የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ማህበረሰብ እና ባህል

በድሬዳዋ አስተዳደር አምራች ኢንዱስትሪዎች ተኪና ወጪ ምርቶችን የማምረት አቅማቸው ጨምሯል

Apr 17, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ድሬዳዋ፤ ሚያዝያ 9/2018 (ኢዜአ)፦ በሀገራዊ ለውጡ ለአምራች ኢንዱስትሪዎች የተሰጠው ትኩረትበአስተዳደሩ የአምራች ኢንዱስትሪዎች ተኪና ወጪ ምርቶችን የማምረት አቅማቸው መጨመሩንየድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሀርቢ ቡህ ተናገሩ።

ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ ለኢንዱስትሪ ዘርፍ በተሰጠው ትኩረት እና ድጋፍ የአምራች ኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅም እየጨመረ ይገኛል።

በተለይም በኢንዱስትሪ ማዕከልነቷ በምትታወቀው ድሬዳዋ በኢትዮጵያ ታምርት ሀገራዊ ንቅናቄ ለረጅም ጊዜ የቆሙ በርካታ ኢንዱስትሪዎች ወደ ምርታማነት ገብተዋል።

የአስተዳደሩ ምክትል ከንቲባና የኢንዱስትሪና የኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሀርቢ ቡህ ለኢዜአ እንደተናገሩት፤ አምራች ኢንዱስትሪዎቹ ተኪ እና ወጪ ምርቶችን በዓይነትና በብዛት በማምረት የውጭ ምንዛሬን በማስቀረት እና በማስገኘት ላይ ናቸው።

በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ እየተደረገ በሚገኘው የተቀናጀ ድጋፍ እና ክትትል በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ ያሉ ችግሮች ተፈተው የማምረት አቅማቸው እንዲጨምርና ዘላቂ ዕድገት እንዲመዘገብ እያስቻለ ይገኛል ብለዋል።

በንቅናቄው የአምራች ኢንዱስትሪዎችን የፋይናንስ፣ የመሬት አቅርቦት፣ የመሠረተ ልማት እና የአገልግሎት አሰጣጥ ትኩረት በመሰጠቱ በዘርፉ የተከማቹ ጥያቄዎችን መፍታት እንዳስቻለ በማስታወስ።

ለአብነትም ከኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በፊት የአስተዳደሩ የአምራች ኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅም 42 በመቶ እንደነበር አስታውሰው፤ ዛሬ ላይ ወደ 62 ነጥብ 6 በመቶ ከፍ ማለቱንና ይኸም ተጠናክሮ መቀጠሉን ጠቅሰዋል።

በተጨማሪም ከንቅናቄው በፊት 6 አምራች ኢንዱስትሪዎች ብቻ ለውጭ ገበያ ያመርቱ እንደነበር አንስተው አሁን ላይ ወደ 13 ከፍ ብለው የውጭ ምንዛሬ እያስገኙ ይገኛሉ ብለዋል።

ከነዚህ ባሻገር ኢንዱስትሪዎቹ ከውጭ የሚገቡትን 69 ዓይነት ምርቶችን በራስ አቅም በማምረት የውጭ ምንዛሬ ከማዳን በዘለለ ቀደም ሲል የፈጠሩትን የስራ ዕድል በዕጥፍ በማሳደግ ከ24 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ ዕድል መፍጠራቸውን አውስተዋል።


እንደ አቶ ሀርቢ ገለፃ ድሬደዋ የነፃ ንግድ ቀጠና እና የደረቅ ወደብና ተርሚናል ባለቤት መሆኗ እንዲሁም ለጅቡቲ ወደብ ያላት ቅርበትና በሁሉም መሠረተ ልማቶች ከጅቡቲ ጋር መተሳሰሯ በዘርፉ ተመራጭነቷን አጉልቶታል።

በኮሪደር ልማቱም ከተማዋ ዘመናዊ የስራና የመኖሪያ ከተማ መደረጓን ተከትሎ በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ የሚሰማሩ ባለሃብቶች ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ እየጨመሩ መሆኑን በመጥቀስ።

እነዚህን ውጤቶች በላቀ ደረጃ በማሳደግ ድሬደዋ በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ሽግግር የተሳካባት ቀዳሚ የብልፅግና ማሳያ ትሆናለች ብለዋል።


በቢሮው የኢንቨስትመንት ፕሮሞሽንና ክትትል ቡድን መሪ አቶ አበራ መንግስቱ በበኩላቸው እንዳሉት፤ ባለፉት ዘጠኝ ወራት 354 ባለሃብቶች ከ59 ቢሊዮን 119 ሚሊዮን ብር በላይ ካፒታል አስመዝግበው ወደ ስራ ገብተዋል።

በአምራች ኢንዱስትሪ፣ በአገልግሎት፣ በኮንስትራክሽን እና በግብርና ዘርፎች ለተሰማሩት የሀገርና የውጭ ሀገራት ባለሃብቶች አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል በማድረግ በፍጥነት ወደ ስራ እንዲገቡ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።

ባለሃብቶቹ ወደ ማምረት ሲሻገሩ ለ11 ሺህ ሰዎች ቋሚ እና ለ7 ሺህ ሰዎች ደግሞ ጊዜያዊ የስራ ዕድል እንደሚፈጥሩ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በሀዋሳ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ ነው-ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ

ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...

Aug 27, 2026

በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12  ባለሀብቶች ላይ  እርምጃ ተወሰደ

ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...

Aug 14, 2026

በአማራ ክልል ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ተሰጠ

ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...

Aug 13, 2026

በክልሉ በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ ተችሏል 

ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...

Jul 31, 2026