የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የባቡር ሐዲድ

የሌማት ትሩፋት ኢኒሼቲቭ በምግብ ራስን ከመቻል ባለፈ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚ አድርጎናል - አርሶ አደሮች

Dec 11, 2025

IDOPRESS

🔇Unmute

ሚዛን፤ ታህሳስ 2/2018 (ኢዜአ)፡- የሌማት ትሩፋት ኢኒሼቲቭ በምግብ ራስን ከመቻል ባለፈ በኢኮኖሚ ተጠቃሚ እንዳደረጋቸው የቤንች ሸኮ ዞን አርሶ አደሮች ተናገሩ።

አካባቢው ለሌማት ትሩፋት ሥራ ያለውን ምቹ ሁኔታ በመጠቀም የሞዴል መንደሮችን ማስፋፋትና እና ምርታማነትን ማሳደግ ላይ ትኩረት ተደርጎ እየተሠራ መሆኑን የዞኑ ግብርና፣ ደን፣ አካባቢ ጥበቃና ኅብረት ሥራ መምሪያ ገልጿል።

በመደመር መንግስት እይታ ውስጥ ከተቀመጡ በሁለት አሐዝና ከዚያ በላይ የማሳደግ ግቦች መካከል የሌማት ትሩፋት ምርታማነትን ማሳደግ ተጠቃሽ ነው።

ለኢዜአ አስተያየታቸውን የሰጡ የቤንች ሸኮ ዞን አርሶ አደሮች እንዳሉት፤ የሌማት ትሩፋት ኢኒሼቲቭ በምግብ ራስን ከመቻል ባለፈ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚ አድርጎናል።

ኢኒሼቲቩ ከመተግበሩ በፊት ከእርሻ ስራ ውጪ እምብዛም ትኩረት የማይሰጧቸው የማርና ሌሎች የልማት ተግባራት አሁን ላይ ተጠቃሚ እያደረጋቸው መሆኑን ተናግረዋል።

በዞኑ የጊዲ ቤንች ወረዳ አርሶ አደር ኤፌሶን ደረሰ በንብ ማነብ ሥራ ተሰማርተው የማር ምርት በመሸጥ ተጨማሪ ገቢ እያገኙ መሆኑን ተናግረዋል።

ከጎረቤቶቻቸው ጋር በመደራጀት በ20 ቀፎዎች በ2016 ዓ/ም የጀመሩትን ንብ የማነብ ሥራ ወደ 150 ዘመናዊ ቀፎዎች አሳድገው ማር እያመረቱ መሆኑን ገልጸዋል።

በዘንድሮ ዓመት ከ1 ሺህ 500 ኪሎ ግራም በላይ የማር ምርት በተደራጀ መልኩ ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ ማቀዳቸውን ገልጸው የማነብ ሥራውን በእጥፍ ለማሳደግ ተጨማሪ የማር መንደር እያመቻቹ መሆኑንም ጠቁመዋል።

በወረዳው የዓሣ ማርቢያ ኩሬ በማዘጋጀት ዓሣ የማምረት ሥራ እየሠሩ ከሚገኙ አርሶ አደሮች መካከል አቶ ከድር አትርሴ ተጠቃሽ ሲሆኑ በየ3 ወሩ የዓሣ ምርት ለገበያ እንደሚያቀርቡ ተናግረዋል።

የሌማት ትሩፋት ንቅናቄ ከመጀመሩ በፊት የዓሳ ምርት በአካባቢው እንዳልተለመደ ገልጸው ሥራውን በጀመሩ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ከ150 ሺህ ብር በላይ ገቢ ማግኘታቸውን ገልጸዋል።

በሼይ ቤንች ወረዳ የኩሻ ቀበሌ አርሶ አደር ጥላሁን ኪዳኔ ደግሞ በወተት ዘርፍ ተሰማርተው ተጠቃሚ መሆን የቻሉ አርሶ አደር ናቸው።

አርሶ አደሩ ስምንት የተሻሻሉ እና ሁለት የሀገረሰብ ላሞችን በመያዝ ወተት በማምረት ለአካባቢው ማህበረሰብ እያቀረቡ መሆኑን ገልጸዋል።

የወተት ሥራውን ለማስፋፋት ያስችላቸው ዘንድ በሁለት ሄክታር ማሳ ላይ የከብቶች መኖ ሳር መትከላቸውን ተናግረው በሌላ በኩል ዶሮ በማርባት ተጨማሪ የኢኮኖሚ አቅም ለመፍጠር ማቀዳቸውን አክለዋል።

የቤንች ሸኮ ዞን ግብርና፣ ደን፣ አካባቢ ጥበቃና ኅብረት ሥራ መምሪያ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል አሰፋ በዞኑ የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር ተግባራዊ የሚደረግባቸው 502 መንደሮች መደራጀታቸውን ገልጸዋል፡፡

ከእነዚህም 146 የሚሆኑት ሞዴል የሌማት ትሩፋት መንደሮች ሲሆኑ በዞኑ አቅም ተለይተው እየተሠሩ ባሉ የወተት፣ የእንቁላል፣ የማር፣ የዓሣና ቀይ ሥጋ መንደሮች እየተገኘ ባለው ውጤት የዘርፉን ገበያ ማረጋጋት ተችሏል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

ከአፍሪካ አቪዬሽን መሪነት እስከ አህጉራዊ የኢኮኖሚ ትስስር

በሙሴ መለሰ ኢትዮጵያ በአፍሪካ የአቪዬሽን ታሪክ ታይቶ የማይታወቅና በአህጉሪቱ ትልቁ የሆነውን የ12 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ግዙፍ የኤርፖርት ግንባታ ፕሮጀክት...

Apr 24, 2026

በከተሞቹ በትንሳዔ በዓል ገበያ በቂ ምርትና የእርድ እንስሳት ቀርቧል 

ሆሳዕና ፤ ሚያዝያ 2/2018 (ኢዜአ)፦በሆሳእና፣ ወላይታ ሶዶና ቦንጋ ከተሞች በትንሳዔ በዓል ገበያ በቂ የምርትና የእርድ እንስሳት አቅርቦት መኖሩ ተመለከተ። ...

Apr 12, 2026

የጉምሩክ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ የኢትዮጵያን ዓለም አቀፍ የጉምሩክ አገልግሎት በሚያቀላጥፍ መልኩ እየተዘጋጀ ነው

አዲስ አበባ፤መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፦የጉምሩክ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ የኢትዮጵያን ዓለም አቀፍ የጉምሩክ አገልግሎት በሚያቀላጥፍ መልኩ እየተዘጋጀ መሆኑን በሕ...

Apr 9, 2026

የማዕከል ወደ ሥራ መግባት በክልሉ የሚገኘውን ሰፊ የእንስሳት ሀብት ወደ ላቀ የኢኮኖሚ ጥቅም ለመለወጥ ያስችላል

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 22/2018 (ኢዜአ)፦ የአፋር ሰመራ ሁለተኛ ደረጃ የቁም እንስሳት ግብይት ማዕከል ወደ ሥራ መግባቱ በክልሉ የሚገኘውን ሰፊ የእንስሳት ሀ...

Apr 1, 2026