🔇Unmute
አዲስ አበባ፤መጋቢት 15/2018(ኢዜአ)፦መንግስት የዜጎችን ህይወት በሚቀይር መልኩ የመሰረተ ልማት ግንባታ ስራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) "ከተማ፣ ከተሜነት፣ ክትመት እና የኮሪደር ልማት በሚል መሪ ሐሳብ ከቃና ቲቪ ጋር ቆይታ አድርገዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ መንግስታት የመሰረተ ልማት ግንባታን ለገበያ ከመስጠት ይልቅ በዘርፉ መዋዕለ ንዋይ የማፍሰሳቸው ተገቢነትን በተመለከተ በሰጡት ማብራርያ፤ በዓለም ላይ መንግስት ሳይገባበት የተገነባ መሰረተ ልማት አለመኖሩን ተናግረዋል፡፡
ሀገራት መሰረተ ልማቶች ከተገነቡና የማህበረሰብ እውቀትና ሀብት ከሆኑ በኃላ ገንዘብ እንዲያመጡ ወደ ግል ማሸጋገር እንደሚፈልጉም አንስተዋል፡፡
ለዚህም ከዛሬ 50 ዓመት በፊት የግል ሳተላይት የሚያመጥቅ እንዳልነበረ እና አሁን ላይ ከሀገራት ባለፈ ግለሰቦችና ኩባንያዎች ጭምር እንደሚያመጥቁ ለአብነት አውስተዋል፡፡
በኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች ከፍተኛ መዋዕለንዋይ የሚፈልጉ በመሆኑ ለባለሀብት መስጠት አዳጋች መሆኑንና ነገር ግን ወደፊት ሊሆን እንደሚችል ተናግረዋል፡፡
በዘርፉ መንግስት መሳተፉ ለኢኮኖሚው ሞተር በመሆኑ የዜጎችን ህይወት በሚቀይር መልኩ ወደፊትም በሰፊው መሳተፉ የሚቀር እንዳልሆነም ጠቁመዋል፡
ይህም የገቢ አቅምን ለመጨመር፤ኢኮኖሚያዊ ፍትሃዊነትን እንዲሁም የኑሮ ጥራትን ለማረጋገጥ ያግዛል ብለዋል፡፡
ወደፊትም ማህበረሰቡን በብዙ መልኩ የሚጠቅም በመሆኑ መንግስት የመሰረተ ልማት ግንባታ ስራን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል፡፡
አዲስ አበባ፤ መስከረም 1/2019 (ኢዜአ)፦የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ከኃይል ማመንጫነት በላይ ትርጉም ያለው፣ የአፍሪካን የውስጥ...
Sep 14, 2026
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡት ግቦች መሳካት ጉል...
Sep 4, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 10/2018 (ኢዜአ)፡- ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን መቻሉን የአዲስ አበባና የድሬዳዋ አስተዳደር ሥነ...
Aug 17, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 4/2018 (ኢዜአ)፡-በአዳማ ከተማ ከልማት ሥራዎች ጎን ለጎን ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር መሸፈኑን የከተማዋ ግብርና ጽሕ...
Aug 11, 2026