የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የባቡር ሐዲድ

በአማራ ክልል በመኸር ወቅት ከለማው ሰብል 138 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ተሰብስቧል   

Jan 16, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ባህር ዳር፤ ጥር 8/2018 (ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በመኸር ወቅቱ ከለማው ሰብል እስካሁን ድረስ 138 ሚሊዮን ኩንታል ምርት መሰብሰቡን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ።

የቢሮው የሰብል ልማትና ጥበቃ ዳይሬክተር ማንደፍሮ አስላከ (ዶ/ር) ለኢዜአ እንደገለጹት፤ በ2017/2018 የምርት ዘመን በክልሉ 5 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በተለያዩ ሰብሎች ማልማት ተችሏል።

በመኸር ወቅቱ ከለማው ሰብል ከ187 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለማግኘት መታቀዱንም አስታውቀዋል።


እስካሁንም በ4 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ላይ የደረሰ ሰብል የምርት ብክነትን በቀነሰ መልኩ በቴክኖሎጂና በሰው ጉልበት ታግዞ ለመሰብሰብ መቻሉን ተናግረዋል።

ከተሰበሰበው ሰብልም 138 ሚሊዮን ኩንታል የገብስ፣ የስንዴ፣ የጤፍ፣የበቆሎ፤ የቅባትና የጥራጥሬ ምርት መገኘቱን አመልክተዋል።

በምርት አሰባሰቡ 76 ኮምባይነሮችና በ517 ሁለገብ የሰብል መውቂያና የበቆሎ መፈልፈያ ማሽኖች ጥቅም ላይ መዋላቸውን ነው የገለጹት።

‎በምስራቅ ጎጃም ዞን የደብረኤልያስ ወረዳ ነዋሪ አርሶ አደር አባትሁን ስራው እንዳሉት፤ በሦስት ሄክታር ተኩል መሬት ላይ ያለሙትን የስንዴ፣ የበቆሎና የጤፍ ስብል በኮምባይነርና በሰው ጉልበት ታግዘው ሰብስበዋል።


‎‎የስንዴና የጤፍ ሰብላቸውን ወቅተው የተሻለ ምርት ወደጎተራ እንዳስገቡ ጠቅሰው፣ የበቆሎ ሰብላቸውን ደግሞ በማሽን ታግዘው እየፈለፈሉ መሆናቸውን ተናግረዋል።

‎በሦስት ሄክታር መሬት ላይ ያለሙትን የስንዴ፣ የቢራ ገብስና የባቄላ ሰብል መሰብሰባቸውን የገለጹት ደግሞ በደቡብ ጎንደር ዞን የእስቴ ወረዳ አርሶ አደር ብርሃን ይመር ናቸው።

‎ሰብሉን በሰው ጉልበት በመውቃት ወደጎተራ እያስገቡ መሆናቸውን ገልጸዋል።


በአማራ ክልል በ2016/2017 የመኸር ወቅት በክልሉ ከለማው 5 ነጥብ 4 ሚሊዮን ሄክታር መሬት 170 ሚሊዮን ኩንታል ምርት መገኘቱን ከቢሮው የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የአፍሪካ የልማትና ትብብር ዓርማ - ታላቁ የሕዳሴ ግድብ በታዋቂው ታይም መጽሔት ገጽ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 1/2019 (ኢዜአ)፦የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ከኃይል ማመንጫነት በላይ ትርጉም ያለው፣ የአፍሪካን የውስጥ...

Sep 14, 2026

በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡ ግቦች መሳካት ጉልህ አስተዋጽኦ አለው-ዋምኬሌ ሜኔ

አዲስ አበባ፤ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡት ግቦች መሳካት ጉል...

Sep 4, 2026

ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን ተችሏል

አዳማ፤ ነሐሴ 10/2018 (ኢዜአ)፡- ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን መቻሉን የአዲስ አበባና የድሬዳዋ አስተዳደር ሥነ...

Aug 17, 2026

በአዳማ ከተማ ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር ተሸፍኗል

አዳማ፤ ነሐሴ 4/2018 (ኢዜአ)፡-በአዳማ ከተማ ከልማት ሥራዎች ጎን ለጎን ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር መሸፈኑን የከተማዋ ግብርና ጽሕ...

Aug 11, 2026