የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ማህበረሰብ እና ባህል

በአማራ ክልል የቱሪዝም መዳረሻ ልማትና የቅርስ ጥበቃ ስራ ከፍተኛ ስኬት የተመዘገበበት ነው

Jul 7, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ባህር ዳር፤ ሰኔ 29/2018(ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል የቱሪዝም መዳረሻ ልማትና የቅርስ ጥበቃ ስራ ከፍተኛ ስኬት የተመዘገበበት መሆኑን የክልሉ ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ገለጸ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) “ቱሪዝም አዲሱ የኢኮኖሚ ሞተር!” በሚል ከቀናት በፊት በሰጡት ማብራሪያ የብዝሃ የኢኮኖሚ አማራጮችን መሰረት በማድረግ በተለይም በቱሪዝም ዘርፍ የተመዘገበውን ዘርፈ ብዙ ስኬት ገልጸዋል።

በተለይም የገበታ ፕሮጀክቶች ግንባታ፣ የከተሞች ኮሪደር ልማትና የቅርሶች እድሳትና ሌሎችም ተግባራት ለዘርፉ እድገትና ማንሰራራት ወሳኝ ስለመሆናቸው አንስተዋል።


ከዚህ አንፃር በአማራ ክልል በቱሪዝም ልማት የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትንና የመጡ ለውጦችን በማስመልከት የክልሉ ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ሃላፊ መልካሙ ፀጋየ ከኢዜአ ጋር ቆይታ አድርገዋል።

በቆይታቸውም ባለፉት ጥቂት ዓመታት በገበታ ለሀገርና ለትውልድ የተከናወኑ አስደናቂ የቱሪዝም ልማት ፕሮጀክቶችን፣ የቅርሶች እዲሳት እንዲሁም በከተሞች ኮሪደር የተከናወኑ ሰፊ ስራዎችን አንስተዋል።

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሃሳብ አመንጪነት፣ ጠንካራ ክትትልና ድጋፍ ጭምር የተሰሩት የጎርጎራ ኢኮ ሪዞርት እና የለጎ ሃይቅ ሪዞርት በጉልህ የሚነሱ ናቸው ብለዋል።

እነዚህ ፕሮጀከቶች ዓለምአቀፍ ደረጃን የጠበቁ፤ በፍጥነትና በጥራት የተገነቡ ዘመን ተሻጋሪ አሻራ ያረፈባቸው ድንቅ ስራዎች መሆናቸውን አንስተዋል።


የፋሲል አብያተ መንግስታትን ጨምሮ ሌሎች ነባር ቅርሶችን በማደስ፣ በመንከባከብና ይበልጥ በማስዋብ የሃብት ምንጭ ከማድርግ ባለፈ በመጠበቅ ከተጋረጠባቸው የህልውና አደጋ መታደግ የተቻለበት እንደሆነም ነው ያነሱት።

በእነዚህና በዘርፉ ልማት በተከናወኑ ዘርፈ ብዙ ተግባራት በክልሉ የቱሪዝም ዘርፍ እድገትና ማንሰራራት እያሳየ መምጣቱን ገልጸዋል።

በዚህም ዓመት የውጭና የሀገር ውስጥ ጎብኚዎች ቁጥር ማደጉን ጠቅሰው ከ16 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ማግኘት ተችሏል ብለዋል።

በዘርፉ የ25 ዓመት አሻጋሪ የልማት ዕቅድ ተዘጋጅቶ እየተተገበረ መሆኑን ጠቁመው ክልሉ ያለውን እምቅ የቱሪዝም ሃብት የማልማትና ይበልጥ የማስተዋወቅ ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉንም ገልጸዋል።

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በተለይም የፋሲል አብያተ መንግስታት፣ የሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ፣ የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናትና ሌሎችም በጎብኚዎች ተመራጨ የጉብኝት መዳረሻዎች እንደነበሩ ከቢሮው የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በሀዋሳ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ ነው-ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ

ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...

Aug 27, 2026

በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12  ባለሀብቶች ላይ  እርምጃ ተወሰደ

ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...

Aug 14, 2026

በአማራ ክልል ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ተሰጠ

ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...

Aug 13, 2026

በክልሉ በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ ተችሏል 

ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...

Jul 31, 2026