🔇Unmute
አዲስ አበባ፣ሰኔ 28/2018 (ኢዜአ)፦በበጀት ዓመቱ የሀብት ማከፋፈያ ቀመሮች በአግባቡ መተግበራቸውን በቅርበት መከታተል መቻሉን የፌዴሬሽን ምክር ቤት የድጎማ በጀትና የጋራ ገቢዎች ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ሽመልስ አብዲሳ ገለጹ።
አቶ ሽመልስ አብዲሳ እንዳሉት በ2018 በጀት ዓመት በክልሎች መካከል የተመጣጠነ ልማትንና የዜጎችን ፍትሐዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በርካታ ውጤታማ ሥራዎች ተከናውነዋል።
የድጎማ በጀትና የጋራ ገቢዎች ክፍፍል ሥርዓት በጥናትና በተደራጀ ዕቅድ እንዲመራ ከማድረግ ባሻገር ወደ ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የሚተላለፉ ሀብቶች ግልጽና ፍትሐዊ በሆነ መንገድ እንዲከፋፈሉ ክትትልና ድጋፍ መደረጉን ተናግረዋል።

በበጀት ዓመቱ የሀብት ማከፋፈያ ቀመሮች በአግባቡ መተግበራቸውን በቅርበት መከታተል መቻሉን ገልጸዋል።
ይህም የሚተላለፉ ሀብቶች ላይ ግልጽነትን ለማሳደግና የበይነ መንግሥታት የፊስካል ሽግግር ሥርዓትን ለማጠናከር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱን አብራርተዋል።
በተጨማሪም የፌዴራል መሠረተ ልማት ስርጭት ፍትሐዊነትን ማስፈን እንዲሁም ልዩ ዓላማ ያላቸው ድጎማዎች በግልጽነትና በተጠያቂነት መርህ ለክልሎች መከፋፈላቸውን ማረጋገጥ የኮሚቴው ዋና ዋና ስትራቴጂካዊ ተግባራት እንደነበሩ አመልክተዋል።
የኢኮኖሚና የማሕበራዊ ዕድገትን ማፋጠንና በክልሎች መካከል ፍትሐዊ ተጠቃሚነትን እውን ማድረግ የረጅም ጊዜ ጥረት እንደሚጠይቅ ገልጸው ማነቆዎችን በመለየትና መረጃዎችን በወቅቱ በማሰባሰብ ዘላቂ መፍትሔዎችን ለማምጣት ይሰራል ማለታቸውን የፌዴሬሽን ምክር ቤት መረጃ ያመለክታል።
ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...
Aug 27, 2026
ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...
Aug 14, 2026
ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...
Aug 13, 2026
ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...
Jul 31, 2026