የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የባቡር ሐዲድ

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ የሀገሪቱን የፋይናንስ ስርዓት በማሳለጥ የጎላ ሚና አለው

Dec 3, 2025

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ ህዳር 23/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ የሀገሪቱን የፋይናንስ ስርዓት በማሳለጥ የጎላ ሚና እንዳለው የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ ገለጹ፡፡

ከዛሬ ጀምሮ ለሶስት ተከታታይ ቀናት የሚካሄደው ሁለተኛው ቀጣናዊ የካፒታል ገበያ ጉባኤ በአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል መካሄድ ጀምሯል።

የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ የካፒታል ገበያ የኢትዮጵያን መፃኢ የፋይናንስ ስርዓት የሚያሳልጥ መሰረታዊ ጉዳይ ነው።


ኢትዮጵያ አካታች የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ በማድረግ በሁሉም ዘርፎች ተጨባጭ ውጤት እያስመዘገበች ትገኛለች ብለዋል።

ማሻሻያው ወደ ተሟላ ትግበራ ከገባ ወዲህ ማክሮ ኢኮኖሚውን በማረጋጋት ሁሉን አቀፍ ዕድገት ማረጋገጥ በሚያስችል ሂደት ላይ መሆኑን ገልጸዋል።

የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሙን ተከትሎ ባለፉት ጥቂት ዓመታት የሀገር ውስጥ ገቢን በማስፋት ዕምርታዊ ለውጥ መመዝገቡንም ገልጸዋል።

በኢኮኖሚ ሪፎርሙ መሰረት ወደ ሥራ የገባው የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን የኢትዮጵያን የፋይናንስ ስርዓት በማሳለጥ ቁልፍ ሚና ይኖረዋል ነው ያሉት።

በመንግሥት የልማት ድርጅቶች ላይ ሪፎርም መደረጉን የገለጹት ሚኒስትሩ፤ የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ የሚያሳድግ ምቹ የኢንቨስትመንት ምህዳር መፍጠር ተችሏል ብለዋል።

ሪፎርሙ ግልጽነትን በመፍጠር፣ በማዕከላዊ ባንክ ላይ ብቻ የተመሰረተውን የፋየናንስ ስርዓት በመቀነስ እና የታክስ መሰረቱን በማስፋት የሚታይ ለውጥ ማምጣቱን ገልጸዋል፡፡

የካፒታል ገበያ ሰፊ የስራ ዕድል በመፍጠር ለኢኮኖሚያዊ ሽግግር ወሳኝ መሆኑን አንስተው፤ ለኢትዮጵያ የፋይናንስ ስርዓት ዝማኔ ቁልፍ መሳሪያ ሆኖ እንደሚያገለግል ገልጸዋል፡፡

በኢትዮጵያ ተዓማኒና ለግሉ ዘርፍ ተስማሚ የፋይናንስ ምህዳር ለማስፈን በተቋማት መካከል ጠንካራ ትብብር መፍጠር እንደሚገባ አመልክተዋል፡፡

በአግባቡ የተደራጀ እና የተሟላ መሰረተ ልማት ያለው የካፒታል ገበያ ስርዓት የኢትዮጵያን የፋይናንስ ዘርፍ ለማሳደግና ከዓለም የፋይናንስ ተቋማት ጋር ለማስተሳሰር ያግዛል ብለዋል።

የካፒታል ገበያ የኢትዮጵያን መሰረተ ልማት በተለያዩ የቦንድ ኢንቨስትመንት አማካይነት ወደ ሀብት መቀየር የሚያስችል ዕድል መፍጠሩንም ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የአፍሪካ የልማትና ትብብር ዓርማ - ታላቁ የሕዳሴ ግድብ በታዋቂው ታይም መጽሔት ገጽ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 1/2019 (ኢዜአ)፦የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ከኃይል ማመንጫነት በላይ ትርጉም ያለው፣ የአፍሪካን የውስጥ...

Sep 14, 2026

በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡ ግቦች መሳካት ጉልህ አስተዋጽኦ አለው-ዋምኬሌ ሜኔ

አዲስ አበባ፤ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡት ግቦች መሳካት ጉል...

Sep 4, 2026

ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን ተችሏል

አዳማ፤ ነሐሴ 10/2018 (ኢዜአ)፡- ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን መቻሉን የአዲስ አበባና የድሬዳዋ አስተዳደር ሥነ...

Aug 17, 2026

በአዳማ ከተማ ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር ተሸፍኗል

አዳማ፤ ነሐሴ 4/2018 (ኢዜአ)፡-በአዳማ ከተማ ከልማት ሥራዎች ጎን ለጎን ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር መሸፈኑን የከተማዋ ግብርና ጽሕ...

Aug 11, 2026