የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የባቡር ሐዲድ

በክልሉ በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ የተከናወኑ የመሰረተ ልማት ማስፋፋት ሥራዎች ውጤታማነትን እያሳደጉ ነው

Aug 12, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ቡታጅራ፤ ነሐሴ 5/2018 (ኢዜአ)፡-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ የተከናወኑ የመሰረተ ልማት ማስፋፋት ሥራዎች የኢንዱስትሪውን ውጤታማነት ይበልጥ እያሳደገው መሆኑ ተገለጸ።

የክልሉ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ከ312 ሚሊዮን ብር በላይ ካፒታል ላስመዘገቡ ኢንዱስትሪዎች በቡታጅራ ከተማ ያስገነባቸውን የማምረቻ ሼዶች ዛሬ አስረክቧል።


የኮርፖሬሽኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ናትናኤል ሚሊዮን በዚሁ ወቅት፣ ኮርፖሬሽኑ የአምራች ኢንዱስትሪውን ውጤታማነት ለማሳደግ የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን አንስተዋል።

በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ የሚሰማሩ ባለሀብቶችን ከማበረታታት ባለፈ የመስሪያና የመሸጫ ሼዶችን ጨምሮ የመሰረተ ልማት ተደራሽነትን በማስፋፋት ለሥራቸው ምቹ ሁኔታ እየፈጠረም ይገኛል።

በዚህም በዘርፉ የተሰማሩ የግል ባለሀብቱን እና ሥራ አጥ ዜጎችን ተጠቃሚነት ማሳደግ መቻሉን ገልጸው፣ ከውጭ የሚገባ ምርትን በሀገር ውስጥ በመተካትም ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬን ለማዳን ተችሏል ብለዋል።

በዛሬው እለትም ከ312 ሚሊዮን ብር በላይ ካፒታል ላስመዘገቡ 7 አምራች ኢንዱስትሪዎች ስምንት ሼዶች የተላላፉ መሆኑን ገልጸው፣ ኢንዱስትሪዎቹ ከ 387 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ቋሚ የሥራ ዕድል እንደሚፈጥሩ ተናግረዋል።

አቶ ናትናኤል እንዳሉት፣ ኮርፖሬሽኑ አነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንዱስትሪዎችን በተለያየ መንገድ በመደገፍ በዘርፉ እየተመዘገበ ያለውን ተጨባጭ ውጤት ለማስቀጠል የጀመረውን ሥራ ያጠናክራል።

ዛሬ የማምረቻ ሼድ ከተላለፈላቸው ኢንዱስትሪዎች መካከል በዱራሜ ከተማ የከምባታ ቡና ማቀነባበሪያ ሥራ አስኪያጅ አቶ ምትኩ ሰልፊሶ በሰጡት አስተያየት ኢንዱስትሪው 150 ሚሊዮን ብር ካፒታል በማስመዝገብ መቋቋሙን ተናግረዋል።


በአሁኑ ወቅትም ከ150 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ቋሚና ጊዜአዊ የሥራ ዕድል እንደሚፈጥር ጠቁመው፣ በኮርፖሬሽኑ የተመቻቸላቸው የማምረቻ ሼድ ለስራቸው ውጤታማነት አጋዥ መሆኑን ገልጸዋል።

ሌላኛው በሀደሮ ከተማ በዝንጅብል ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪ ዘርፍ የተሰማራው የሱዳስ ግሩፕ ሥራ አስኪያጅ አቶ አስፋው አበበ በበኩላቸው ኢንዱስትሪው በ70 ሚሊዮን ብር የመነሻ ካፒታል ወደሥራ መግባቱን ተናግረዋል።


ኢንዱስትሪው ለ100 ዜጎች ቋሚና ጊዜያዊ የሥራ ዕድል በመፍጠር ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።

የማምረቻ ሼዶችን ለአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ለማስተላለፍ በተዘጋጀው መርሐ ግብር ላይ የክልል ከፍተኛ አመራሮችና በዘርፉ የተሰማሩ ባለሀብቶች ተሳትፈዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በአዳማ ከተማ ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር ተሸፍኗል

አዳማ፤ ነሐሴ 4/2018 (ኢዜአ)፡-በአዳማ ከተማ ከልማት ሥራዎች ጎን ለጎን ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር መሸፈኑን የከተማዋ ግብርና ጽሕ...

Aug 11, 2026

በባሕር ዳር ከተማ የተከናወኑ አበረታች የልማት እንቅስቃሴዎች የብልፅግና አቅጣጫዎችን በግልጽ ያመላከቱ ናቸው 

አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 30/2018 (ኢዜአ) ፦በባሕር ዳር ከተማ የተከናወኑ አበረታች የልማት እንቅስቃሴዎች የብልፅግና አቅጣጫዎችን በግልጽ ያመላከቱ መሆናቸውን ...

Aug 7, 2026

ፋይዳቨርስ በዲጂታል ሉዓላዊነታችንና በኢኮኖሚ ዕድገት ጉዟችን አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት ነው - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 28/2018 (ኢዜአ)፦ ፋይዳቨርስ በዲጂታል ሉዓላዊነታችንና በኢኮኖሚ ዕድገት ጉዟችን አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስ...

Aug 5, 2026

የቤኒን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እና ኢኖቬሽን ሚኒስትር ማሁና አክፕሎጋን የኢፌዴሪ መሶብ አገልግሎትን ጎበኙ

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 29/2018 (ኢዜአ)፦ የቤኒን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እና ኢኖቬሽን ሚኒስትር ማሁና አክፕሎጋን የኢፌዴሪ መሶብ አገልግሎትን ጎብኝተዋል። ...

Aug 5, 2026