🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 29/2018 (ኢዜአ)፦ የቤኒን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እና ኢኖቬሽን ሚኒስትር ማሁና አክፕሎጋን የኢፌዴሪ መሶብ አገልግሎትን ጎብኝተዋል።
የቤኒን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እና ኢኖቬሽን ሚኒስትር ማሁና አክፕሎጋን የተመራ የልዑካን ቡድን በኢትዮጵያ የአምስት ቀን የሥራ ጉብኝት ለማድረግ ትናንት ምሽት አዲስ አበባ መግባቱ ይታወቃል።
በዚህም መሰረት ሚኒስትሩና የልዑካን ቡድናቸው በኢፌዴሪ መሶብ አገልግሎት ጉብኝት እያደረገ ነው።

በኢፌዴሪ የመሶብ አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዮናስ አለማየሁ ለልዑኩ ገለፃ አድርገውላቸዋል።
ዋና ሥራ አስፈፃሚው በገለፃቸው በመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በአንድ ዓመቱ ውስጥ ከ200 በላይ የመንግሥት አገልግሎት በተሟላ መሰረተ ልማት ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት ተችሏል ብለዋል።
ይህም የኢትዮጵያ ቁልፍ የኢኮኖሚ መሰረተ ልማት እንደሆነ በመግለጽ ቅሬታ የሚበዛበትን የመንግስት አገልግሎት ግልፅና ቀልጣፋ ማድረግ መቻሉን ገልጸዋል።
መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የንግድና ኢንቨስትመንት እንቅስቃሴን በማሳለጥ ተጨባጭ ውጤት ማስመዝገቡን ተናግረዋል።
አገልግሎቱ የመንግስት ተቋማትን በማቀናጀት ተቋማት በአንድ ጣሪያ ስር ሁሉንም የመንግሥት አገልግሎት በፍትሐዊነት መስጠት አስችሏል ብለዋል።

የቤኒን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽንና ኢኖቬሽን ሚኒስትሩና ልዑካቸው በቆይታቸው ከመንግሥት ከፍተኛ የሥራ ሀላፊዎች ጋር በሁለትዮሽና ትብብርን ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ።
በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን፣ የህዝብ አስተዳደር፣ ኢኖቬሽንና ስትራቴጂያዊ አስተዳደር ላይ ልምድ ይለዋወጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 29/2018 (ኢዜአ)፦ የቤኒን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እና ኢኖቬሽን ሚኒስትር ማሁና አክፕሎጋን የኢፌዴሪ መሶብ አገልግሎትን ጎብኝተዋል። ...
Aug 5, 2026
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 28/2018 (ኢዜአ)፦ ፋይዳቨርስ በዲጂታል ሉዓላዊነታችንና በኢኮኖሚ ዕድገት ጉዟችን አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስ...
Aug 5, 2026
እምድብር፤ ሐምሌ 18/2018(ኢዜአ):- የቡና ጥራትና ምርታማነትን ለማሳደግ የተጀመሩ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን አስታ...
Jul 27, 2026
ዲላ፤ ሐምሌ 13/2018 (ኢዜአ)፦ በጌዴኦ ዞን በ2018/19 የመኸር አዝመራ ወቅት ከ44 ሺህ 700 ሄክታር በላይ መሬት ለማልማት ታቅዶ ወደ ትግበራ መገባቱን...
Jul 21, 2026