🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 16/2018 (ኢዜአ)፦ መንግስት በኢትዮጵያ በሁሉም መስክ አስተማማኝ መሰረት እንደሚጥል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከተማ፣ ከተሜነት፣ ክትመት እና የኮሪደር ልማት በሚል መሪ ሐሳብ ከቃና ቲቪ ጋር ቆይታ አድርገዋል።
በቆይታቸውም የከተማ ፕላን፣ የዘላቂ ልማት እና የኮሪደር ልማት ፕሮጀክቶች አዲስ አበባንና ሌሎች ከተሞችን እንዴት እየቀየሩ እንደሆነ፤ እንዲሁም የመሠረተ ልማትን፣ የንግድና የኢኮኖሚ ዕድሎችን በመላው ሀገሪቱ ለማሳደግ ያላቸው ፋይዳ በጥልቀት ተዳሷል።
ኢትዮጵያ ውብ፣ ታላቅና በስልጣኔ ቀደምት የሆነች ሀገር ናት ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአፍሪካ የራሷ አቆጣጠር ያላት፣ በአፍሪካ ቅኝ ያልተገዛች ብቸኛ ሀገር፣ የሰው ልጅ መገኛ ቡናን ለዓለም የሰጠች ሀገር መሆኗንም አውስተዋል።
ይህም ኢትዮጵያ ተቀባይ ብቻ ሳትሆን ለዓለም አስተዋጽኦ ማድረግ የሚያስችል ብቃት ያለው ህዝብ እንዳላት የሚያመላክት እንደሆነም ተናግረዋል።
ኢትዮጵያን ከአጭር ጊዜ ይልቅ አርቆ በማየትና በማሰብ በትብብር ከገነባን ለብዙዎች ብርቅ ለብዙዎች መጠለያ ለብዙዎች መሸሸጊያ የምትሆን ሀገር መፍጠር ይቻላል ነው ያሉት።
ከ1 ነጥብ 3 ሚሊየን በላይ ፍልሰተኞችን ተቀብላ ማስተናገዷን ጠቅሰው ሀገርን በወግ እና በስርዓት መገንባት ከተቻለ ከኢትዮጵያ አልፎ ለሌሎች የሚተርፍ አድርጎ መስራት እንደሚቻል አመልክተዋል።
የሰው ልጅ የተሰጠው ጊዜ ውስን ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተሰጠን ጊዜ በተገቢው ሁኔታ መስራትና ለልጆች የሚታወስና የሚጠቅም ነገር ማድረግ አለብን ብለዋል።
በኢትዮጵያ በሁሉም መስክ አስተማማኝ መሰረት ጥለን እናልፋለን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፖለቲካውም በኢኮኖሚውም በዲፕሎማሲውም በወታደራዊ አቅሙም ለትውልድ አስቻይ የሆነ መሰረት ጥለን እንደምናልፍ ተስፋ አለኝ ብለዋል።
ይሄ ነገር እንዳይሳካ የሚያደናቅፉ ኃይሎች ሊኖሩ ቢችሉም እኛ እንቅፋቶቻችንን ከመንገዶቻችን እያስወገድን ያሰብነውን ለማሳካት በተሰጠን ጊዜ ቀንና ለሊት እንተጋለን ልጆቻችን ያስቀጥሉታል ነው ያሉት።
ኢትዮጵያ ድንቅ መሆኗን ታሪክ ጠገብ መሆኗን ሀብታም መሆኗን በንግግር ሳይሆን በተግባር ገልጠን የምናሳይበት ጊዜ አሁን ነው ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።
ኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እድገት እና የግዙፍ መሰረተ ልማት ግንባታዎችን ጨምሮ በተለያዩ መስኮች በስኬትና በለውጥ ላይ የምትገኝበት ወቅት መሆኑንም ገልጸዋል።
የተጀመረው ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተግተን ከሰራን የወደፊቷ ያማረ እና የበለጸገች ኢትዮጵያን መፍጠር እንደሚቻል ተናግረዋል።
አዲስ አበባ፤ መስከረም 1/2019 (ኢዜአ)፦የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ከኃይል ማመንጫነት በላይ ትርጉም ያለው፣ የአፍሪካን የውስጥ...
Sep 14, 2026
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡት ግቦች መሳካት ጉል...
Sep 4, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 10/2018 (ኢዜአ)፡- ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን መቻሉን የአዲስ አበባና የድሬዳዋ አስተዳደር ሥነ...
Aug 17, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 4/2018 (ኢዜአ)፡-በአዳማ ከተማ ከልማት ሥራዎች ጎን ለጎን ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር መሸፈኑን የከተማዋ ግብርና ጽሕ...
Aug 11, 2026