🔇Unmute
ቦንጋ፤ ሰኔ 29/2018(ኢዜአ)፦ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል በ2018/19 የመኸር አዝመራ ከ463 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በተለያዩ አዝርእቶችና በሆርቲካልቸርሰብሎች እንደሚለማ ተገለጸ።
በክልሉ ያለፈው አመት አፈጻጸምና የ2018/19 የመኸር ግብርና ስራዎችን አስመልክቶ የንቅናቄ መድረክ በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ነው።

የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደርና ግብርና ቢሮ ኃላፊ ማስረሻ በላቸው፣ በክልሉ የግብርናውን ዘርፍ በማጠናከር የማይታረስ መሬት እንዳይኖር የተሰጠው ትኩረት ውጤት እያስገኝ ነው ብለዋል።
በዚህም በበልግና በመኸር በአጠቃላይ በክልሉ የሚታረስ መሬት ወደ አንድ ሚሊየን ሄክታር የደረሰ ሲሆን ክልሉ ካለው እምቅ አቅም አንፃር ሲታይ በርካታ ስራዎች ማከናወን እንደሚገባም ነው የተናገሩት።
በ2017/18 የመኸር እርሻ 421 ሺህ ሄክታር ማሳ በተለያዩ ሰብሎች በማልማት 17 ነጥብ 7 ሚሊየን ኩንታል ምርት መሰብሰቡን አስታውቀዋል።
በዘንድሮው የ2018/19 የመኸር ወቅትም ከ463 ሺህ ሄክታር ማሳ በአዝርት በመሸፈን ከ20 ነጥብ 5 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት ለመሰብሰብ ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል።
በዚሁ ወቅት ከሚለማው 463 ሺህ ሔክታር መሬት ውስጥ 109 ሄክታሩ በክላስተር እንደሚለማም ጠቁመዋል።

የተያዘውን ግብ ለማሳካት የግብርና ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ማሳደግን ጨምሮ የሚሰጡ ምክረ ሀሳቦችን ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባም ነው ያሳሰቡት።
ሰርቶ ማሳያዎችን በተሟላ ቴክኖሎጂ በማልማት ለአርሶ አደሩ ማስተዋወቅ እንደሚገባ ጠቁመው የግብርና ባለሙያዎችና በየደረጃው የሚገኙ ባለድርሻ አካላትም ድጋፋቸውን ማጠናከር ይገባቸዋል ብለዋል።
በመድረኩ የክልል፣ የዞን ከፍተኛ አመራሮች የግብርና ጽህፈት ቤት ኃላፊዎችና የሚመለከታቸው አካላት ተሳትፈዋል።
ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...
Aug 27, 2026
ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...
Aug 14, 2026
ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...
Aug 13, 2026
ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...
Jul 31, 2026