🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ጥር 7/2018(ኢዜአ)፦የመጀመሪያው እና ሁለተኛው የሃገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች ጠንካራ እና አዳዲስ ተቋማት እንዲፈጠሩ አስችሏል ሲሉየገንዘብ ሚኒስትርአህመድ ሺዴ ገለጹ፡፡
ከሰባት ዓመት በፊት በኢትዮጵያ የነበረው የማክሮ ኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ከፍተኛ ስብራት ውስጥ የነበረ ነው ያሉት ሚኒስትሩ የማክሮ ኢኮኖሚ መዛባት፣ የእዳ ጫና፣ የውጭ ምንዛሬ እጥረት እና የገበያ አለመረጋጋት ከለውጡ በፊት የነበሩ የማክሮ ኢኮኖሚው ዋና ስብራቶች ሆነው ቆይተዋል ብለዋል።
መንግሥት እነዚህን ስብራቶች ለመለወጥ በወሰዳቸው የለውጥ ተግባራት አሁን ላይ ውጤቶች እየተመዘገቡ ይገኛሉ ሲሉም ተናግረዋል።
ይህም ለውጥ ኢትዮጵያ በአፍሪካ በፍጥነት እያደጉ ካሉ ሃገራት መካከል እንድትሆን እንዳስቻላት ገልጸዋል።
የመጀመሪያው እና ሁለተኛው የሃገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች ጠንካራ እና አዳዲስ ተቋማት እንዲፈጠሩ አስችሏል ያሉት ሚኒስትሩ ለውጡ ካመጣቸው ውጤቶች መካከል የመንግስት ገቢን ለማሳደግ የሚያግዙ ጠንካራ፣ አዳዲስ እና ቀልጣፋ ስትራቴጂዎች እንዲነደፉ አድርጓል ብለዋል።
ከለውጡ በኋላ የመንግስት ገቢ የውጭ ፍሰትን ጨምሮ በአምስት እጥፍ አድጓል፤የመንግስት የታክስ ገቢ በ400 % ጨምሯል ነው ያሉት።
የመንግስት ጠቅላላ ገቢ በ2010 ዓ.ም ከነበረበት ዛሬ ላይ 446 በመቶ ጨምሯል ብለዋል። ከውጭ ሃብት ፍሰትም ባለፉት ሰባት ዓመታት በአጠቃላይ 25 ቢሊየን ዶላር ማግኘት ያስቻለ ውጤት የተመዘገበበት ነው ሲሉም ተናግረዋል።
በድህነት ተኮር ዘርፎች የዋለው በጀት በ2010 ከነበረበት በአራት እጥፍ ያደገ መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሩ የበጀት ጉድለትን በተመለከተ በ2010 ዓ.ም ከነበረበት 2.5 በመቶ በ2017 ወደ 0.9 በመቶ መቀነስ ተችሏል ማለታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡
አዲስ አበባ፤ መስከረም 1/2019 (ኢዜአ)፦የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ከኃይል ማመንጫነት በላይ ትርጉም ያለው፣ የአፍሪካን የውስጥ...
Sep 14, 2026
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡት ግቦች መሳካት ጉል...
Sep 4, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 10/2018 (ኢዜአ)፡- ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን መቻሉን የአዲስ አበባና የድሬዳዋ አስተዳደር ሥነ...
Aug 17, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 4/2018 (ኢዜአ)፡-በአዳማ ከተማ ከልማት ሥራዎች ጎን ለጎን ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር መሸፈኑን የከተማዋ ግብርና ጽሕ...
Aug 11, 2026