🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ጥር 9/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የቴክኖሎጂ ፈጠራ በወሳኝ ጥቂት የሕክምና ዘርፎች የሚታየውን የሰው ሃይል እጥረት ለመሙላት ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው የቢግ ዊን ፊላንትሮፒ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር ከሰተብርሃን አድማሱ ገለፁ።
የቢግ ዊን ፊላንትሮፒ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር ከሰተብርሃን አድማሱ በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ጉብኝት አድርገዋል።

ዋና ሥራ አስፈጻሚው በጉብኝታቸው በኢንስቲትዩቱ እየተከናወኑ ያሉ የቴክኖሎጂ ፈጠራዎችና ተግባራዊ እንቅስቃሴዎች አስደናቂ መሆናቸውን መመልከታቸውን ገልጸዋል።
በተለይም በጤናው ዘርፍ ለተግባራዊ አገልግሎት የሚውሉ የቴክኖሎጂ መፍትሄዎች ላይ እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎች አበረታች ናቸው ብለዋል።

የጤና እና የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ባለሙያዎች በቅንጅት መስራት የሚቻልበት ሁኔታ መኖሩ ከፍተኛ ደስታ እንደፈጠረባቸው ገልፀዋል።
ይህም በሀገሪቱ የሰው ኃይል እጥረት ባለባቸው የሕክምና ዘርፎች ላይ የሚታየውን ክፍተት ለመሙላት ትልቅ ሚና እንደሚጫወት ጠቁመዋል።
በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ቴክኖሎጂ ሰፊ ዓለም አቀፍ የትብብር ዕድሎች መኖራቸውን ዶክተር ከሰተብርሃን ጠቁመዋል፡፡
በቦርድ አባልነት የሚያገለግሉበት ሴፒ የተሰኘው ዓለም አቀፍ ድርጅት ወረርሽኝ ሊያስከትሉ የሚችሉ ቫይረሶችን ቀድሞ በመለየት በ100 ቀናት ውስጥ ክትባቶችን ለማምረት እየሰራ እንደሚገኝ አስረድተዋል።
ተቋሙ በአፍሪካ ውስጥ አብረውት ሊሰሩ የሚችሉ ማዕከሎችን በመፈለግ ላይ መሆኑን ጠቅሰው፤ ጉብኝታቸው በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት እና በሴፒ መካከል ጠንካራ የሥራ ግንኙነት ለመፍጠር ዕድል እንደሚኖረው ገልጸዋል።
ይህም የኢትዮጵያ የጤና ምርምር ተቋማት ሴፒ የሚያዘጋጃቸውን የኤ አይ ኢንጂኖች (AI Engines) በስፋት መጠቀም የሚችሉበትን መንገድ እንደሚያመቻች አመልክተዋል።
አዲስ አበባ፤ መስከረም 1/2019 (ኢዜአ)፦የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ከኃይል ማመንጫነት በላይ ትርጉም ያለው፣ የአፍሪካን የውስጥ...
Sep 14, 2026
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡት ግቦች መሳካት ጉል...
Sep 4, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 10/2018 (ኢዜአ)፡- ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን መቻሉን የአዲስ አበባና የድሬዳዋ አስተዳደር ሥነ...
Aug 17, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 4/2018 (ኢዜአ)፡-በአዳማ ከተማ ከልማት ሥራዎች ጎን ለጎን ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር መሸፈኑን የከተማዋ ግብርና ጽሕ...
Aug 11, 2026