🔇Unmute
ጋምቤላ ፤ የካቲት 23/2018(ኢዜአ)፦ኢትዮጵያውያን በዓድዋ ያሳዩትን አኩሪ ገድል የዘመኑ ትውልድ በልማቱ ሊደግመው ይገባል ሲሉ የጋምቤላ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ጋትሉዋክ ሮን (ዶ/ር) ገለጹ።
የዓድዋን ድል ስናከብር የተሰጠንን ሀገራዊ ተልእኮ በላቀ ብቃትና ዝግጁነት ለመወጣት ዳግም ቃል በመግባት ነው
’’ከአኩሪ ታሪክ ወደ ብሩህ አድማስ’’ በሚል መሪ ሃሳብ 130ኛው የዓድዋ ድል በዓል በጋምቤላ ከተማ ተከብሯል።
ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ በክብረ በዓሉ ላይ እንዳሉት፤ ቀደምት አባቶች በአንድነትና በህብረት በዓድዋ ያሳዩት ድል ለኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካውያን ጭምር ታላቅ የነፃነት ቀንዲል ነው።

በዘመኑ ኢትዮጵያውያን ለዓድዋ ታሪካዊ ድል የበቁት በአንድነትና በህብረት በመታገላቸው መሆኑን ተናግረዋል።
በመሆኑም የዘመኑ ትውልድ የአባቶቹን የአብሮነት፣ የአንድነትና የትብብር እሴት በማጎልበት በክልሉ ብሎም በሀገሪቱ የታለሙትን የልማት ግቦች ለማሳካት በቁርጠኝነት ሊሰራ ይገባል ብለዋል።
የዘንድሮው የዓድዋ ድል በዓል በርካታ የልማት ጅምሮችና ስኬቶች እየተመዘገቡ ባሉበት ወቅት መከበሩ ልዩ ትርጉም ያለው መሆኑን ገልጸዋል።
የጋምቤላ ከተማ ከንቲባ አቶ ቱት ጆክ በበኩላቸው፤ የዓድዋ ድል ኢትዮጵያውያን የሀገራቸውን ሉዓላዊነት ላለማስደፈር ጽናታቸውና አይበገሬነታቸውን ለዓለም ማህበረሰብ ያሳዩበት ታሪካዊ ቀን ነው ብለዋል።
በመሆኑም የዓድዋ ድል ለእኛ ለኢትዮጵያዊያን የአሸናፊነትና የጥንካሬያችን ማሳያ ታሪካዊ የድል በዓል ነው ሲሉ ገልጸዋል።

በክብረ በዓሉ ላይ የታደሙት የጸጥታ አካላት በሰጡት አስተያየት፤ በጀግኞች አባቶች ተከብራና ታፍራ የቆየችው ኢትዮጵያ ዛሬም በእኛ በልጆቿ ክብሯና ሉዓላዊነቷ ጸንቶ ይቀጥላል ብለዋል።
የዓድዋ ድል ለዘመኑ ትውልድ ጽናትን፣ አንድነትን፣ ህብረትንና አልሸነፍ ባይነትን ያወረሰ ታሪካዊ የድል ቀን መሆኑን የጸጥታ አካላቱ ገልጸዋል።
በክብረ በዓሉ ላይ የጋምቤላ ከተማ ነዋሪዎች፣ የመንግስት ሰራተኞችና ሌሎችም የህብረተሰብ ክፍሎች የታደሙ ሲሆን የክልልና የፌዴራል የጸጥታ አካላት የሰልፍ ትርኢት አሳይተዋል።
አዲስ አበባ፤ መስከረም 1/2019 (ኢዜአ)፦የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ከኃይል ማመንጫነት በላይ ትርጉም ያለው፣ የአፍሪካን የውስጥ...
Sep 14, 2026
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡት ግቦች መሳካት ጉል...
Sep 4, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 10/2018 (ኢዜአ)፡- ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን መቻሉን የአዲስ አበባና የድሬዳዋ አስተዳደር ሥነ...
Aug 17, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 4/2018 (ኢዜአ)፡-በአዳማ ከተማ ከልማት ሥራዎች ጎን ለጎን ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር መሸፈኑን የከተማዋ ግብርና ጽሕ...
Aug 11, 2026