🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 24/2018(ኢዜአ)፦በዘንድሮው የመኸር እርሻ 21 ነጥብ 8 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በዘር ለመሸፈን መታቀዱን የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ መለስ መኮንን (ዶ/ር) ገለጹ።
የግብርና ሚኒስቴር የ2018/19 የመኸርና የበልግ ወቅት የሰብል ልማት ንቅናቄን በተመለከተ መግለጫ ሰጥቷል።
የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ መለስ መኮንን (ዶ/ር) በመግለጫቸው እንደገለጹት፤ በኢትዮጵያ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የመኸር፣ የበልግና የበጋ መስኖ ልማት ስራዎች በተቀናጀ መልኩ እየተከናወኑ ይገኛሉ።
"ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የምግብ ሉዓላዊነት በሀገር ደረጃ ማረጋገጥ" በሚል መሪ ሀሳብ የሰብል ምርትን በመሬት ሽፋንና በምርታማነት ማሳደግ የሚያስችል እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ ለግብርና ስራ ምቹ የሆነ የሰብል ልማት ስነ-ምህዳር ያላት በመሆኑ፣ በክልሎች የሚገኙ ጸጋዎችን በመለየት ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ የሚያስችል ዕቅድ ተዘጋጅቶ ወደ ስራ መገባቱን ገልጸዋል።
ከ2011/12 የምርት ዘመን ጀምሮ በመኸር፣ በበልግ እንዲሁም በስንዴ ልማትና በሌሎች ምርቶች የሚታረስ መሬት በመጠንም ሆነ ከሄክታር የሚገኘው ምርት በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን ተናግረዋል፡፡
ለአብነትም በ2011 ዓ.ም በ3 ሺህ 500 ሄክታር መሬት ላይ የተጀመረው የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ዘንድሮ 4 ነጥብ 2 ሚሊዮን ሄክታር መድረሱን ገልጸዋል፡፡
በዚህም መጀመሪያ ላይ ይገኝ የነበረው 100 ሺህ ኩንታል ምርት፣ በዘንድሮው ዓመት ወደ 175 ሚሊዮን ኩንታል ከፍ ማለቱን ተናግረዋል፡፡
የመኸር ስንዴ ልማት በ2011 ዓ.ም ከነበረው 1 ነጥብ 75 ሚሊዮን ሄክታር ሽፋን በአሁኑ ወቅት ወደ 4 ነጥብ 4 ሚሊዮን ሄክታር በላይ ማደጉን ጠቅሰዋል፡፡
በመኸር የሰብል ልማት የእርሻ መሬትና በሄክታር የሚገኝ ምርታማነት በየዓመቱ እያሳየ የመጣውን ጭማሪ ተከትሎ ለቀጣዩ የ2018/19 የመኸር ወቅት 21 ነጥብ 8 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በዘር ለመሸፈን ግብ መቀመጡን ተናግረዋል፡፡
ለበልግ እርሻ 4 ነጥብ 2 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በዘር ለመሸፈን ታቅዶ እስካሁን 3 ነጥብ 8 ሚሊዮን ሄክታር መሬት መዘጋጀቱን ገልጸዋል፡፡
በኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ ለተመዘገበው ስኬት የአመራሩ ቁርጠኝነት ወሳኝ ሚና መጫወቱንም አንስተዋል፡፡
የኩታ ገጠም እርሻ መስፋፋት፣ የግብርና ሜካናይዜሽን ማሽነሪዎች አቅርቦት ማደግ፣ የአፈር ማዳበሪያና ምርጥ ዘር አቅርቦት መሻሻል ለግብርናው ዘርፍ እድገት ተጠቃሽ ምክንያቶች መሆናቸውን ገልጸዋል።
አዲስ አበባ፤ መስከረም 1/2019 (ኢዜአ)፦የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ከኃይል ማመንጫነት በላይ ትርጉም ያለው፣ የአፍሪካን የውስጥ...
Sep 14, 2026
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡት ግቦች መሳካት ጉል...
Sep 4, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 10/2018 (ኢዜአ)፡- ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን መቻሉን የአዲስ አበባና የድሬዳዋ አስተዳደር ሥነ...
Aug 17, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 4/2018 (ኢዜአ)፡-በአዳማ ከተማ ከልማት ሥራዎች ጎን ለጎን ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር መሸፈኑን የከተማዋ ግብርና ጽሕ...
Aug 11, 2026