የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የባቡር ሐዲድ

በክልሉ ባለፉት ዘጠኝ ወራት የተከናወኑ ተግባራት ህዝብን ተጠቃሚ ያደረጉ ናቸው

Apr 21, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ቦንጋ ፤ሚያዝያ 12/2018 (ኢዜአ)፦በክልሉ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ህብረተሰቡንና የልማት አጋሮችን በማሳተፍ የተከናወኑት ተግባራትህዝብን ተጠቃሚ ያደረጉ መሆናቸውንየደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) ገለጹ።

በክልሉ የመንግስትና የፓርቲ የዘጠኝ ወራት የስራ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ በቦንጋ ከተማ ተካሂዷል ።


የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ እንደገለጹት፤ በክልሉ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ህብረተሰቡንና የልማት አጋሮችን በማሳተፍ የተከናወኑት ተግባራት ለህዝብ የልማት ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡ ናቸው።

በመሰረተ ልማት፣ በገቢ አሰባሰብ፣ በግብርና፣ በስራ እድል ፈጠራ ፣ በጤና፣ በትምህርትና በሌሎችም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት አበረታች ውጤቶች መመዝገባቸውን ጠቅሰዋል።

በክልሉ የተመዘገቡ ልማቶች አበረታች ቢሆኑም ከክልሉ የመልማት አቅም አንፃር ገና ሰፊ ስራ የሚጠይቅ በመሆኑ ይበልጥ መትጋት እንደሚገባ ገልጸዋል።

ለዚህም የክልሉን አመራሮችና ሰራተኞች እስከታችኛው መዋቅር ድረስ በማቀናጀት ተከታታይነት ያለው ድጋፍና ክትትል ማድረግ እንደሚገባም አክለዋል።

ባለፉት ዘጠኝ ወራት በመንግስትም ሆነ በፓርቲ የተመዘገቡ ውጤቶችን ማስቀጠል ይገባል ያሉት ደግሞ የክልሉ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ፍቅሬ አማን ናቸው።


በተለይም አመራሩ ስራን በመገምገምና በቅንጅት በመስራት እንዲሁም ህብረተሰቡን በማስተባበር የመጡ ውጤቶችን ማስቀጠል እንዳለበት አስገንዝበዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የአፍሪካ የልማትና ትብብር ዓርማ - ታላቁ የሕዳሴ ግድብ በታዋቂው ታይም መጽሔት ገጽ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 1/2019 (ኢዜአ)፦የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ከኃይል ማመንጫነት በላይ ትርጉም ያለው፣ የአፍሪካን የውስጥ...

Sep 14, 2026

በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡ ግቦች መሳካት ጉልህ አስተዋጽኦ አለው-ዋምኬሌ ሜኔ

አዲስ አበባ፤ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡት ግቦች መሳካት ጉል...

Sep 4, 2026

ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን ተችሏል

አዳማ፤ ነሐሴ 10/2018 (ኢዜአ)፡- ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን መቻሉን የአዲስ አበባና የድሬዳዋ አስተዳደር ሥነ...

Aug 17, 2026

በአዳማ ከተማ ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር ተሸፍኗል

አዳማ፤ ነሐሴ 4/2018 (ኢዜአ)፡-በአዳማ ከተማ ከልማት ሥራዎች ጎን ለጎን ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር መሸፈኑን የከተማዋ ግብርና ጽሕ...

Aug 11, 2026