🔇Unmute
ሐረማያ ፤ጥር 14/2018 (ኢዜአ) ፡-በሐረሪ ክልል፣ ምስራቅ ሐረርጌ ዞንና ማያ ከተማ አስተዳደር ከ11ሺህ በላይ ከሆኑ የኢኮኖሚ ድርጅቶች መረጃ የመሰብሰብ ስራ ይከናወናል።
በኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት የሐረር ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የኢኮኖሚ ድርጅቶች ቆጠራ ለሚያከናውኑ የመስኩ ባለሙያዎች ስልጠና እየሰጠ ነው።
በአገልግሎቱ የሐረር ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ ሙክታር ጀማል እንደገለጹት ስልጠናው ከሐረሪ ክልል፣ ምስራቅ ሐረርጌ ዞንና ማያ ከተማ አስተዳደር ለተውጣጡ 625 መረጃ ሰብሳቢዎች፣ ተቆጣጣሪዎች እና አስተባባሪዎች እየተሰጠ ነው።

በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ ለ10 ቀናት በሚሰጠው በዚሁ ስልጠና በሶስት የተለያዩ ክፍሎች ላይ ያተኮረ ሙያዊ ስልጠና እንደሚሰጥ ጠቁመዋል።
በዚህም በሐረሪ ክልል፣ ምስራቅ ሐረርጌ ዞንና ማያ ከተማ አስተዳደር ከተመረጡ 11ሺህ 567 የኢኮኖሚ ድርጅቶች የሰው ሃይላቸውን፣ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴያቸውንና ወጪና ገቢያቸውን ጨምሮ ሌሎችም መረጃዎች ይሰበሰባሉ ብለዋል።
እንደ አቶ ሙክታር ገለጻ ከጥር 25 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ዋናው የመረጃ መሰብሰብ ስራ እንደሚገባም አክለዋል።
የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ዘርፈ ብዙና የተለያዩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥናቶችን በማከናወን መረጃዎችን በመሰብሰብ ይተነትናል ያሉት ደግሞ የስልጠናው ዋና አስተባባሪ አቶ እንዳሻው ፈለቀ ናቸው።

ስልጠናው የኢኮኖሚ ድርጅቶችን መረጃ ለመሰብሰብ የሚያስችሉ ግንዛቤን ለቆጣሪዎች በመስጠት ስራውን ለማሳካት ያለመ ነው ብለዋል።
የኢኮኖሚ ድርጅቶች ቆጠራም የአገራችንን የኢኮኖሚ ሃብት ደረጃ ለማወቅ እንዲሁም ድርጅቶች ያላቸውን የሰው ሃይልና ሌሎች መረጃዎቻቸውን ለመለየትና ለጥናትና ምርምር፣ ለፖሊሲ ዝግጅት በማዋል ዘርፈ ብዙ ጥቅም አለው ብለዋል።

ስልጠናውን እየተከታተሉ ከሚገኙት መካከል ማዓዛ ሀብታሙ እንደገለጸችው ስልጠናው የጠራ መረጃ በመሰብሰብ ለአገራዊ እድገት መሰረት እንዲጣል የሚያግዝ ነው ብላለች።
ስልጠናው በኢኮኖሚው ዘርፍ የተመዘገበውን ስኬት ለማስቀጠል ፋይዳው የጎላ ነው ያለው ደግሞ ሌላው ሰልጣኝ ሸምሸዲን አብዶ ነው።

አዲስ አበባ፤ መስከረም 1/2019 (ኢዜአ)፦የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ከኃይል ማመንጫነት በላይ ትርጉም ያለው፣ የአፍሪካን የውስጥ...
Sep 14, 2026
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡት ግቦች መሳካት ጉል...
Sep 4, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 10/2018 (ኢዜአ)፡- ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን መቻሉን የአዲስ አበባና የድሬዳዋ አስተዳደር ሥነ...
Aug 17, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 4/2018 (ኢዜአ)፡-በአዳማ ከተማ ከልማት ሥራዎች ጎን ለጎን ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር መሸፈኑን የከተማዋ ግብርና ጽሕ...
Aug 11, 2026