የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የባቡር ሐዲድ

ማህበሩ የኦሮሞን ህዝብ ታሪክ ለመሰነድና ትውልድን በእውቀት ለመቅረጽ ልዩ ትኩረት ሰጥቷል

Apr 23, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 14/2018 (ኢዜአ)፡- የኦሮሞ ምርምር ማህበር የኦሮሞን ህዝብ ታሪክ ለመሰነድና ትውልድን በእውቀት ለመቅረጽ ልዩ ትኩረት መስጠቱን ገለጸ።

ማህበሩ ከአምቦ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው 2ኛው ዓለም አቀፍ የምርምር ኮንፈረንስ መካሄድ ጀምሯል።


የማህበሩ የቦርድ ሰብሳቢ ፕሮፌሰር በቀለ ጉተማ፤ የኦሮሞ ምርምር ማህበር የኦሮሞን ህዝብ ታሪክ፣ ባህል፣ ቋንቋ እና የገዳ ስርዓትን በጥናትና ምርምር በመፈተሽ ለትውልድ ለማስተላለፍ በቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

የኦሮሞን ጥልቅ ዕውቀት መመርመርና ማሳወቅ፣ የህዝቡን ትናንት አጥንቶ ማስገንዘብ፣ ዛሬን መፈተሽና መተቸት፣ እንዲሁም የወደፊቱን እጣ ፈንታ መተንበይና አቅጣጫ መጠቆም ከማህበሩ ተልዕኮዎች ዋነኞች መሆናቸውን ገልጸዋል።

በተጨማሪም ማህበሩ ትውልዱን በማስተማርና የወደፊት ጉዞውን ለማቅናት የተለያዩ ጥናታዊ ጽሁፎችንና መድረኮችን በማዘጋጀት፤ ባህልና እሴቶችን ለተተኪው ትውልድ ለማስተላለፍ ምሁራንን በማሳተፍ ላይ እንደሚገኝም ገልጸዋል።

ማህበሩ ከተመሰረተ ጀምሮ የተለያዩ ኮንፈረንሶችን በማዘጋጀት ምሁራን በኦሮሞ ጉዳዮች ላይ ሃሳብ እንዲለዋወጡ ማድረጉን ገልጸው፤ በአሁኑ ወቅትም በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ምርምር እያደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።

በዚህም በባህላዊና ታሪካዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ አራት መጻህፍት በተለያዩ ቋንቋዎች አሳትሞ ማሰራጨቱን አስታውሰዋል።

በአሁኑ ወቅትም በስድስት የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ምርምሮች እየተካሄዱ መሆኑንና በቅርቡ ለህትመት እንደሚበቁም ጠቁመዋል።


የአምቦ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት ሰለሞን ማሾ (ዶ/ር)፤ ዩኒቨርሲቲው በኦሮሞ ባህልና እሴቶች ላይ በንቃት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

ከዚህም ባለፈ ዩኒቨርሲቲው በዘርፉ ከሚሰሩ ማናቸውም ተቋማት ጋር በቁርጠኝነት እየሰራ እንደሚገኝና ወደፊትም አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።


በኮንፈረንሱ ላይ የተገኙት የቀድሞው የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሙላቱ ተሾመ (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ መሰል የምርምር ተቋማት የህዝብን ታሪክ፣ ባህልና ማንነት ጠብቆ ለትውልድ ለማስተላለፍ ያላቸው ፋይዳ የላቀ መሆኑን ገልጸዋል።

ለሁለት ቀናት በሚቆየው በዚህ ዓለም አቀፍ ጉባኤ ላይ የተለያዩ ጥናታዊ ጽሁፎች ቀርበው ሰፊ ውይይት ይደረግባቸዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የአፍሪካ የልማትና ትብብር ዓርማ - ታላቁ የሕዳሴ ግድብ በታዋቂው ታይም መጽሔት ገጽ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 1/2019 (ኢዜአ)፦የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ከኃይል ማመንጫነት በላይ ትርጉም ያለው፣ የአፍሪካን የውስጥ...

Sep 14, 2026

በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡ ግቦች መሳካት ጉልህ አስተዋጽኦ አለው-ዋምኬሌ ሜኔ

አዲስ አበባ፤ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡት ግቦች መሳካት ጉል...

Sep 4, 2026

ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን ተችሏል

አዳማ፤ ነሐሴ 10/2018 (ኢዜአ)፡- ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን መቻሉን የአዲስ አበባና የድሬዳዋ አስተዳደር ሥነ...

Aug 17, 2026

በአዳማ ከተማ ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር ተሸፍኗል

አዳማ፤ ነሐሴ 4/2018 (ኢዜአ)፡-በአዳማ ከተማ ከልማት ሥራዎች ጎን ለጎን ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር መሸፈኑን የከተማዋ ግብርና ጽሕ...

Aug 11, 2026