሴ ግድብ በታዋቂው ታይም መጽሔት ገጽ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 1/2019 (ኢዜአ)፦የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ከኃይል ማመንጫነት በላይ ትርጉም ያለው፣ የአፍሪካን የውስጥ...

Sep 14, 2026

በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡ ግቦች መሳካት ጉልህ አስተዋጽኦ አለው-ዋምኬሌ ሜኔ

አዲስ አበባ፤ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡት ግቦች መሳካት ጉል...

Sep 4, 2026

ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን ተችሏል

አዳማ፤ ነሐሴ 10/2018 (ኢዜአ)፡- ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን መቻሉን የአዲስ አበባና የድሬዳዋ አስተዳደር ሥነ...

Aug 17, 2026

በአዳማ ከተማ ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር ተሸፍኗል

አዳማ፤ ነሐሴ 4/2018 (ኢዜአ)፡-በአዳማ ከተማ ከልማት ሥራዎች ጎን ለጎን ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር መሸፈኑን የከተማዋ ግብርና ጽሕ...

Aug 11, 2026