🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ሕዳር 27/2018(ኢዜአ)፦ ካሜሩን በካሜሩን ቴሌኮሙኒኬሽን (CAMTEL) እና ኢትዮ ቴሌኮም የፈጠሩት ስትራቴጂካዊ ጥምረት ውጤታማ እንዲሆን አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ የሀገሪቷ ጠቅላይ ሚኒስትር ጆሴፍ ዲዮን ንጉቴ(ዶ/ር) ገለጹ።
የካሜሩን ቴሌኮሙኒኬሽን (CAMTEL) እና ኢትዮ ቴሌኮም በካሜሩን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽንን ማፋጠን የሚያስችል የኮንትራት ስምምነት ተፈራርመዋል።

ስምምነቱን በካሜሩን ያውንዴ በመገኘት የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ እና የካምቴል ዋና ስራ አስኪያጅ ጁዲት ያህ ሰንዴይ ፈርመዋል።
የሁለቱ ተቋማት ስምምነት(Master Service Agreement) የካምቴል ኩባንያ የስራ ኃላፊዎች እ.ኤ.አ በኤፕሪል 2025 በኢትዮጵያ ያደረጉትን ጉብኝት ተከትሎ የተጀመረውና ዕውን የሆነው የትብብር ግንኙነት አካል መሆኑም ተገልጿል።
የካሜሮን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆሴፍ ዲዮን ንጉቴ(ዶ/ር) ኢትዮ ቴሌኮም እና ካምቴል የፈጠሩት ስትራቴጂካዊ አጋርነት አድንቀዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዲጂታላይዜሽን የዘላቂ ልማት ምሰሶ መሆኑን ገልጸው ይህም እውን ሊሆን የሚችለው በአፍሪካ የቴሌኮም ተቋማት መካከል ጠንካራ ትብብር ሲኖር ነው ብለዋል።
በዚህ ረገድም ሁለቱ ተቋማት የወሰዱትን እርምጃ አድንቀዋል።
የካሜሮን መንግስት ለተቋማቱ ስትራቴጂካዊ አጋርነት ስኬታማነት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አመልክተዋል።
ጥምረቱ በኢትዮጵያ ያለው የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን በካሜሮንም እንዲደገም ያደርጋል ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ።
ዲጂታላይዜሽን በማፋጠን አካታች ኢኮኖሚ የመገንባት አቅሙን ሲያጎለብት ኢትዮ ቴሌኮም ‘ቀጣዩ አድማስ፡ ዲጂታልና ከዚያም ባሻገር 2028 ስትራቴጂ’ መሰረት ከአፍሪካዊ ኦፕሬተሮች ጋር በአጋርነት የዲጂታል አፍሪካን ጉዞ ለማፋጠንና ድንበር ተሻጋሪ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል አዲስ ታሪካዊ ምዕራፍ እንደሚከፍት ኢትዮ ቴሌኮም ለኢዜአ በላከው መረጃ አመልክቷል።
አዲስ አበባ፤ መስከረም 1/2019 (ኢዜአ)፦የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ከኃይል ማመንጫነት በላይ ትርጉም ያለው፣ የአፍሪካን የውስጥ...
Sep 14, 2026
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡት ግቦች መሳካት ጉል...
Sep 4, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 10/2018 (ኢዜአ)፡- ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን መቻሉን የአዲስ አበባና የድሬዳዋ አስተዳደር ሥነ...
Aug 17, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 4/2018 (ኢዜአ)፡-በአዳማ ከተማ ከልማት ሥራዎች ጎን ለጎን ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር መሸፈኑን የከተማዋ ግብርና ጽሕ...
Aug 11, 2026