🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ጥር 8/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ አስደናቂ ኅብረ-ባህል፣ ነባርና አዳዲስ የመስኅብ ስፍራዎችን የታደለች ውብ ሀገር ናት ሲሉ የውጭ ሀገራት ጎብኚዎች ተናገሩ።
ኢዜአ ያነጋገራቸው የውጭ ሀገራት ጎብኚዎች እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ የጎብኚዎችን ቀልብ የሚስቡ ታሪካዊ፣ ባህላዊና ተፈጥሯዊ መዳረሻዎች ያሏት ሀገር ናት፡፡

የኢትዮጵያን እምቅ ባህል፣ ታሪክ፣ ቅርስና የተፈጥሮ መስኅብ እንዲሁም ውብ የሆኑ አዳዲስ የመስኅብ ስፍራዎችን መጎብኘታቸውን ገልጸዋል።
ለጤና ተስማሚ የሆነና ሁሉንም ሥርዓተ-ምኅዳር የሚያካትት የተለየ የአየር ጸባይ የታደለች ውብ ሀገር መሆኗንም ጠቅሰዋል፡፡

አዲስ አበባ ከዚህ በፊት ከተመለከቷቸው በርካታ የዓለም ከተሞች በልዩነት ውብ ሆና እንዳገኟት ከቤልጂየም የመጡት ጎብኚ ቴር ጊለር ተናግረዋል።
ከተማዋ ፅዱ፣ ነፋሻማ፣ አረንጓዴ እና ለጎብኚዎች ታሪክን የሚያስረዱ በርካታ መዳረሻዎች መያዟ ቀልባቸውን በእጅጉ እንደገዛውም አንስተዋል።

ብሔራዊ ሙዝዬምንና እንጦጦ ፓርክን ጨምሮ የተለያዩ መዳረሻዎችና ፓርኮችን መጎብኘታቸውን ገልጸው፤ በዚህም እጅግ ደስተኛ መሆናቸውን ነው የተናገሩት።

ከጀርመን የመጡት ሉካስ ኩፐንሃገል በበኩላቸው፤ በኢትዮጵያ ከተመለከቷቸው የቱሪዝም መዳረሻዎች በተጨማሪም በሀገሪቱ ኅብረ-ብሔራዊ ዕሴቶች መደነቃቸውን ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ በታሪካዊ፣ ተፈጥሯዊና ሰው ሠራሽ መስኅቦች የደመቀች ሀገር መሆኗንም ዐይቻለሁ ብለዋል።

በኢትዮጵያ ነባር መዳረሻዎችን መልሶ የማልማትና አዳዲስ አስደናቂ የመስኅብ ቦታዎች መገንባታቸው የጎብኚዎች ቁጥር እንዲጨምር ማስቻሉን የተናገሩት ደግሞ የታላቁ ኢትዮጵያ አስጎብኚ ድርጅቶች ማኅበር ምክትል ፕሬዚዳንት እንቁ ሙሉጌታ ናቸው።
ኢትዮጵያ የብዝኃ-ባህል፣ ታሪክ እና የበርካታ መዳረሻዎች መገኛ መሆኗ በዘርፉ ለተሰማሩ ባለድርሻ አካላት ትልቅ ዕድል መፍጠሩንም ጠቁመዋል።

የቱሪዝም ሚኒስትር ዴዔታ ስለሺ ግርማ በበኩላቸው፤ የገበታ ለሀገር ፕሮጀክቶች ለቱሪዝም ዕድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ከማበርከታቸው በላይ የሀገርን ገጽታ የቀየሩና የግሉ ዘርፍ እንዲበረታታ በር የከፈቱ ድንቅ ሥራዎች ናቸው ብለዋል፡፡
መዳረሻዎቹ የጎብኚ ቁጥር እንዲጨምር እና የቆይታ ጊዜያቸውን እንዲያራዝሙ በማድረግ ከፍተኛ የሆነ ምጣኔ ሃብታዊ፣ ማኅበራዊና፣ ዲፕሎማሲያዊ ጠቀሜታ እያስገኙ መሆኑንም አስገንዝበዋል።
አዲስ አበባ፤ መስከረም 1/2019 (ኢዜአ)፦የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ከኃይል ማመንጫነት በላይ ትርጉም ያለው፣ የአፍሪካን የውስጥ...
Sep 14, 2026
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡት ግቦች መሳካት ጉል...
Sep 4, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 10/2018 (ኢዜአ)፡- ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን መቻሉን የአዲስ አበባና የድሬዳዋ አስተዳደር ሥነ...
Aug 17, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 4/2018 (ኢዜአ)፡-በአዳማ ከተማ ከልማት ሥራዎች ጎን ለጎን ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር መሸፈኑን የከተማዋ ግብርና ጽሕ...
Aug 11, 2026