🔇Unmute
ጅማ፤ መጋቢት 22/2018(ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል በለውጡ ዓመታት የተመዘገቡ ስኬታማ የልማት ስራዎች ቀጣይነት እንዲኖራቸው ምሁራን ድርሻቸውን ማጠናከር እንዳለባቸው ተመለከተ።
በጅማ ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው ውይይት የኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ምሁራን እየተሳተፉ ነው።

በብልፅግና ፓርቲ የኦሮሚያ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ነመራ ቡሊ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፤ በክልሉ ባለፉት የለውጥ ዓመታት ሁሉን አቀፍ የልማት ስኬቶች ተመዝግበዋል።
በተለይም በግብርና፣ በትምህርት እና በጤና ዘርፎች የተከናወኑ የልማት ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት በተሻለ መልኩ ያሳደጉ መሆናቸውን ተናግረዋል።
በክልሉ ከትምህርት ጥራት ጋር የተያያዙ ችግሮችን በዘላቂነት ለመቅረፍ የቡዑረ ቦሩ የቅድመ-መደበኛ ትምህርት ቤቶች በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች በስፋት መገንባታቸውን አስታውሰዋል።
ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር የተያያዙ ችግሮችን ለመቅረፍም መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን የማስፋፋትና የዲጂታል አገልግሎትን ተደራሽ የማድረግ ስራ ውጤታማ እንደሆነ አመልክተዋል።
እነዚህ የተመዘገቡ ስኬታማ ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ምሁራን በጥናትና ምርምር የማገዝ ሚናቸውን ሊያጠናክሩ እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

በመድረኩ የውይይት መነሻ ጽሁፍ ያቀረቡት የክልሉ መንግሥት ፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አብዱላዚዝ ዳውድ(ዶ/ር)፤ በክልሉ ሲተገበሩ የቆዩ ሰው ተኮር የልማት ስራዎች ውጤት እያስመዘገቡ መሆኑን ገልጸዋል።
በተለይም ባለፉት የለውጥ ዓመታት የተተገበሩ አዳዲስ የግብርና ልማት ኢኒሼቲቮች የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጉዞ ያጠናከሩ መሆናቸውን ተናግረዋል።
በ2010 ዓ.ም በ1 ነጥብ 9 ሚሊየን ሄክታር መሬት ላይ ብቻ ይለማ የነበረው የስንዴ ምርት፣ አሁን ላይ የመስኖ ልማትን በማስፋፋት ወደ 6 ነጥብ 3 ሚሊየን ሄክታር ማሳደግ መቻሉን ለአብነት አንስተዋል።
ይህ ስኬት የተገኘውም በዓመት ሁለት ጊዜና ከዚያ በላይ ማምረት በመቻሉ መሆኑን ገልጸው፤ ለመጪው ትውልድ የተሻለ ኢኮኖሚ ለማውረስ ሁሉም በጋራ መረባረብ አለበት ብለዋል።
አዲስ አበባ፤ መስከረም 1/2019 (ኢዜአ)፦የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ከኃይል ማመንጫነት በላይ ትርጉም ያለው፣ የአፍሪካን የውስጥ...
Sep 14, 2026
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡት ግቦች መሳካት ጉል...
Sep 4, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 10/2018 (ኢዜአ)፡- ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን መቻሉን የአዲስ አበባና የድሬዳዋ አስተዳደር ሥነ...
Aug 17, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 4/2018 (ኢዜአ)፡-በአዳማ ከተማ ከልማት ሥራዎች ጎን ለጎን ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር መሸፈኑን የከተማዋ ግብርና ጽሕ...
Aug 11, 2026