🔇Unmute
ጅማ ፤ ታህሳስ 1/2018(ኢዜአ)፡-የጅማ ከተማ የኮሪደር ልማት ከተማዋን ውብ እና ማራኪ በማድረጉ የጎብኚዎች ቁጥር መጨመሩን የከተማው ቱሪዝም ጽህፈት ቤት ገለጸ።
የኮሪደር ልማት በስፋት ከተካሄደባቸው ከተሞች መካካል ጅማ ተጠቃሽ ስትሆን በከተማው የተሰራው የኮሪደር ልማት ከተማዋን ከማስዋብ ባለፈ በርካታ እድሎች ይዞ የመጣ መሆኑ ተመልክቷል።

ከእድሎቹ መካከል በከተማው የጎብኚዎች ቁጥር እንዲጨምር ማድረግ አንዱ ሲሆን በተለያዩ ዘርፎች የተፈጠረው የስራ እድልም ይጠቀሳል።
የጅማ ከተማ የቱሪዝም ጽህፈት ቤት ሀላፊ ሮዚ ዛኪር እንደተናገሩት፤ በጅማ ከተማ የተከናወነው የኮሪደር ልማት ከተማዋን ለነዋሪ ብቻ ሳይሆን ለጎብኚዎችም ምቹ አድርጓታል።

በኮሪደር ልማት ስራው የአገር ውስጥ እና የውጪ አገር ጎብኚዎች ቁጥር መጨመሩን ጠቅሰው ባለፈው ዓመት ከ1 ሺህ በላይ የውጪ አገር ጎብኚዎች ከተማዋን ጎብኝተዋል ብለዋል።
በተያዘው በጀት ዓመት በርካታ የአገር ውስጥ እና የውጪ ጎብኝዎች ጅማን እየጎበኙ መሆኑን ጠቁመው ጎብኚዎቹ በዋናነት የአባጅፋር ቤተመንግስት እና የቦዬ ሀይቅን እየጎበኙ ነው ብለዋል።

በከተማዋ የኮሪደር ልማት ስራ የጎብኚዎች ቁጥር ከመጨመር ባለፈ ጅማን የኮንፍረንስ ቱሪዝም ማዕከል እንድትሆን እድል እየፈጠረላት መሆኑንም አስረድተዋል።

በከተማዋ በተገነባው የኮሪደር ልማት የጎዳና ላይ ፎቶ የስራ እድል የተፈጠረላቸው የከተማው ወጣቶችም ኮሪደር ልማቱ ገቢ እንደፈጠረላቸውም ተናግረዋል።
ወጣቶቹ በከተማዋ አደባባዮችና ጎዳናዎች በኮሪደር ልማቱ ላይ የእግር ጉዞ የሚያደርጉ ሰዎችን ፎቶ በማንሳት ገቢ እያገኙ ይገኛሉ።

በከተማዋ ኮሪደር ልማት አማካኝነት በተፈጠረላቸው የስራ እድል ደስተኛ መሆናቸውንም ተናግረዋል።
በጅማ ከተማ የኮሪደር ልማቱን ተከትሎ በዋና ዋና መንገድ ዳር የቡና መሸጫ ቤቶች፣ ፈጣን ምግቦች መሸጫ እና የእንጨት ውጤቶች መሸጫ ሱቆች በብዛት ስራ ላይ ይገኛሉ።
አዲስ አበባ፤ መስከረም 1/2019 (ኢዜአ)፦የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ከኃይል ማመንጫነት በላይ ትርጉም ያለው፣ የአፍሪካን የውስጥ...
Sep 14, 2026
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡት ግቦች መሳካት ጉል...
Sep 4, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 10/2018 (ኢዜአ)፡- ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን መቻሉን የአዲስ አበባና የድሬዳዋ አስተዳደር ሥነ...
Aug 17, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 4/2018 (ኢዜአ)፡-በአዳማ ከተማ ከልማት ሥራዎች ጎን ለጎን ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር መሸፈኑን የከተማዋ ግብርና ጽሕ...
Aug 11, 2026